Get Mystery Box with random crypto!

🇪🇹ኢትዮ-ዚያራ/ETHIO-ZIYARA

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioziyara — 🇪🇹ኢትዮ-ዚያራ/ETHIO-ZIYARA
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioziyara — 🇪🇹ኢትዮ-ዚያራ/ETHIO-ZIYARA
የሰርጥ አድራሻ: @ethioziyara
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 575
የሰርጥ መግለጫ

👉👳 በመላው ሀገራችን ያሉ ደፋ ቀና የሚሉ ዑለማወቻችንን ደረሶቻችንን መዘየር🤝
👉🕌 ታሪካዊ ኢስላሚክ ቦታወችን መጐብኘት
👉📙 አውንታዊ ታሪኮች የምናወሳበት..
👉📰 አዳድስ መረጃወች..
👉📚 ለመሻይኾቻችን በቻልነው አቅም ድጋፍ ማድረግ 💸 ለምሳሌ ; ቁርዕን፣ኪታቦች፣አልባሳት ... insha'Allah በ አላህ ፍቃድ እንዲሳካልን በዱዕ እንበርታ።
ለዚህ ኒያችን Allah ወኪል።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-03 17:12:36 የሸዋል ጾም
=======
ከአቡ አዩብ አል‐አንሷሪይ [ረዐ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ረመዳንን ጾሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው ይህ ዓመቱን እንደጾመ ይቆጠርለታል።» ሙስሊምና ሌሎችም ዘግበውታል።
ከጃቢር [ረዐ] እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ረመዳንን የጾመ ከዚያም ከፊጥር በኋላ ስድስት ቀናትን ያስከተለ ሰው አመቱን በሙሉ እንደጾመ ይቆጠራል። አንድን መልካም ስራ የሰራ ሰው በዐስር አምሳያዎቹ ይባዛለታል።» ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።
:
የመልካም ስራ ምንዳው በዐስር ይባዛል። ስለዚህ የረመዳን ጾም በዐስር ሲባዛ ዐስር ወራት ይሞላል። የሸዋል ስድስት ቀናት በዐስር ሲባዙ ስድሳ ቀናት ይሆናሉ። ሁለት ወር ማለት ነው። ስለዚህ ሰውየው ሙሉ አመቱን እንደጾመ ይቆጠርለታል።
:
የዒድ ማግስትን ማስከተል
=================
በሁለቱ ሐዲሶች መሰረት ስድስቱን ቀን ከዒዱ ቀን ማግስት ጀምሮ በመሀል ምንም ክፍተት ሳይኖር መጾም እንደሚወደድ ያመለክታሉ። ሻፊዒዮቹ ይህንን ሃሳብ ይመርጣሉ። ምክንያቱም በዚህ መንገድ መልካም ስራን በማከታተሉ ጾሙን እንዳይተወው ያግዘዋል። በሰፊው የሀገራችን ክፍል ከአባቶቻችን ጀምሮ የለመድነው አካሄድም ይህንን መሰረት ያደረገ ነው።
:
በእርግጥ ሐዲሶቹ ቀናቶቹን አከታትሎ መደርደር መልካም መሆኑን በይበልጥ የሚያመለክት ስሜት ቢኖራቸውም ቀናቶቹን አለያይቶ እያረፉ መጾም ችግር እንደሌለውም ይጠቁማሉ።
ስለዚህ ከዒዱ ዋዜማ አንስቶ እስከ ሰባተኛው ቀን ድረስ የጾመ ሰውም ሆነ አዘግይቶ ሰብስቦ በማከታተል ወይም እያረፈ ነጣጥሎ የጾመ ሰው ሱናውን አግኝቷል። ይህ ሻፊዒዮቹ፣ አሕመድ እና አብዝሀኞቹ ዑለሞች ዘንድ የተረጋገጠ ሃሳብ ነው።
:
ሐነፊዮቹ ተመራጭ ያደረጉት ሃሳብ ስድስቱን የሸዋል ቀናት መጾም ችግር የለውም [ይወደዳል ሳይሆን] የሚለውን ሃሳብ ነው። በእርግጥ ከሐነፊዮች ከፊሎቹ አከታትሎ መጾም ይጠላል ያሉበት ሁኔታም ነበር። ለዚህ ድምዳሜ ምክንያት ያደረጉት ከሸዋል ስድስት ቀን መጾም ከረመዳን ጋር እንዳይመሳሰል ወይም ተጨማሪ ግዳጅ እና ድንጋጌ እንዳይመስል መስጋታቸውን ብቻ ነው። ከኢማም ማሊክም ተመሳሳይ ሃሳብ ተሰንዝሯል። ነገርግን የዒድን ቀንን በማፍጠር ከረመዳን ጋር የመመሳሰል ስሜቱ ስለሚጠፋ ሸዋልን መጾሙ ችግር የለውም የሚለውን ሀሳብ ብዙዎቹ ሐነፊዎች መርጠውታል። "አልሂዳያ" "አልጋያ" የተሰኙ መፅሀፍቶቻቸው ይህንን አብራርተዋል።
:
በርግጥም ከላይ የጠቀስናቸው ሐዲሶች የስድስቱ የሸዋል ቀናት ጾም ተወዳጅ መሆኑን ያረጋግጣሉ። ሐዲሶቹ መከራከሪያ ለመሆን ብቁ የሆኑ ግልፅ መረጃዎች ናቸው። ስለዚህ ሳንጠራጠር በዚሁ መንገድ መጓዝ እንችላለን።
:
ከሌላ ኒያ ጋር ማቆራኘት
===============
የስድስቱ ቀን ጾም ላይ ቀዳእን ጨምሮ በመነየት መጾም ይፈቀዳል። ሰውየው የሁለቱንም ምንዳ ያገኛል። ኢማም ሲዩጢይ [ረዐ] 'አል‐አሽባህ ወን‐ነዟኢር' በተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ እንዲህ ይላሉ: ‐ "ለምሳሌ በዐረፋ ቀን ከዐረፋ ጾም ጋር ቀዷእን፣ የስለት ጾምን፣ ከፋራን… በአንድ ላይ ነይቶ መጾም አስመልክቶ እንደሚፈቀድና ምንዳውም እንደሚገኝ አል‐ባሪዚይ ፈትዋ ሰጥተዋል። እንደውም እለቶቹን ልቅ በሆነ የጾም ኒያ ቢያሳልፈውም የስድስቱን የሸዋል ጾም ምንዳ ያገኛል ብለዋል። እርሳቸው የሸዋልን ጾም በተሒይ‐የቱል‐መስጂድ ሶላት መስለውታል።"
