Get Mystery Box with random crypto!

ፍቅር❤️ እና ሳቅ™😂

የቴሌግራም ቻናል አርማ love_laugh19 — ፍቅር❤️ እና ሳቅ™😂
የቴሌግራም ቻናል አርማ love_laugh19 — ፍቅር❤️ እና ሳቅ™😂
የሰርጥ አድራሻ: @love_laugh19
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.03K
የሰርጥ መግለጫ

➳ፍቅር ጣፋጭ ነው
➳ፍቅር ሰላም ነው
➳ፍቅር እርካታ ነው
➳ፍቅር እማይጠገብ ነው
➳ፍቅር እማያልቅ ነው
➳ፍቅር ዘር ቀለም ሀብት መልክ #እማይጠይቅ
➳የውስጥ ስሜት ነው
••┈┈• ♡ ••┈┈•••┈┈•
የቻናሉን አባላት ለማብዛት ስንል promotion ስለምንሰራ እንዳትሰላቹ
For cross & comment👉
@Yfiker_ena_sak_bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-18 09:47:56 የቆሙ ሰዎች እንዳያቆሙህ!

አንዳንድ ሰዎች የሚተቹ ቃላትን መሰንዘር ልማድ ይሆንባቸዋል ፤ ምንም ሳይሰሩ በሚሰራው ሰው ቦታ ላይ ሳይቀመጡ በእርሱ ሚዛን የመመዘን ብቃቱም ሳይኖራቸው አንተ እኮ አትረባም ይሉታል!

ኳስ ሜዳ ላይ ያሉ ደጋፊዎች እንዲህ አድርግ እንዲያ አታድርግ እያሉ አስተያየት የሚወረረውሩ ለአንድ ደቂቃ እንኳን እሱን መሆን እና ሜዳው ገብተው ለመጫወት ብቁ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው ! ምናልባት እድሉን ቢያገኙት የተጫዋቹን ሩብ ታህል ብቃት አያሳዩም ! " ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ" አደል የሚባለው ! ለማይሰራ ሰው አስተያየት መስጠት ይቀለዋል ስለዚህ እከሌ ተቸኝ እከሌ በስራዬ አሾፈብኝ ስሜት የሚጎዳ መጥፎ አስተያየት ሰጠኝ እያልክ መንገድህን እንዳታቆም ያመንክበትን ነገር በደንብ ከልብህ ጠንክረህ ስራበት በፍፁም እንዳትቆም ! የቆመ ሰው ሌላውን ማስቆም ነው እና አላማው ነቅተህ ራስህን አድነው!

ደስ የሚል ሀሙስ ተመኘን
@Maryam_2121
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ
865 viewsℤ𝕖𝕣𝕚𝕙𝕦𝕟, 06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 22:04:03 ​​​​​​​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ ⸙━━━━ ◈

