Get Mystery Box with random crypto!

ጌታዬ ሁለመናዬ!

የቴሌግራም ቻናል አርማ yarieddessale — ጌታዬ ሁለመናዬ!
የቴሌግራም ቻናል አርማ yarieddessale — ጌታዬ ሁለመናዬ!
የሰርጥ አድራሻ: @yarieddessale
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.11K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ አንዲት፡ ቅድስት፡ ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተ-ክርስቲያን ምንነትና ምን እንደምታስተምር ለማወቅ፣ ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ፤ ስለመላዕክት፣ ስለቅዱሳን-ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣ ተዓምራት፤ የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስን ወቅታዊ ትምህርቶች፤ መንፈሳዊ ፊልሞችን ሁሉ በቀላሉ ያገኙበታል፡፡ #ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 22:17:17 “እግዚአብሔር ይማረን፤ ይባርከን፤
ፊቱንም በላያችን ያብራ፤ ”
(መዝ. 67፥1)'
141 views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 20:24:38 "ልጅህን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለ ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም" (ምሳ. 22:6)
211 viewsedited  17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:07:12


Dear all Alumnis of Catholic School



This is to inform you that Nekemte Kidhanemihret Catholic School is planning to celebrate the 50th Year Golden Jubilee with a grand celebration which is planned to be hosted on October 5 and 6(Fulbana 25 fi 26), the grand ceremony will be on the second day which is Oct 6.
You are all invited to be part of this grand celebration and we are looking forward to have you all back in the school. We encourage everyone if you can to present educational materials like books, pen, bag, paper,etc..to support the students/ school as a gift or gratitude. You also will have opportunity to buy school bulletin which will be published in that day.

Happy 50th Year Anniversary to all students, teachers, directors and Alumnis of Catholic School!

#via Ye Duro YeNekmte Lijoch






https://t.me/YariedDessale/5219




The Universal Catholic Church Teaching Channel.
310 viewsedited  07:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 08:26:34 የእግዚአብሔር ምርጥ ሰዎች አይሳሳቱም፤ ምክንያቱም እነሱ እምነታቸው በተዓምራትና በድንቅ ስራዎች ላይ በቋሚነት አልተመሠረተም፡፡


https://t.me/YariedDessale
303 viewsedited  05:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 07:02:48
የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውምማል፤እግዚአብሔር ቸር እንደሆነ ቅመሱ፤እወቁም።
(መዝ 33፥7-1)

https://t.me/YariedDessale/5217
307 viewsedited  04:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:47:01


የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ታዛዥነት!!




#ታዛዥነት_ከእግዚአብሔር_የጸጋ_ሙላት_የሚመነጭ_የትሕትና_ፍሬ_ነው።
#እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ ትሑት ስለሆነች ታዛዥ ነበረች።

#ሁለተኛው_የቫቲካን_ጉባኤ ስለ ማርያም ታዛዥነት አስፍቶ ይናገራል። “የእግዚአብሔር መልአክ ፣ በናዝሬት ወደ ምትኖረው ድንግል ተላከ ፤ “አንቺ ጸጋ የተሞላሽ” እያለ ሰላምታ ባቀረበላት ጊዜ ፣ ይህንን ሰማያዊ ብሥራት “እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ ፤ አንተ እንዳልህ ይሁንልኝ” እያለች መለሰችለት።” ሉቃ 1፡38 ቅዱሳን አበው ቤተ ክርስቲያን ፣ በአምላክ የድኅነት ሥራ ፣ ማርያም በዝምታ ሳይሆን በፈቃደኝነት ፣ በእምነትና በታዛዥነት እንደተሳተፈች ያምናሉ። ምንክያቱም ፣ ቅዱስ ኢረኒዮስ እንደሚለው ፣ እሷ ታዛዥ በመሆኗ ፣ ለራሷና ለሰው ዘር በሙሉ የድኅነት ምክንያት ሆነች። ስለዚህ አንዳንድ አበው ከቅዱስ ኢረኒዮስ ጋር በመሆን ፣ የሔዋን የእንቢተኝነት ቋጠሮ በማርያም ተፈታ ፤ ሔዋን ባለማመንዋ ያሰረችውን ነገር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በማመንዋ ፈታችው። … ብፅዕት ድንግል ማርያም ስላመነችና ስለታዘዘች ፣ የእግዚአብሔርን ልጅ በምድር ላይ ወለደችው። ለመውለድ የበቃችው ከወንድ ሳትገናኝ ከመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው። በሁለቱም መካከል ንጽጽር በማድረግ ለማርያም “የሔዋን እናት” ብለው ይጠሩዋታል ፤ ቀጥሎም “ሞት በሔዋን መጣ” “ሕይወት ግን በማርያም መጣ” ይላሉ።

