Get Mystery Box with random crypto!

የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ቁጥር 11 እና ሃራጅ ቁጥር 11/2015 በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ | Yegof tender

የጨረታ ማስታወቂያ ግልፅ ቁጥር 11 እና ሃራጅ ቁጥር 11/2015

በአዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ተወርሰው የሚገኙ

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
አዳዲስ አልባሳት፣
ሸቀጣሸቀጥ፣
ኮስሞቲክስ፣
የተለያዩ የቢራ፣ የለስላሳ ጠርሙሶች እና ሳጥኖች፣
2 ሞተር ሳይክሎች እና አንድ ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ እንዲሁም
መጠጥ ነክ፣
ሸቀጣሸቀጥ፤
ብዛት ያለው ኔትዎርክ ኬብል እና
የተሽከርካሪ መለዋወጫ በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም:

በአዳማ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፣ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት እና ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት ቀን ማቅረብ ይኖርበታል።
በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ5oo ሺህ ብር በታች የሆኑ ዕቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።
በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሰው መስፈርቶች ቢኖርም ሞተር ሳይክል ላይ ማንኛውም እድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የቀበሌ መታወቂያ በመያዝ ያለ ቅድመ ሁኔታ ጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል።
የግልጽ እና የሃራጅ ጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እiከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት ኢማ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤቱ የገቢ ሂሳብና ዋስትናዎች አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመግዛት በጨረታ የወጡትን ዕቃዎችን ማየት የሚትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
በግልጽ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ምድብ ለዕቃዎቹ የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ማለትም ለምድብ 1 መጠጥ ነክ ብር 40,000፤ ለምድብ 2 ኔትዎርክ ኬብል ብር 640,000 ለምድብ 3 ተሽከርካሪ መለዋወጫ ብር 4,000 እና ለምድብ 4 ሽቀጣሽቀጥ ብር 800 ከባንክ በተመሰከረለት (CPO) Customs Commission Adama Branch Office ስም በማሰራት ለግልፅ ጨረታ በተራ ቁጥር ላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች ጋር በማያያዝ እንድታስገቡ እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት እለት ይዛቸው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
በጨረታ ሽያጭ የእቃው አስመጪ ወይም ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።
በግልጽ ጨረታ ለሽያጭ ለቀረቡት እቃዎች የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት የቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን አስተዳደር የስራ ሃደት ቢሮ ቁጥር 21 ድረስ በመሄድ በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልገውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት CPO፣ የጨረታ ሰነዱን እና በተራ ቁጥር 1 ላይ ከተጠቀሱት ሌሎች ሰነዶች ጋር በፖስታ በማሸግ ሳጥኑ ከመዘጋቱ በፊት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
በጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አማ ግቢ መጋዘን ጥር 5 ፤ መጋዘን ቁጥር 10 (ሜዳ ላይ) እና እንዲሁም በዳቱ ቀበሌ 07 በሚ?ኘው በቅ/ጽ/ቤቱ የውርስ መጋዘን ቁጥር 2 ስለሚገኙ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለግልፅ ጨረታ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ ሳጥኑ በስምንተኛው ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጐ በ4፡15 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን፤ ነገር ግን ስምንተኛው ቀን በበዓል ወይም እሁድ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። ለሃራጅ ጨረታ በአዲስ ዘን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በስድስተኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን፤ ስድስተኛው ቀን በዓል ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚካሄድ ይሆናል።
የግልጽ ጨረታ ሳጥኑ የሚከፈትበት ቦታ ቅ/ጽ/ቤቱ በሚገኝበት በአዳማ ከተማ በከልቻ ትራንስፖርት አማ ግቢ በሚገኘው የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል ሆኖም ተጫራቾች ካልቀረቡ ታዛቢዎች ባሉበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል።
አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶሰት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሽነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።
ለጨረታ የቀረቡት kቃዎች ሸያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።
ከላይ በተ/ቁ 11 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሜ ለሽያጭ ይቀርባል።
ማንኛውም ተጫራች 100 ብር ሰነድ የዛበትን ደረሰኝ ለግልፅ ጨረታ ከሌሎች ሰነዶች ጋር አያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ያለበት ሲሆን፤ ለሃራጅ ጨረታ ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ከሌሎች ሰነዶች ጋር ይዞ መገኘት አለበት።
ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች- 022-111-8429 እና 022-211-8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

አዳማ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

Telegram channel
t.me/yegofbusines