2022-08-29 18:52:25
ህጻናትን ከትምህርት ቤት ወደ ጦርነት የትህነግ ሌላኛው ክፋት ሲጋለጥ
አልሸባብ በሶማሊያ ጎዳናዎች ላይ ህፃናትን ፈንጂ አስታጥቆ በማሰማራት ጥፋት እንደሚያደርስ ሁሉ የትህነግ የሽብር ብድንም እድሜያቸው ከ15-19 ያሉ ታዳጊዎችን በመመልመል ወደ ጦርነት እየማገዳቸው ይገኛል።
አሸባሪው ትህነግ እድሜያቸው ከ15-19 የሆኑ ታዳጊዎችን ደብተርና እስኪቢርቷቸውን አስጥሎ ክላሽ በማስታጠቅ ወደ ጦርነት እሳት እየማገዳቸው ይገኛል።
ለአሸባሪው ትህነግ ዓለማ ለጥቂት ሰዎች የግል ስልጣንና ጥቅም ብቻ ሲባል ህጻናት ትምህርታቸውን አቋርጠው ጫካ ገብተው እንዲያልቁ ተፈርዶባቸዋል፡፡
ህፃናትን ለጦርነት መመልመል በአለም አቀፍ ህግ እና በኢትዮጵያ ህግ ከፍተኛ ወንጀል ነው፡፡ እናም ድርጊቱ ከሞራል ብቻ ሳይሆን ከሕግም አኳያ ይታያል፡፡ ህጻናት ለወታደርነት መልምሎ ስልጠና መስጠት እና መጠቀም የተባበሩት መንግስታት ስምምነትን እንደ መጣስ እና እንደ የጦር ወንጀል ይቆጠራል፡፡ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በጦርነት ውስጥ ምንም አይነት ተሳትፎ እንደማይኖራቸው በአለም አቀፍ ህግ በግልጽ ተደንግጓል።
አትዮጵያ ባፀደቀችው የአለም አቀፍ ህጎች ውስጥ ህፃናትን ለጦርነት መጠቀም ፤የጦር፤ መሳሪያ ማስታጠቅ እና ለጦርነት መመልመል የተመለከቱ የህግ ማህቀፎች መካከል African charter on the rights and welfare of the child አንቀፅ 22 ንዑስ (2)፤- ማንኛውም ልጅ በጦርነት ውስጥ በቀጥታ ማሳተፍ የለበትም፡፡ ንዑስ ( 3 )፤ በግጭቶች ውስጥ በተለየ መልኩ ለህፃናት ጥበቃ ያስፈልጋል ይላል፡፡ The convention of right of child (UNCRC) አንቀፅ 38 ንዑስ (2 )፤ 15 አመት ያልሞላቸውን በጦርነት ተሳትፎ መከልከል፤ ንዑስ( 3) ፤ 15 አመት ያልሞላቸውን ወደ ጦር ሃይል ከመቅጠር መቆጠብ እንደሚገባ ያትታል፡፡
እነዚህ የጸደቁ ስምምነቶች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ13 (2) እና 9 (4) መሰረት የሀገሪቱ ሕግ አካል በመሆናቸው መንግስት እና ሌሎች አካላት የሕገ መንግስቱን እና የስምምነቶችን ድንጋጌዎች ከማስፈጸም አኳያ አስተዋጽኦ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
የሀገራችንም የተለያዩ ሕጎች የህፃናትን በጦርነት ማሳተፍ እንደሚያስጠይቅ ደንግገዋል፡፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጦር መሳሪያ አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ 1177/2012ዓ.ም አንቀ 4 የጦር መሳሪያ ከተፈቀደለት ሰው /አካል ውጪ የጦር መሳሪያ እንዲይዝ ያሰለጠነ በወንጀል ያስጠይቃል፤ እንዲሁም በአንቀፅ 8 ንዑስ 1 መሰረት የመሳሪያ ተጠቃሚውን ልዩ ሁኔታ ሳያገናዝብ የጦር መሣሪያውን ያስታጠቀ በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 22 ነዑስ 11 ላይ የህግ ሰውነት ባላቸው ቡድን ወይም ተቋም ከሆነ በወንጀል ተጠያቂ ያደርጋል፡፡
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገመንግስት አንቀጽ 36 ላይ የሕጻናት መብትን አስመልክቶ የተቀመጠ ግንጋጌ ይገኛል፡፡ ይህ ድንጋጌ ማንኛውም ሕጻን ጉልበቱን ከሚበዘብዙ ልማዶች የመጠበቅ፣ በትምህርቱ፣ በጤናው እና በደህንነቱ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሥራዎች እንዲሰራ ያለመገደድ ወይም ከመሥራት የመጠበቅ መብት እንዳለው አስቀምጧል፡፡ ሕጻናትን የሚመለከቱ እርምጃዎች በሚወሰዱበት ጊዜም የሕጻናት ደህንነት በቀደምትነት መታሰብ እንዳለበት አጽንኦት ይሰጣል፡፡
በ1996 ዓ.ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 270/ኀ/ መሰረት ማንም ሰው በጦርነት ግጭት ወይም በጠላት ወረራ ጊዜ የዓለምአቀፍ ሕግ ድንጋጌዎችን እና የዓለምአቀፍ የሰብአዊነት ሕግጋትን በመጣስ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ጉዳት ለማድረስ በማደራጀት፣በማዘዝ ወይም ድርጊቱን በመፈጸም ወይ ምበማናቸውም ሌላ መንገድ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ልጆችን በጦርነት ውስጥ እንዲሳተፉ ለማድረግ ለወታደራዊ አገልግሎት አባልነት የመለመለ እንደሆነከ 5 ዓመት እስከ 25 ዓመት ለመድረስ በሚችል ጽኑ እስራት ወይም ነገሩ በጣም ከባድ በሆነ ጊዜ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ወይም በሞት ሊያስቀጣ የሚችል መሆኑ ተደንግጎ እናገኘዋለን፡፡
የትህነግ የሽብር ብድን የዓለም አቀፍና የሀገሪቱን ህጎች በጣሰ መልኩ እድሜያቸው ከ18 በታች የሆኑ ህጻናትን ለጦርነት እየተጠቀመ እንደሆነ በግልጽ ታውቋል:: ይህ ጉዳይ ለትውልድ ተቆርቋሪ ነኝ የሚል ሁሉም በደረጃ ካላወገዘና ለህግ ተጠያቂ ካለደረገ እየተባባሰ መምጣቱ አይቀርም ኢ-ህገመንግስታዊ በመሆኑ ‹‹ሳይቃጠል በቅጠል›› ሊባል ይገባል፡፡
#አዲስ መረጃ
1.6K viewsSamuel Belete(bama), 15:52