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ ●•٠·˙

⚀ የመጨረሻው ክፍል ⚀

.....ጆሮዬን ከሀዲዱ ጋር አጣብቄ አዳመጥኩ ግምቴ ልክ ነበር ። ድምፅ ሰማው።
ቶሎ ብዬ ሀዲዱ ላይ ተቀምጬ እራሴን ከሀዲዱ ጋር መተብተብ ፣ መጠፈር ያዝኩ። ቀድሜ ሁለቱ እግሮቼን ከሀዲዱ ጋር ጠፍሬ አሰርኩት። ቀጥዬ እጅና እጆቼን አጠላልፌ አሰርኳቸው።
ከዚያ ባቡሩን መጠበቅ ጀመርኩ። ፍሌሜን አጥቼ መኖር ስለማልችል ፣ እሷ ሞታ በመቃብሯ ላይ ቆሜ እህህ እያሉ ቀን መግፋት ስለማይሆንልኝ ባቡሩ ድጦኝ እንዲያልፍ ፈቅጃለሁ።
ባቡሩ ቢቀርበኝና ህይወት አሳስታኝ ልትረፍ ብል እንኳን እራሴን ሆነ ብዬ ከሀዲዱ ጋር ተብትቤዋለሁ ለመፍታትም ባቡሩ ጊዜ አይሰጠኝም።
የባቡሩን ሀዲድ እና ትብታቡን አንቼ ቀና ስል.....
.
ባቡሩ እየገሰገሰ ወደእኔ እየመጣ ነው።ግፋ ቢል ሁለት ደቂቃ ቢቀረው ነው።
የአሸዋውን አቧራ እያቦነነ መጣ። ልቤ ተሰቀለች። መሞት ፈራው። ልቤ ቶሎ ቶሎ ትመታ ጀመር።
እናቴን አሰብኳት ፣ የታሰረ አባቴን አሰብኩት፣ፍሌሜን አሰብኳ ፣ ትርሃሴን አሰብኳት.....ቀና ስል...አንዲት ልጃገረድ ቢጤ እየሮጠች ወደ እኔ ስትመጣ ተመለከትኩ።
በደንብ ስትቀርብ ሳያት ለየዋት። ፍሌም ነች።ባቡሩን አየውት በጣም እየቀረበኝ ነው። መልዓከ ሞትን አስቀድሞ የሚገሰግስ የሞት ሰራዊት መሰለኝ ።
ፍሌም ሻርቧን ነፋሱ ነጥቋት ሲሄድ እያየው ወደ እኔ እየሮጠች " ግሩም..! ግሩም..!" አለች።....ባቡሩ ፈጠነ።
እኔም የታሰርኩበትን ትብታብ በደመ ነፍስ መፈታታት ጀመርኩ።
ባቡሩ ቀ.....ረ......በ... በፍጥነት የእጄን ትብታብ ፈትቼ ወደ እግሬ ገባሁ። አንዱ እግሬን ፈትቼ ስጨርስ ቀግምት 8 ወይም 7 ደቂቃ ያህል ቢቀረው ነው።
ፍሌሜ በደረቷ አሸዋው ላይ እራሷን ስታ ወድቃለች።
ትብታቡን ለመፈታታት እታገላለሁ። ባቡሩ ሊድጠኝ ይገሰግሳል..........


❂───── ❁ ተ ፈ ፀ መ ❁ ───── ❂

━━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ ⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃


አጨራረሱ ላይ ብዙዎቻችሁ ደስተኛ እንደማትሆኑ ይገባኛል ።

ዋና አላማው የአጨራረሱ ጉዳይ እናንተን የልቦለዱ አካል በማድረግ #ውሳኔ እንድትሰጡ ማለትም ሁሉም ሰው የራሱን ግምት እንዲያስቀምጥ የተተወ ቦታ ነው ። አንዳንዴም ያለቀለት ከማንበብ በራሳችን የአፃፃፍ ስልት መጨረስ መቻል አለብን ። ሌላው ይሄ አንድ ራሱን የቻለ የአፃፃፍ ስልት ወይም ዘዴ ነው።

ግን የተሰማችሁን ስለምታደርሱልን እናመሠግናለን ።
በእግዚአብሔር ፍቃድ በሌሎች ስራዎችም እንገናኛለን።
867 views የፍቅ ታሪክ , 19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 21:57:42 ​​​​​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ ⸙━━━━ ◈