#ቅዱሳን በእመቤታችን ማርያም ታዛዥነትና ፣ ስለ ታዛዥነትን ጥቅም እንዲህ እያሉ ይናገራሉ፦

#ቅዱስ_አጎስጢኖስ፥
“ያቺ የመለኮታዊው እናት በመታዘዟ ፣ ሔዋን ባለመታዘዟ ያመጣችብንን ጉዳት ካሠች” ይላል።

#ቅዱስ_በርናርዶስ፥
“ሰማች - አየች ፤ ሰማች - አመነች ፤ አየች - ገባት። ጆሮዎቿን ለመታዘዝ አዘነበለች” ይላል። “በብፅዕት ድንግል ማርያም ፣ መዘግየት የሚባል ነገር የለም። ስለዚህ ልክ በመንፈስ ቅዱስ እንደሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ ነበረች” ይላል ቅዱስ በርናርዶስ።

#ማርያም ፣ እግዚአብሔርን ከታዛዥነት በላይ የሚያስደስተው ነገር እንደሌለ ስለገባት ፣ በዚህ መንገድ ልታገለግለው ወሰነች። ታዛዥነት ፣ ትልቅ መስዋዕትነት ፣ መንፈሳዊ ጀግንነት ፣ የጽድቅ መንገድ እንደሆነ ስለተገነዘበች ፣ የሕይወቷ ዓላማ አድርጋ ያዘችው። ቅዱስ ጳውሎስ ፣ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲናገር “እስከ ሞት ታዛዥ ሆነ” ፊል 2፡8 ይላል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ደግሞ እንደ ልጇ፣ ከልጅነት እስከ ሞት ታዛዥ ሆነች። ይህንን ከባድ የታዛዥነት ቀንበር በደስታ ተሸከመችው።
ለማን ትታዘዝ ነበር?
#መጀመርያ ለእግዚአብሔር ፣
#በመቀጠል ለሰው ትታዘዝ ነበር።

ለእግዚአብሔር ትታዘዝ ነበር፦
“ለኃጢአት ስርየት የሚሆን መሥዋዕት እንዲቀርብልህ አትጠይቅም ፤ በዚህ ፈንታ የአንተን ትእዛዝ በመስማት እንዳገለግልህ አደርግኸኝ። … ሕግህን በልቤ አኖራለሁ።” መዝ. 40፡ 6-8 እያለች ፣ እግዚአብሔርን በሁለንተናዋ ልታገለግለው ፈቃደኛ እንደሆነች ገለጸችለት። የራሷን ፍላጎት ትታ ፣ ፈጣሪዋ ልክ እሱ እንደሚፈልገው የታዛዥነትን መስዋዕት ልታቀርብለት ቁርጥ ፈቃድ አደረገች። እግዚአብሔር የመድኃኔ ዓለም እናት እንድትሆን ሐሳቡን በገለጸላት ጊዜ ፣ ያ የምትወደው የነበረው የንጽሕና ሕይወቷን ትታ ፣ የሱን ቅዱስ ፈቃድ በደስታ ተቀበለችው። ይህ የሚያስደንቅ ታዛዥነቷ ደግሞ ለሰው ልጅ ድኅነትን አመጣ ፤ የኃጢአታችንም ካሣ ሆነ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በመታዘዟ ምክንያት ፣ በኃጢአታቸው ተጸጽተው አማልጅነቷን ለሚማጠኑ ኃጢአተኞች ምሕረት እንዲያገኙ ፣ ከእግዚአብሔር ፊት ታቀርባዘዋለች። የሚያፈቅረው ልጁ በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኖ እንዲቀርብ የአባቱ ፈቃድ እንደሆነ ባወቀች ጊዜ ፣ ራሷን ዝቅ አድርጋ ፣ የአምላክን ፈቃድ ተቀበለችው። አምላክ በተለያየ መንገድ ሲገለጥላት ሳለ ፣ ቶሎ ብላ ትከተለው ነበር። ሁልጊዜ ይህንን መለኮታዊ ፈቃድ ፣ ፍላጎት ትመለከት ነበር። በተለያየ ዓይነት መከራ ውስጥ ብታልፍም በደስታ ትቀበለው ነበር። ታዛዥነቷ ፣ በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ፣ የሚያስደስት ፣ ፍሬ ያለው ነበር።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በአነጋገሯ ፣ በሥራዋ ፣ በሓሳቧ እግዚአብሔርን አትቃወምም ነበር። ለራሷ ምንም ሳታስቀር ለእግዚአብሔር በሁለንተናዋ ትታዘዘው ነበር።