ማንኛውም ሰው መስጂድ ገብቶ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዐና ከዚያ በላይ የሆነ ማንኛውም ሶላት ቢሰግድ ተሒያን ቢነይትም ባይነይትም የተሒያውን ምንዳ እንደማያጣው፣ ፈርድ ወይም ሱና ሲሰግድ አብሮ ተሒያን መነየት እንደሚፈቀድለት ሁሉ የሸዋል ጾምም በዚሁ አኳያ መታየት አለበት እያሉ ነው።
ምክንያቱም ተሒይ‐የቱል መስጂድ ያስፈለገው ሰውየው መስጂድ ሲገባ ከመቀመጡ በፊት ሶላት እንዲሰግድ ማድረግ ብቻ ነው። ስለዚህ በማንኛውም ሶላት ይህንን ማሳካት ስለሚችል ተሒያውን ያገኘዋል።
የተሒይ‐የቱል መስጂድ ድንጋጌን አስመልክቶ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ "እያንዳንዳችሁ መስጂድ ስትገቡ ሁለት ረከዐ ሳትሰግዱ አትቀመጡ።"
በሸዋል ወር ያሉት የስድስት ቀናት ጾምንም አል‐ባሪዚይ እና በርካታ መሰሎቻቸው እንደዚሁ ተመልክተውታል።
በዚህ መሰረት ሱና ጾም በፈርድ ውስጥ መካተት እንደሚችል ዐሊሞች [በተለይ ሻፊዒዮች] ጠቁመዋል። ነገርግን ፈርድ ጾም በሱና ጾም ኒያ ውስጥ መካተት አይችልም።
:
ስለዚህ ሴቶች በረመዳን በወር አበባ ምክንያት ያመለጣቸውን ከሸዋል ጾም ጋር በአንድ ላይ በመነየት ቀዳቸውን መክፈል ይችላሉ ማለት ነው።
ነገርግን በቅድሚያ ቀዷቸውን ቢከፍሉ ከዚያም ሸዋል ሳይወጣባቸው የሸዋልን ጾም ቢጾሙ፤ ወይም በተቃራኒው መጀመሪያ የሸዋል ስድስቱን ጾም አስቀድመው ቢጾሙ ከዚያም ቀዳቸውን አስከትለው ቢከፍሉ የተሻለ ነው። ምክንያቱም ደርቦ በመጾም ምንዳ ያገኛል ማለት ነጣጥሎ በመጾም የሚገኘውን የተሟላ ምንዳ ያገኛል ማለት አይደለም። ነጣጥሎ በተለያዩ ጊዜያት ኒያውን ሳያደራርብ የጾመ ሰው ኒያዎችን አደራርቦ ከጾመ ሰው የበለጠ ምንዳ አለው።
:
ኢማም ረምሊይ [ረዐ] እንዲህ ይላሉ: — "በሸዋል ወር ቀዳእን፣ ስለትን እና ሌሎች ጾሞችን የጾመ ሰው የሸዋል ሱና ጾምን ምንዳ ያገኛል። ይህ አባቴ [ረሒ] አል‐ባሪዚን፣ አል‐አስፈዊን፣ አን‐ናሺሪን፣ አል‐ፈቂህ ቢን ሷሊሕ አል‐ሐድረሚን እና ሌሎችንም ዋቢ በማድረግ የሰጡት ፈትዋ ነው። ነገርግን ረመዳንን በስድስት የሸዋል ቀናት ጾም አስከትሉት የተባለበትን የተሟላ ምንዳ አያገኝም።"
:
የስድስቱ ቀናት የሸዋል ጾም በፈርዱ ላይ የተከሰተን ጉድለት ይሞላል። የረመዳን ጾም ተቀባይነት ማግኘቱን ይጠቁማል። ምክንያቱም መልካም ስራ ተቀባይነት ማግኘቱን ከሚጠቁሙ ምልክቶች መሀል አንዱ ወዲያው መልካም ስራን ማስከተል ነው። ሰውየው አላህን ማምለክ እንደማይሰላች ማረጋገጫም ይሆናል።
የሸዋል ጾምም ሆነ የማንኛውም ሱና ጾምን ኒያ በሌሊት ብቻም ሳይሆን እስከ ዙህር ባለው ሰዓት ማስገኘት ይቻላል።
:
በመልካም ነገር ላይ እንተጋገዝ። እንዘያየር። በሸዋል ጾም አደራ እንባባል።
መልካም ዒድ!
http://t.me/fiqshafiyamh
114 viewsBin Baba Ali, 14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-12 10:16:31
238 viewsBin Baba Ali, 07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-12 11:43:47
إنا لله وإنا إليه راجعون
የሱመያ መስጂድ ኢማም እና ኸጢብ ታላቁ ሸይኽ ሰዒድ ወደ ማይቀርበት አኼራ አልፈዋል። ሊላሂ ተዓላ ብለን ሁላችንም ፋቲሃ እንቅራላቸው።
لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُقْبَضَ الْعِلْمُ
"የትንሳኤ ቀን አትደርስም ዒልም እስካልተነሳ ድረስ"
የዒልም ምንጮቹ ደግሞ ኡለሞች ናቸውና ሁላችንም ዱዓ እናድርግ አሏህ ቀብራቸውን ሰፊ መኖሪያቸውን ጀነት ከነብያቶች፤ ከወልያቶች እና ከሸሂዶች ጋር ያድርገው።
**********************************************
አስ - ሱናህ TV ''ሚዛናዊ መርህ || قناة السنة نهج الاعتدال ||
As-Sunnah TV ''The Way Of Moderation'' ||
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCnUcEEmMpVeXIoW01gKnxIQ
የጽሑፍ እና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት በፌስቡክ ገጻችንን Like ያድርጉ
https://www.facebook.com/AssunnahTVOfficial
የጽሑፍ እና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ወደ ቴሌግራም ቻናላችን Join ያድርጉ
https://t.me/AssunnahTVOfficial
አስተያየትና ምክረዎን ለመለገስ በWhatsapp ወይም በቀጥታ ስልክ ቁጥራችን በመደወል ያድርሱን
+251 90 300 0102
268 viewsBin Baba Ali, 08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-12 08:59:09
ኢናሊላህ ወኢናኢለይሂ ረጅኡን በጣም ትልቅ ዐሊም በጣም ትልቅ ሰዉ አጣን ወላሂ በጣም ጥልቅ ሀዘን ነዉ