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ ●•٠·˙

⚀ ክፍል ሀያ አንድ ⚀


.
ፍሌሜም እኔ ፊት ደስተኛ ሆና ለመታየት ፈገግ ትላለች። ያ ውብ ዲንፕሏ ድምቀቱ ጠፍቶ የበርባሮስ ጉድጓድ መስሏል።
ሽማግሌው የፍሄሜን የመዳን ጉጉት በእኔ ውስጥ አሻግሮ ከተመለከተ በኃላ ሊያድናት የሚችል የባህል መድሃኒት እንዳለና ሁለት ሳምንታት እንደሚፈጅ ነገረኝ።ሌላ ሰው ልከው እንዳልተመለሰ ሲነግሩኝ አላመነታሁም።ይህን ዜና በሰማው ማግስት ሰማይና ምድር ተራክቧቸውን አጠናቀው ሲለያዩ ማልጄ ጉዞ ጀመርኩ።
.... የአስር ቀናት ጉዞን ተጉዤ በሀረር አቅጣጫ ወደ ገጠሩ ዘልቄ የተባለውን መድሃኒት ይዤ ግመሌን እየጎተትኩ 18 ቀን ከፈጀ አድካሚና አሰልቺ ጉዞ በኃላ ድሬ ገባሁ።
የእለቱ ፀሀይ ሀሩር ነበር። ረጫሞው እንደጉድ ይፋጃል። ፍሌሜ ወዳለችበት መንደር ስቃረብ ደነገጥኩ ሀሞቴ ፍስስ አለ ብዙ ሰው ጭንቅላቱን ይዞ እያለቀሰ ፍሌም ወዳለችበት ጊቢ ይገባል ይወጣል። ይህን ሳይ እግሬ ቄጤማ ሆነ። ሆዴ ክፉኛ ተሸበረ ውስጡ የነበረው የመኖር ተስፋ እየተሟጠጠ ቀፎ ሲሆን ይሰማኛል።
ከግመሏ ጀርባ ላይ ገመድ ፈትቼ ወደ ኃላ ወደ በረሃው ሸሸው።
ከለቀስተኞች ውስጥ ስመለስ አይቶ የተከተለኝ ስለመሰለኝ ረጅም መንገድ ሮጥኩ።
ከዚያ ዙሪያ ገባውን ቃኘውት። በረሃ ነው አንድም ዛፍ የለም።
አንድ ሀሳብ መጣልኝ ከርቀት የባቡር ጣቢያ ቤት ነገር አየው። መቆጣጠሪያው ነው ብዬ ገመትኩ።
ወደ እግሬ ተመለከትኩ የቆምኩት የባቡር ሀዲድ ላይ ነው።
ላቡ እንደ ጅረት በክንድ እና ክንዷቼ ላይ እየተንቆረቆረ ውሃ ወደ ማይጠግበው የበረሃው አሸዋ ላይ ይንጠፈጠፋል።
ቀና ብዬ ፀሀይዋን አየዋት በአናቴ ትክክል ናት። አሁን የከሰዓቱ ባቡር ከተለያየ አቅጣጫ ድሬ የሚገባበት ሰዓት ነው።
ጆሮዬን ከሀዲዱ ጋር አጣብቄ አዳመጥኩ ግምቴ ልክ ነበር ። ድምፅ ሰማው።
ቶሎ ብዬ ሀዲዱ ላይ ተቀምጬ እራሴን ከሀዲዱ ጋር መተብተብ ፣ መጠፈር ያዝኩ። ቀድሜ ሁለቱ እግሮቼን ከሀዲዱ ጋር ጠፍሬ አሰርኩት። ቀጥዬ እጅና እጆቼን አጠላልፌ አሰርኳቸው።
ከዚያ ባቡሩን መጠበቅ ጀመርኩ። ፍሌሜን አጥቼ መኖር ስለማልችል ፣ እሷ ሞታ በመቃብሯ ላይ ቆሜ እህህ እያሉ ቀን መግፋት ስለማይሆንልኝ ባቡሩ ድጦኝ እንዲያልፍ ፈቅጃለሁ።
ባቡሩ ቢቀርበኝና ህይወት አሳስታኝ ልትረፍ ብል እንኳን እራሴን ሆነ ብዬ ከሀዲዱ ጋር ተብትቤዋለሁ ለመፍታትም ባቡሩ ጊዜ አይሰጠኝም።
የባቡሩን ሀዲድ እና ትብታቡን አንቼ ቀና ስል.....
........ .......


የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል......
ፍሌም...

