Get Mystery Box with random crypto!

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 3//2015 የኦሮሚያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለ2015 የበጀት አ | Yegof tender

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 3//2015

የኦሮሚያ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ለ2015 የበጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ላፕቶፕ ኮምፒዉተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ሎት1፡-ላፕቶፕ ኮምፒውተር መግዛት

በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሉ አቅራቢዎች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል።

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
ተጫራቾች በዘርፉ መወዳደር የሚያስችል የታደሰ የግድ ፍቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቲን(TIN) እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ(BID BOND) ለሎት1 ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) ከጨረታ መወዳደሪያ ኦሪጅናል ሰነድ ጋር በባንክ በተመሰከረለት (CPO) ብቻ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል ከግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 መውሰድ ይችላሉ።
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለጸው የመዝጊያ ቀን ከ4 ሰዓት በፊት ቀድመው ሰነዱን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
ኤጀንሲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የጨረታው አሸናፊ እቃውን በ10 ቀን ውስጥ ማቅረብ አለበት።
የጨረታ ሰነዱ የሚገኝበት አድራሻ፡-አዳማ ወንጂ መንገድ የኦሮሚያ አዳሪ ት/ቤት ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡-022 212 3599 /0911 65 97 49 / 0911 17 88 98 መደወል ይቻላል።

በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኦሮሚያ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ

Telegram channel
t.me/yegofbusines