ኢናሊላህ ወኢና ኢላሂ ራጅኡን
"እኛ የአላህ ነን ወደ እርሱም ተመላሾች ነን"

كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوْنَ أُجُورَكُمْ يَوْمَ الْقِيَامَةِ ۖ فَمَن زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ ۗ وَمَا الْحَيَاةُ الدُّنْيَا إِلَّا مَتَاعُ الْغُرُورِ
299 viewsBin Baba Ali, 05:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-12 06:36:23 ተቀጣሪ ሰራተኛ ሆነህ የመስክ ስራዎችን የምታዘወትር ከሆነ፣ በየሳምንቱ ወይም በየወሩ ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን ከመኖሪያህ ርቀህ ስራህን ስትጨርስ ወደ መኖሪያህ የምትመለስ ከሆነ…
ተማሪ ከሆንክ፣ በየቀኑ ከአካባቢህ ርቀህ እየቆየህ ተመልሰህ ወደ መኖሪያህ የምትመለስ ከሆነ…
የረዥም ርቀት ሹፌር ከሆንክ፣ በቋሚነት ጉዞ ብታዘወትርም በየሁለት ወይም ሦስተ ቀን ወደ ቤትህ የምትመለስ ከሆነ…
:
ሶላት ማሳጠር ትችላለህ። ዙህር፣ ዐስርና ዒሻእን ሁለት ሁለት ረከዓ እያደረግክ መስገድ ትችላለህ። መግሪብና ሱብሒን ግን ባሉበት ተዋቸው።
ዙህር እና ዐስርን፣ መግሪብና ዒሻን ሰብስበህ መስገድም ትችላለህ።
ነገርግን ይህን የምታደርገው ከአካባቢህ በራቅክበት ጊዜ ነው። ወደ ቀዬህ ስትመለስ ግን በመደበኛ ሁኔታው ስገድ።
አላሁ አዕለም!
https://t.me/fiqshafiyamh
174 viewsBin Baba Ali, 03:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-23 00:17:02
181 viewsBin Baba Ali, 21:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-23 00:16:32
167 viewsBin Baba Ali, 21:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-23 00:15:52
143 viewsBin Baba Ali, 21:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-23 00:14:52
134 viewsBin Baba Ali, 21:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-23 00:14:52
133 viewsBin Baba Ali, 21:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