Creator ፦ @Maryam_2121

━━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃
861 views የፍቅ ታሪክ , 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 23:35:42 ​​​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ ⸙━━━━ ◈

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ ●•٠·˙

⚀ ክፍል ሀያ ⚀


.
ድሬ እውነተኛ ፍቅር እና መቻቻል የሚንፀባረቅባት ውብ ከተማ ነች። ሀገሬው ጭንቅ አይወድም። ጭንቀትም በአየሯ ላይ ቦታ የለውም በፈገግታና ፍቅር እየተባረረ ድንበሯን ጥሶ ይጠፋል።
ገና ከተማዋ ስገባ መንፈሱ የደስ ደስ ይሰጠኝ ጀምሯል።
ድሬ ፍቅር ፍቅር ትሸታለች።
.
ሁለት ሳምንታት ድሬን ዞርኩ ምንም ጠብ ያለ ነገር አላገኘውም። ወደ ጅማ መመለስ አልፈለግኩም።
ፍሌሜን አየዋት የሚለኝ ሰው አጣው።
ጀማ ሆኜ ሳስብ እንዲህም ተንከራትቼ የማጣት አልመሰለኝም ነበር። የበላት ጅብ አልጮህ ቢል ልቤ ቀቢፀ ተስፋውን ወደ መጥራቱ እያዘነበለ በነበረበት ሰሞን የሆነ ባለሱቅ ጋር ስለፍሌም ና ስለእኔ በደንብ አወጋን እሱም አሰብ አድርጎ ፍሌምን እንደሚያውቃት ነገር ግን ከቅርብ ወራት በፊት በድንገተኛ የመኪና አደጋ እንደሞተች እና እናትየው በህይወት እንዳሉ ነገረኝ።
ይህን ሲለኝ ሰማይ የተደፋብኝ ያህል ዞረብኝ የሰማውት ነገር ቅዠት እንጂ እውነት አልመስልህ አለኝ።
ግራ በተጋባ ስሜት ውስጥ ሆኜ ራሴን ጠላውት። ዛሬውኑ ድሬን ለቅቄ ለመሄድ ወሰንኩ። ግን ከዚህ ወዲህ ፍሌምን አጥቶ እንዴት ይኖራል? ዋ!!!
ግን ይሄ ሁላ እንዴት ሊሆን ቻለ?
ፍሌም እናቷ ካልሞቱ እንዴት ደክመዋል ተብሎ ሲቀጥልም ሞተዋል ብለው ጠሯት? ' እያልኩ ስብሰከሰክ ድሬ ከገባሁ ወዲህ የተዋወቅኩት አንድ ጫታም እየተንከወከወ መጥቶ የሆነ ሽማግሌ ጋ ወሰደኝ።
ሽማግሌው ወንድምየው ታሞበት እያስታመመ መሆኑን እና እውነተኛዋ እኔ የምፈልጋት ፍሌም እዚሁ ጊቢው ውስጥ እንዳለች ነግሮኝ ፍሌሜን ሊያሳየኝ ወደ ጊቢው ይዞኝ ገባ።
ፍሌም አለች የተባለችበት ሰርቢስ ውስጥ ነበር።
ስገባ ቤቱ ጭልምልም ብሏል። እሷን የሚመስሉ አሮጊት ሴትዮ ወደ አልጋው ትራስጌ ቆመዋል።
አልጋው ላይ ፍሌም ተኝታለች። ቀረብ ብዬ ተመለከትኳት።መልኳ ገርጥቷል።ፍሌሜን አሟታል፤,የድሮ መልኳ ተለውጧል።
ገና ስታየኝ እያቃሰተች ተጣጥራ አቀፈችኝ ፤ እምባዋን አዘራች።
አምርሬ አለቀስኩ ከፈጣሪዬም ጋር ተዋቀስኩ። በእጅጉ አለም እንደከዳችኝ ገባኝ።
ሳለቅስ ሽማግሌው የታመመ ወንድምየው እንዳይረበሽ ለቅሶዬን አስቁሞ ያፅናናኝ ገባ።
የማየው ነገር ሁሉ እውነት አልመስልህ አለኝ።
.... እንደዋዛ ከፍሌም ጋር ለሶስት ቀናት ቆየው። ከሚያስታምሟት እናቷ ጋር ሆነን የማይገፉ ሶስት ቀናትን የዘላለም ያህል እየከበደኝ ገፋሁት።
ፍሌሜም እኔ ፊት ደስተኛ ሆና ለመታየት ፈገግ ትላለች። ያ ውብ ዲንፕሏ ድምቀቱ ጠፍቶ የበርባሮስ ጉድጓድ መስሏል።



ክፍል ሀያ አንድ ይቀጥላል........

