Get Mystery Box with random crypto!

Yegof tender

የቴሌግራም ቻናል አርማ yegoftender — Yegof tender Y
የቴሌግራም ቻናል አርማ yegoftender — Yegof tender
የሰርጥ አድራሻ: @yegoftender
ምድቦች: ንግድ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 313
የሰርጥ መግለጫ

Yegof solution is an innovative channel strive to deliver information but not limited to tender notice. visit https://yegof.com

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-03-11 11:40:24 The Benishangul Gumuz Regional Health Bureau intends to award a work contract for Different Projects

Bid closing date: Tender closing date shall be 30 calendar days after the date of notice published. If the closing date is on the public holiday (non-working days), the closing date will be the next working day at 02:00 pm or 8:00 local time

Bid opening date: Same day with closing date at 02:30 pm or 8:30 local time.

Published on: Ethiopian Herald (Mar 09, 2023)

Bid document price: 300 ETB for each lot.

Bid bond: 10,000 to 330,000.00 (from one hundred thousand birr to three hundred thirty thousand Birr) for each lot

Click Here For More Information
203 viewsedited  08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 11:39:00 የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ህዳሴ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎች እና አገልግሎቶችን መግዛት ይፈልጋል

Bid closing date ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በዛው ዕለት ከቀኑ 11፡00 ሰዓት

Bid opening date: በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት

Published on: አዲስ ዘመን (Mar 09, 2023)

Bid document price100.00 ብር

Bid bond: የጨረታው ማስከበሪያ ብር መጠን በየሎቱ የተለያየ ነው

Click Here For More Information
179 viewsedited  08:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-11 11:36:01 የአማራ ብሔ/ክ/መ/የሰ/ሸዋ/ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገንዘብ/ፅ/ቤት ግ/ን/አሰ/ቡድን ለተለያዩ ሴ/መስሪያ ቤቶች የተለያዩ ደንብ ልብስ እና የአፄ ውሃ ዘመናዊ የመስኖ ካናል ግንባታ ለ2015 ዓ.ም. ለመግዛት እና ለማስገንባት ይፈልጋል

Bid closing date: የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን የተለያየ ነው

Bid opening date: የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን የተለያየ ነው

Published on: አዲስ ዘመን (Mar 09, 2023)

Bid document price: 50.00 ብር

Bid bond: የጨረታው ማስከበሪያ ብር መጠን በየሎቱ የተለያየ ነው

Click Here For More Information
166 viewsedited  08:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 21:30:39 African Leadership Excellence Academy (AFLEX) invites eligible bidders to participate only by forming a consortium (joint venture) with an international firm of proven experience and similar category that holds a valid trade license, and is in good standing with regards to its registration in the country of its practice

Bid closing date:No Specific Closing Date and Time

Bid opening date No Specific Opening Date and Time

Published on: Ethiopian Herald (Mar 09, 2023)

Bid document price

Bid bond:

Region: Addis Ababa

For More Information https://yegof.com/blog/2023/03/10/african-leadership-excellence-academy-aflex-invites-eligible-bidders-to-participate-only-by-forming-a-consortium-joint-venture-with-an-international-firm-of-proven-experience-and-similar-category/
272 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 19:43:50 በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን በቀወት ወረዳ የገ/ጽ/ቤት ለቀወት ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ጋቢዮን ጋልቫናይዝድ የሆነ (የፋብሪካ ምርት) ፣ በጉንፋታ ወንዝ የመስኖ ግንባታ ጥገና ፣ የስፖርት ትጥቅ እንዲሁም የማሽን ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Bid closing date: የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው

Bid opening date: የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት በየሎቱ የተለያየ ነው

Published on: አዲስ ዘመን (Mar 08, 2023)

Bid document price የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር በየሎቱ የተለያየ ነው

Bid bond: የጨረታ ማስከበሪያ ብር በየሎቱ የተለያየ ነው

Region: Amhara

For More Information
Click Here
273 viewsedited  16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 15:11:32 በሲዳማ ብ/ክ/መንግሥት የወንዶ ገነት ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት ጩኮ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ ሊያሠራ ላቀደው የሣይት ግሪነር ሥራ ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል

Bid closing date: ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን ከቀኑ 6:00

Bid opening date: 22ኛው ቀን ከቀኑ 8:00

Published on: አዲስ ዘመን (Mar 08, 2023)

Bid document price 400 ETB

Bid bond: 50,000.00 ETB for each lot

Region: Sidama

For More Information Click Here
279 views12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-10 15:07:26 በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ለመሸጥ ይፈልጋል

Bid closing date: በየሎቱ የተለያየ ነው

Bid opening date: በየሎቱ የተለያየ ነው

Published on: አዲስ ዘመን (Mar 08, 2023)

Bid document price 100 ETB

Bid bond: 5%

Region: Dire Dawa

For More Information Click Here
250 views12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 15:07:14 በጉምሩክ ኮሚሽን ሞጆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

የተተው እቃዎች ግልጽ ጨረታ ቁጥር ግ37/2015 ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎችን በጉምሩክ አዋጅ 859/2006 አንቀፅ 51 ፣ ንዑስ አንቀፅ 1 እና በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት ዕቃቸውን የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው ተቆጥረዋል።

ስለሆነም በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ያሉ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በአወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም

ሶፋ ማቴርያል ፣
ፌርሙዝ ፣
የቡና መፍጫ ማሽን ፣
ማስክ ፣
ከፕላስቲክ የተሰሩ የእቃ መያዣ ፣
ካርቶን ኬሚካል ፣
የላሜራ ጥቅል ብረት ፣
የቡና መፍጫ ማሽን ፣
የተለያዩ የሻወር ቤት ዕቃዎች ፣
ብረታ ብረት ማሽን ፣
ባጃጅ ፣
የግንባታ ዕቃ እና
ባትሪና የእቃ መያዣ (BATTERY AND RACK) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር ፣ ዓይነት ፣ ብዛት ፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡30 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው። ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የ15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ማስከበሪያ አሸናፊው ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል። ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን የጨረታ እንደታወቀ በ3 (ሶስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከአሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብላቸው ይሆናል። ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCHOFFICE በሚል ሲሆን የግል ባንክ ከሆነ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ቅርጫፎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሆነ ደግሞ ከአዲስ አበባ ፣ አዳማና ሞጆ ቅርጫፎች መዘጋጀት አለበት። ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተዘጋጅተው ማህተም ያረፈበት ሠነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አስቀድሞ ማየት ያለባቸው ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
የግልፅ ጨረታ ተሳታፊ ተጫራቾች እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ ፣ የሞሉበት ሠነድ ፣ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት ጠዋት 4:45 ድረስ በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል።
የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጨምሮ በ8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:45 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ጠዋቱ 5፡00 ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።
ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም።
ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ጨረታውን ለማሸነፍ ሲል መደለያ የሰጠ ወይም ለመስጠት የሞከረ ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ይወገዳል፡፡ ጨረታው ከተካሄደ በኋላም ቢሆን ጨረታ አሸናፊው ጨረታውን ያሸነፈው በህገ-ወጥ መንገድ መሆኑ ከተረጋገጠ የጨረታው ውጤት ይሰረዛል።
ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም።
ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም።
ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5(አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት። 05 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል። ያሸነፉት ዕቃም በድጋሚ ለጨረታ ሽያጭ ይቀርባል።
በተራ ቁጥር 12 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል። ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ይሸፍናል።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው።
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-9094 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

Telegram channel
t.me/yegofbusines
235 viewsedited  12:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 15:06:39 የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 3//2015

የኦሮሚያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለ2015 የበጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ላፕቶፕ ኮምፒዉተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት1፡-ላፕቶፕ ኮምፒውተር መግዛት

በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
ተጫራቾች በዘርፉ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ የግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቲን(TIN) እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ(BID BOND) ለሎት1 ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) ከጨረታ መወዳደሪያ ኦሪጅናል ሰነድ ጋር በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ብቻ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል ከግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የመዝጊያ ቀን ከ4 ሰዓት በፊት ቀድመው ሰነዱን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የጨረታው አሸናፊ እቃውን በ10 ቀን ውስጥ ማቅረብ አለበት።
የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት አድራሻ፡-አዳማ ወንጂ መንገድ የኦሮሚያ አዳሪ ት/ቤት ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡-022 212 3599 /0911 65 97 49 / 0911 17 88 98 መደወል ይቻላል።

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ

Telegram channel
t.me/yegofbusines
177 viewsedited  12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 15:06:02 የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ቁጥር 11 እና ሃራጅ ቁጥር 11/2015

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ተወርሰው የሚገኙ

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
አዳዲስ አልባሳት፣
ሸቀጣሸቀጥ፣
ኮስሞቲክስ፣
የተለያዩ የቢራ፣ የለስላሳ ጠርሙሶች እና ሳጥኖች፣
2 ሞተር ሳይክሎች እና አንድ ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ እንዲሁም
መጠጥ ነክ፣
ሸቀጣሸቀጥ፤
ብዛት ያለው ኔትዎርክ ኬብል እና
የተሽከርካሪ መለዋወጫ በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም:

በአዳማ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት እና ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት ቀን ማቅረብ ይኖርበታል።
በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ5oo ሺህ ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሰው መስፈርቶች ቢኖርም ሞተር ሳይክል ላይ ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የቀበሌ መታወቂያ በመያዝ ያለ ቅድመ ሁኔታ ጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል።
የግልጽ እና የሃራጅ ጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እiከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት ኢማ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሂሳብና ዋስትናዎች አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመግዛት በጨረታ የወጡትን ዕቃዎችን ማየት የሚትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ ለዕቃዎቹ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ማለትም ለምድብ 1 መጠጥ ነክ ብር 40,000፤ ለምድብ 2 ኔትዎርክ ኬብል ብር 640,000 ለምድብ 3 ተሽከርካሪ መለዋወጫ ብር 4,000 እና ለምድብ 4 ሽቀጣሽቀጥ ብር 800 ከባንክ በተመሰከረለት (CPO) Customs Commission Adama Branch Office ስም በማሰራት ለግልፅ ጨረታ በተራ ቁጥር ላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች ጋር በማያያዝ እንድታስገቡ እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት እለት ይዛቸው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
በጨረታ ሽያጭ የእቃው አስመጪ ወይም ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
በግልጽ ጨረታ ለሽያጭ ለቀረቡት እቃዎች የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት የቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሃደት ቢሮ ቁጥር 21 ድረስ በመሄድ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPO፣ የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር 1 ላይ ከተጠቀሱት ሌሎች ሰነዶች ጋር በፖስታ በማሸግ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
በጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አማ ግቢ መጋዘን ጥር 5 ፤ መጋዘን ቁጥር 10 (ሜዳ ላይ) እና እንዲሁም በዳቱ ቀበሌ 07 በሚ?ኘው በቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን ቁጥር 2 ስለሚገኙ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግልፅ ጨረታ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ ሳጥኑ በስምንተኛው ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጐ በ4፡15 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን፤ ነገር ግን ስምንተኛው ቀን በበዓል ወይም እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። ለሃራጅ ጨረታ በአዲስ ዘን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን፤ ስድስተኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚካሄድ ይሆናል።
የግልጽ ጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቦታ ቅ/ጽ/ቤቱ በሚገኝበት በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አማ ግቢ በሚገኘው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል ሆኖም ተጫራቾች ካልቀረቡ ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል።
አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶሰት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሽነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
ለጨረታ የቀረቡት kቃዎች ሸያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
ከላይ በተ/ቁ 11 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።
ማንኛውም ተጫራች 100 ብር ሰነድ የዛበትን ደረሰኝ ለግልፅ ጨረታ ከሌሎች ሰነዶች ጋር አያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን፤ ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ከሌሎች ሰነዶች ጋር ይዞ መገኘት አለበት።
ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች- 022-111-8429 እና 022-211-8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

Telegram channel
t.me/yegofbusines
145 viewsedited  12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