2023-03-08 15:04:39
የሙያ ስራ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ጎንደር ዞን በነፋስ መዉጫ ከተማ የሚገኘው የልደት ኃ/የተወሠነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ዩኒዬን ለታች ጋይንት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል ባለ ሦስተኛ ፎቅ (G+3) በመደበኛ በጀት ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም በተጫራቹ በኩል የሙያ እና የጉልበት ስራ የሚቀርቡ ሲሆን ሌሎቹ በድርጅቱ በኩል የሚቀርቡ መሆኑን እያሳሰበ ለበለጠ መረጃ በተጫራቾች መመሪያ ገጽ 7 ላይ እንዲመለከቱ እያሳሰበ የእጅ (የጉልበት)እና የሙያ ስራ ግዥ ለጠቅላላ ስራ ተቋራጭ (G.C) ከደረጃ 6 እና በላይ ለህነፃ ስራ ተቋራጭ (B.C) ከደረጃ 5 እና በላይ ከሆኑ ህጋዊ ተወዳዳሪዎች መካከል በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
አቅራቢዎች ህጋዊና በዘመኑ የታደሠ የንግድ /የስራ/ ፈቃድ እንዲሁም ከመንግስት የሚጠበቅባቸውን የዘመኑን ግብር
የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የወጣው ጨረታ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ዋጋ እንደሚሆን ሲገመት የተጨማሪም የእሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
የጨረታ ማስከበሪያ 2 በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመጫረቻ ሰነድ በአማረኛ ቋንቋ መዘጋጀት ይኖርባቸል።
ተጫራቾች በሚሞሉት የመወዳደሪያ ሃሳብ ስማቸውን ፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል።
የጨረታ ሰነዱ በነፋስ መዉጫ ከተማ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ለ10 ተከታታይ ቀናት የመጨረሻ ሠነዱን ዋናው ጽ/ቤት ድረስ በመምጣት በአካል /ህጋዊ ወኪላቸው በኩል መግዛት ይችላሉ።
የጨረታ መዝጊያው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
የጨረታው ሰነዱ በሁለት ኢንቨሎፕ /ፖስታ/ አንድ ወጥ የሆኑ ዋጋ ዋና እና ቅጅ በሰም ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
የቅጅዎቹ ብዛት ሠነዶቹ ሥልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸውና ማህተም ሊኖራቸው ይገባል።
የመጫረቻ ሰነዱን ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን 11 ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
የመጫረቻ ሰነዱ በ11ኛው ከቀኑ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎች/ በተገኙበት /ባይገኙም / ይከፈታል።
1 ዩኒዬኑ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የአከፋፈሉ ሁኔታን በተመለከተ በተጫራቾች መመሪያ ይመልከቱት።
የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ 7 ገፅ የተጫራቾች መመሪያ መያያዙን ያረጋግጡ።
ተጫራቾች አሪጅናሉን በ1 ፖስታ በማሸግ ፣ ኮፒዉን በ 1 ፖስታ በማሸግ ፣ ሲፒኦዉን በ1 ፖስታ በማሸግ እና 3 ቱንም ፖስታዎች በአንድ ላይ በሌላ ፖስታ ዉስጥ በማድረግ እና በማሸግ ጨረታ ሳጥን ዉሰጥ ማስገባት ግዴታ ነዉ።
ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዬችን በስልክ ቁጥር 058 445 0048 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የልደት ኃ/የተወሠነ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኅብረት ሥራ ዩኒዬን
Telegram channel
t.me/yegofbusines
132 viewsedited 12:04