━━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃
917 views የፍቅ ታሪክ , 20:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 20:13:21 የቆራጥ ሰው እጣፋንታ

ቆራጥ መሆን ስትጀምርና ወደ ራስህ ስታተኩር ምድራዊ ጥያቄህ መመለስ ይጀምራል፤ እጣፋንታህ በሰዎች እጅ መሆኑ ያቆማል። ህይወትህን የሚቀይረው ከሰዎች በምታገኘው እርዳታ ወይ ትብብር አይደለም ወይ ሁኔታዎች በሚያመጡት ዕድል አይደለም!

ህይወትህ የሚቀየረው ቆራጥ በመሆንህ አምላክህ በሚያዘጋጀልህ ስጦታ ነው! ለዛ ነው መጠንከር ስትጀምር ሰዎች የሚያከብሩህ፣ ስራው ዕድሉ ገንዘቡ የፍቅር ግንኙነቱ ሁሉ የሚስተካከለው። ወዳጄ መጠንከር እንደጀመርክ አውቃለው ከዛ ግን ወደኋላ ማየት የለም!

ተአምረኛ ምሽት ተመኘንላችሁ
@Yfiker_ena_sak_bot
የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
979 viewsℤ𝕖𝕣𝕚𝕙𝕦𝕟, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 22:57:22 አንድ አንድ ሰዎች ለምን #ቢዚ እንደሆኑ ታውቃላችሁ ??
:
ቆይ አሁን #Busy ነኝ በኋላ ነግራችኋለሁ

𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 𝐒𝐇𝐄𝐑
@Maryam_2121
948 viewsℤ𝕖𝕣𝕚𝕙𝕦𝕟, 19:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 14:49:05 ኢትዮ ቴሌኮም ምናለበት የሚስት ብድር ቢጀምር
@Maryam_2121
ሁሌም የማታ ጥቅል እገዛ ነበር

#አንዱ_ሲል_ሰምቼው_ነው

𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 𝐒𝐇𝐄𝐑
@Yfiker_ena_sak_bot
961 viewsℤ𝕖𝕣𝕚𝕙𝕦𝕟, 11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 14:00:23 ​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ⸙━━━━ ◈

