2022-07-28 09:56:18
#ጌታ_ሆይ_አንተ_ማን_ነህ?
#ጳውሎስ ከዚህ ቀደም የክርስቲያኖች ጠላት እና አሳዳጅ ነበር።
(ር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስ)
#ጳውሎስ_በንጉሱ_ፊት_መሰከረ:
#ጳውሎስ ከዚህ ቀደም የክርስቲያኖች ጠላት እና አሳዳጅ ነበር። አሁን ግን በአጭሩ በክርስቶስ ላይ ያለው እምነት በሚፈተንበት ሁኔታ ላይ ነው። ከ25 ዓመታት በሗላ ሐዋርያው ከክርስቶስ ጋር መገናኘቱን እንደጥሩ አጋጣሚ ይቆጥረዋል።
ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ሲገድል እንደነበር ይናራል፣ አንድ ቀን ይህንኑ ለማድረግ ወደ ደማስቆ እየሄደ እስካለበት ጊዜ ድረስ። በዚያን ቀን ከጸሀይ የደመቀ ብርሃን በእርሱ እና በአጋሮቹ ላይ በራ (ሐዋ 26፡13) እርሱ ብቻ ግን “ድምፅ” ሰማ፤ የክርስቶስን ድምፅ እርሱን በስሙ ጠርቶ ሲያናግረው ሰማ።
#ሳውል!_ሳውል!
በማስተዋል ይህንን ክስተት እናጢነው፤ ጌታ ሳውልን በስሙ በመጥራት እሱን በደንብ እንደሚያውቀው እንዲገነዘብ ያደርገዋል። ማን እንደሆንህ እና ምን ልታደርግ እንደሆነም ሳይቀር አውቃለሁ በቀጥታም እያናገረው ይሄንን ይለዋል። ጌታም ሁለት ጊዜ ጳውሎስ በሚል በልዩ ሁኔታ ጥሪውን በሚያመለክት ስም ልክ ከዚህ ቀደም ከሙሴ ጋር (ዘጸ 3:4) ከሳሙኤል ጋር (1ሳሙ 3:10) እንዳደረገው ጠርቶታል። ይህም ግልጠት ወደ ግራ መጋባት ውስጥ ከቶታል፤ እንዲያበቃለት ግን አላደረገም። ይልቁንም ራሱን በሌላ ስም ሲጠራ እንዲያገኝ አደረገው እንጂ።
በግል ዝምድና በሆነ መተዋወቅ በሆነ መልኩ ከክርስቶስ ጋር ስንገናኝ ብቻ ህይወት ይቀየራል። ኢየሱስም ጳውሎስን በደንብ እንደሚያውቀው በውስጥም በውጪም አሳይቶታል። ምንም እንኳን ጳውሎስ አሳዳጅ ቢሆንም ልቡም ለክርስቲያኖች ባለው ጥላቻ የተሞላ ቢሆንም ኢየሱስ ይሄ ካለማወቅ የመጣ መሆኑን ተረድቷል። ምህረቱን ሊያደርግለት እና በእርሱም ላይ ሊያሳድር ፈልጓል። ይህ እንዲሁ ሊገኝ የማይችል እና ከሌላ ምንም ሳይጠብቅ የሚሰጥ የፍቅር ትሩፋት ለሳውል ሕይወት መሰረታዊ የለውጥ ብርሃን ሆኗል።
#ጌ_ ሆይ_አንተ_ማን_ነህ?
ከዚህ ምስጢራዊ ግንኙነት እና የስሙ መጠራት ተከትሎ ጳውሎስ “ጌታ ሆን አንተ ማን ነህ?” (ሐዋ 16:15) ሲል ጠየቀ። ይህ ጥያቄ ወሳኝ የሆነና ሁላችንም ራሳችንን ልንጠይቀው የሚገባን ጥያቄ ነው። ሌሎች ሰዎች ስለ ኢየሱስ ሲያወሩ መስማት ለብቻው በቂ አይደለም፤ እርሱን ጠለቅ ባለ መልኩ እራሳችን ልናወራው ይገባል። ይህ ነው እንግዲህ ጸሎት ማለት። ጸሎት በቀጥታ ከኢየሱስ ጋር ማውራት ነው። ምንም እንኳ ልቦቻችን ግራ የተጋቡ ቢሆንም አዕምሮአችን በጥርጣሬዎች የተሞላ ቢሆንም ክርስቶስን እና ቤተክርስቲያኑንም የምንንቅ ብንሆንም እንኳ ሁሉም ወጣት በልቡ ይሄንን ጥያቄ ለራሱ መጠየቅ ይችል ዘንድ ጸሎቴ ነው። “ጌታ ሆይ አንተ ማን ነህ?”
መቼም ሁሉም ሰው ኢየሱስን ያውቀዋል ብለን መደምደም አንችልም። በዚህ በኢንተርኔት ዘመን እንኳ ብዙ ሰዎች ኢየሱስን እና ቤተክርስቲያኑን የሚጠይቁት ተመሳሳይ ጥያቄ ነው “አንተ ማን ነህ?” (ኢየሱስን)። በአጠቃላይ በዚህ ታሪክ ላይ ጳውሎስ ብቸኛ የተናገረባት ቦታ ይህች ብቻ ናት። ጌታም ወዲያውኑ “እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ” ሲል መልሶለታል።
“እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ።”
በዚህ መልኩ ኢየሱስ ለሳውል ትልቅ ምስጢር ገልጦለታል። እርሱም ይህ ነው ራሱን ከቤተክርስቲያን እና ከክርስቲያኖች ጋር አንድ አድርጎ እንደሚያሳድድ ነው። እስከዛ ድረስም ጳውሎስ የሚያሳድዳቸውን ክርስቲያኖች እንጂ (ሐዋ 26:10) ኢየሱስን አላየም ነበር። ክርስቲያኖች ለክፉ እንዴት መልስ ይመልሱ እንደነበር፣ ፍትህ በተጓደለበት ጊዜ እንኳ በሰከነ መልኩ ለጥላቻ ፍቅርን ይመልሱ እንደነበር አይቷል። ባያውቀውም በዚህ አይነት መልኩ ሳውል ክርስቶስን አግኝቶት ነበር፤ ያየውም በክርስቲያኖች ውስጥ ነበር።
ከጌታ ጋር መጋጨት (መማታት) ይጎዳል።
ጳውሎስ ከወደቀ በሗላ በእነዚህ ቃላት ጌታ ለተወሰነ ጊዜ በምስጢር እንዲህ ብሎታል . . . . . . .
#ይቀጥላል።።።።
ለተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አስተምህሮዎችን ለማግኘት ታች ያላውን ሊንክ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑን፡፡
#ሼር።
https://t.me/YariedDessale/5079
https://t.me/YariedDessale/5091
The Universal Catholic Church Teaching Channel.
1.1K viewsedited 06:56