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ ●•٠·˙

⚀ ክፍል አስራ ዘጠኝ ⚀
.
.... ብላ ልትቀጥል ስትል እምባ ተናነቃት። አምቃ የያዘቸውን ለቅሶ አፈነዳችው። እየተንሰቀሰቀች ወጥታ ሄደች....
እናቴ ግራ ገባት። ልትቆጣኝ አልወደደችም። እንድደነግጥ አልፈለገችም።
"የእኔ ጌታ ትንሽ ምግብ አትበላም?"አለች አይኗን ቡዝዝ አድርጋ እየተመለከተችኝ። በግምባሯ ላይ የተጋደሙትን እጥፋቶች ስመለከት በትልልቅ ችግር ውስጥ አላሳልፍ ብሎ የተጋደመ ትልቅ ግንድ ያየው መሰለኝ።
በረጅሙ ተንፍሼ እመባዬን እያበስኩ "በቃኝ እማ!" አልኳት።
"ግሩም ልጄ ምነው አሳቀቅከን ምነው ስቃዬን በቃሽ ብትለኝ ?
እህትህንም ሰላም አልሰጣሃትም! ተሰቃየች እኮ ጌታዬ እኔስ ባማጥኩህ በወለድኩህ ልጎዳ እህትን ምነው ልጄ!?
የኔ ጌታ ፈተናህን ተወው ይቅር ግን አንዴ ብቻ ተጣጥበህ ልብስህን ለውጠህ ምግብ ብላልኝ! ልጄ ባጠባውህ ጡት ይዤሃለው እባክህ እባክህ!" አለች እናቴ እምባዋን እያዘራች።
የለበሰችው ቢጃማ በላይዋ ላይ አድፏል። ስለእኔ ማሰቡ ክስት አድርጓታል። የድሮ ወዟን አጥታ አመዷ ቡን ብሏል። ይባስ ብሎ አባቴ ከሶስት ወራት በፊት ለአንድ ወር ከወጣበት የመስክ ስራ ሲመለስ ሰርቦ በተባለች የጅማ አዋሳኝ ትንሽዬ ከተማ ውስጥ ህፃን ልጅ ገጭቶ ከታሰረ ወዲህ እናቴ እንቅልፍ የላትም ትርሃሴም እንደቆዘመች ትውላለች። ታድራለች። በቤታችን ሰማይ ስር መከራ ጥቁር ጥላውን አጥልቷብናል።
ይሄን ፈተና ተፈትኖ ፍሌሜን ድሬዳዋ ሄጄ ልፈልጋት አሰብኩኝ። ትርሃሴን እና እናቴን ደስ እንዲላቸው ጠዋት ወጥቼ ማታ እገባለሁ።
ሀደኮ መጥታ ታየኛለች ብቻዬን ስታየኝ ውሃውን ሳትቀዳ ተመልሳ ትገባለች። ከፍሌም ጋር ፀሀይን የምናጠልቅበት ከጀምበር መጥለቂያ ላይ አንዳንዴ እሄዳለሁ ግን ምን ያደርጋል። ትዝታ ብቻ። ህይወት ለዛዋ ጠፍቶ ቀለም አልባ ትሆንብኛለች።
የጎዳናው ዳር ፣ የሲኒማው ቤት ፣ የመናፈሻ እና የሬስቶራንቶች ደስታው እና ፌሽታው ልጆችዋን እንደተራበች ወፍ በረው ጠፍተዋል።

....... .......

እንደምንም አንድ ወሬን ባጅቼ ፈተናዬን አጠናቅቄ ወደ ድሬዳዋ ለመሄድ ተነሳሁ። ትርሃሴ አብሬህ ካልሄድኩ ብላ አስጨነቀችኝ በስንት ውትወታ አስቀረዋት። ከሶስት ቀናት በኃላ " የበረሃዋ ንግስት " ወደምትሰኘው ታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ድሬ ከተማ ገባሁ።
ድሬ እውነተኛ ፍቅር እና መቻቻል የሚንፀባረቅባት ውብ ከተማ ነች። ሀገሬው ጭንቅ አይወድም። ጭንቀትም በአየሯ ላይ ቦታ የለውም በፈገግታና ፍቅር እየተባረረ ድንበሯን ጥሶ ይጠፋል።
ገና ከተማዋ ስገባ መንፈሱ የደስ ደስ ይሰጠኝ ጀምሯል።
ድሬ ፍቅር ፍቅር ትሸታለች።......


ክፍል ሀያ ይቀጥላል........

━━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ ⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃
944 views የፍቅ ታሪክ , 11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 22:52:55 ​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ ⸙━━━━ ◈

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ ●•٠·˙

⚀ ክፍል አስራ ስምንት ⚀

ከወዲያኛው የስልኩ ጫፍ
"ግሩሜ በፍጥነት ቤት ና እፈልግሃለው " የሚል የፍሌሜን ድምፅ እንደሰማው ስልኩ ተዘጋ።
ግራ ገባኝ ተነስቼ ከነፍኩ።
የትርሃስ ስድብና ንጭንጭ እስክወጣ እየተከተለኝ ነበር።
➲➲➲➲➲➲➲➲➲➲➲
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተንጋልያለሁ ትርሃስ አልጋው ጫፍ ላይ ሆና ታፋዋ ላይ አስተኝታኝ ጣቶቿን በፀጉሬ ውስጥ ታርመሰምሳለች። ፍዝዝ ብላለች ትክዝ ብያለሁ
"ግሩሜ " አለች ቅዝቅዝ ባለ ድምፀት
ዝም አልኩ!
"ለምን እንዲህ ትሆናለህ የኔ ጌታ! እራስህን እየጎዳህ እኮ ነው ግሩሜ ቢያንስ እናታችንን አስባት እስኪ ምን ያህል እንደተጎሳቆለች። ፈተናህም አንድ ወር ነው የቀረው። በዛ ላይ ፍሌም ከሄደች ይኸው ድፍግ አምስት ወር ሆናት አይደል እንዴ!" አባታችንስ ከታሰረ ሶስት ወር ሆነው አይደል? እሷስ ብትሆን የእውነት ከወደደችህ እና ካፈቀረችህ እንዴት ይህን ያህል ጊዜ ትተውሃለች?!" አለችኝ። እምባ በአይኗ እየቀረረ ሳግ እየተናነቃት።
ትመጣለች! እናቷ ሞተው ታዲያ በዚህ ፍጥነት .....እምባ አነቀኝ።እልህ ጉሮሮዬን ፈጥርቆ ያዘው።ትኩስ እምባዬ ጉንጬን እንደሳማ እየለበለበኝ እርግፍ እርግፍ ሲል ይታወቀኛል።
ፍሌም ናፈቀችኝ በዛች የተረገመች ቀን ጠርታኝ እናቷ እንደደከሙ እና አሁኑኑ መሄድ እንዳለባት እየተርበተበተች የነገረችኝ ነገር ሁኔታው በአይነ ህሊናዬ ውልብ አለ።
ከሄደች ጀምሮ በሽተኛ ሆኛለሁ። አልጋ ላይ ሆኜ እምባዬ አለከልካይ በጉንጮቼ ሲንፎለፎል ትርሃስ ጭንቅላቴን ወርውራ ተነሳች።
"ቆይ አንተ ምንድነው ፍላጎትህ.."እኔ አላሳዝንህም ? እማዬ አታሳዝንህም ? ቅዱሴን እንኳን ተመልከተው ግሩሜ! እኔ እህትህ እኮ ደስታህን እፈልገዋለሁ ቆይ ከፍትህ አልጋ ላይ ስትውል የማይከፋኝ ይመስልሃል ? ምን ስሆን ማየት ነው የምትፈልገው?.."
"ምንድነው ምን ሆናችሁ ሚሚዬ "እናቴ ከውጭ ገባች።
እማ እኔ ግሩሜ በዚሁ እየቀጠለ የሚኖር ከሆነ ከእኔም ሆነ ከቅዱሴ ምንም ነገር አትጠብቂ እንደውም እኔ እህቱ አይደለሁም! እማ ተመልከቺው እስኪ ምግብ በስርዓቱ የበላው መች ነው? ይሄን ልብስ ከቀየረው ስንት ጊዜው ነው? እኔና አንቺን መች አይቶን ያውቃል? የታሰረ አባቱን ከጠየቀው ስንት ጊዜ ነው? እማ በእግዚአብሔር ጠይቂው ጨነቀኝ እንደድሮ አያናድደኝም ስድቤ አይናፍቀውም እማ የድሮው ግሩም ናፈቀኝ... !" ብላ ልትቀጥል ስትል እምባ ተናነቃት። አምቃ የያዘቸውን ለቅሶ አፈነዳችው። እየተንሰቀሰቀች ወጥታ ሄደች.....


ክፍል አስራ ዘጠኝ ይቀጥላል.......

━━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ ⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃
837 views የፍቅ ታሪክ , 19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 22:45:10 ​​​​​​◈ ━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ ⸙━━━━ ◈

⊶⊷⊶⊷❍ ፍሌም ❍⊶⊷⊶⊷

˙·٠•● ተከታታይ ልቦለድ ●•٠·˙

⚀ ክፍል አስራ ሰባት⚀




እማ ምነው ትርሃሴ ቆየች!? " አልኳት ቻርጀሩ መቀበል አለመቀበሉን እያረጋገጥኩ።
"አሁን ትመጣልህ የለ!" ብላኝ ሳትጨርስ
"እማ እንዴት ነሽልኝ እናቴ !" እያለች ገባች። ከመቅበጥበጧ የተነሳ የምትዘፍን ነበር የምትመስለው።
"ሚሚዬ እንዴት ዋልሽ ልጄ?"
"አለውልሽ ኡፍፍፍ ደክሞኛል እማ ውሃ ስጪኝ በማሪያም?"
"እሺ እሺ ወንድምሽን ሰላም አትዪውም እንዴ? ምነው ትርሃሴ?" አለች
ባክሽ እኔ የማንንም ሽንኩርታም ሰላም ስል ጊዜዬን አላቃጥልም! You know time is the gold"አለች በጎሪጥ እየተመለከተችኝ።
"ማንን ነው አንቺ? አይጥ!"አልኳት ኮስተር ለማለት እየታገልኩ።
"እኔ ግሩም ብዬ ጠርቼሃለው ሽንኩርታም!" አለች ጀነን እንዳለች።
ሚሚዬ እግዚአብሔርን ይሄን ሽንኩርት አበላሻለሁ! ጥጋብሽን ቀንሺ "አልኳት።
"ወንድ ነኻ ዝም ስልህ የፈራሁህ መሰለህ? አመዳም! ግምባራም! ሂሽ ሽንኩርታም!!" አለች።
ከምከትፈው ሽንኩርት ላይ በእጄ ዘግኜ ወስጄ ላበላት ታስታገል ጮኸች።
"ግሩሜ በእግዚአብሔር በእግዚአብሔር ግሩሜ የኔ ወንድም በእግዚአብሔር አዪዪዪ እማ ተው በይው እንጂ ኧረ በማሪያም እማ?!" አለች እየታገለችኝ
"አንቺ ማን ነገር ፈልጊው አለሽ እና ነው?" አለች እናቴ
"ኧረ እማ አበላኝ እኮ በእግዚአብሔር ቱ ምን አይነት ገገማ ነው በእግዚአብሔር " አለች ፊቷን ጭፍግግ አድርጋ ያበላዋትን ሽንኩርት እየተፋች
"አሁንም እንዳላበላሽ ዋ!"
"ሂድ ወደዛ ሽንኩርታም! ወንድ ነህ ግሩሜ አሁንማ"አለች ወደ እናቴ እየርጠች። እናቴን መሃል አድርገን ተያየን።
"ምነው ጌታዬ ብትተዉ ሽንኩርቱንም በትናችሁ ጨረሳችሁት እኮ አዬ ልጅነት"አለች ወደ እኔ ዞራ።
"አንቺም እረፊ ተሞጣሙጠሽ ስታበቂ እኔን አትጥሪኝ ደቃቃ" አለቻት በፍቅር ቁጣ
"እማ ግን ሁል ጊዜ እኔ ላይ ነው አይደል የምትጮሂው? እንዴ......" ትርሃስ እየተነጫነጨች ስልኬ ጮኸ።አነሳሁት።
"አቤት ፍሌሜ!" አልኩኝ
ከወዲያኛው የስልኩ ጫፍ
"ግሩሜ በፍጥነት ቤት ና እፈልግሃለው " የሚል የፍሌሜን ድምፅ እንደሰማው ስልኩ ተዘጋ።
ግራ ገባኝ ተነስቼ ከነፍኩ።
የትርሃስ ስድብና ንጭንጭ እስክወጣ እየተከተለኝ ነበር።


ክፍል አስራ ስምንት ይቀጥላል........

━━━━⸙ ፍቅር እና ሳቅ⸙━━━━
▃▅▆██▆▅▃▃▅▆██▆▅▃
804 views የፍቅ ታሪክ , 19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