ዛሬ ላይ እኛስ ፣ እግዚአብሔርን እንደዚህ አድርገን እንታዘዘዋለን ወይ? ልክ እንደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሁልጊዜ የሱን ፈቃድ ነው የምፈጽመው? ፤ ፈቃዱ ልፈጽም ነው የመጣሁት እንላለን ወይ? የእርሱን ቅዱስ ፈቃድ ፣ ከልባችን በታዛዥነት መንፈስ ቶሎ ብለን እንፈጽመዋለን ወይ? የሕይወታችንስ ዓላማ ነውን? እስኪ እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች በመጠየቅ ሕሊናችንን እንመርምር።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአምላክ በመቀጠል ለሰው ትታዘዝ ነበር፡- የአምላክ እናት ነኝ ፤ ከፍጥረት በላይ ነኝ ፤ ስለዚህ ለአምላክ እንጂ ለሰው መታዘዝ የለብኝም ፤ ምክንያቱም ከእኔ በታች ናቸው ብላ ለሰው መታዘዝን እምቢ አላለችም። ለሰው መታዘዝ የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑ አውቃ ፣ ለወላጆቿ ፣ ለካህናት ፣ ለቅዱስ ዮሴፍ ፣ ለሁሉም በሷ ላይ ኃላፊነት ለነበራቸው ሁሉ ትታዘዝ ነበር። ለጨካኞቹ ዓለማውያን ባለስልጣኖችም ሳይቀር ትታዘዝ ነበር። ስለዚህ ከሰው ጋርም ታዛዥነቷ ፍጹም ነበር።

ይህ የሚያንጽ ታዛዥነት በእኛ ሕይወት ዛሬ ላይ ይገኝ ይሆን? ለወላጆቻችን ፣ ለቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች ፣ ለመሪዎቻችን ፣ ለባለስልጣኖች እንዴት አድርገን ነው የምንታዘዘው? እነርሱ በሚያዙን ጊዜ በትሕትና እሺ ብለን እንታዘዛለን ውይ? በጥላቻ ፣ በንቀት ወይ በቸልተኝነት ደስ ሳይለን ነው የምንታዘዘው? የእግዚአብሔር ድምጽ የሆነችው ሕሊናችን ምን ትለን ይሆን?

ዘወትር የመታዘዝ እና የትሕትና ተምሳሌት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተምሳሌትነትዋን የሕይወታችን ክፍል እናደርገው ዘንድ በአማላጅነትዋ በልጇ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፊት ታቅርበን። አሜን!!!

#አቅራቢ: መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ
#ቫቲካን


የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን አስተምህሮዎችን ለማግኘት ከዚህ በታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑን፡፡
#ሼር።
#ክብር_ለአምላካችን_ይሁን።



https://t.me/YariedDessale/5216




The Universal Catholic Church Teaching Channel.
556 viewsedited  06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:19:46 "Here I am, The Servant of The Lord"

- World Youth Day —— WYD Panama 2019 English Version





343 views19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 22:19:13
#መልካም_ዜና



“አንተ እንደ መልከጼዴቅ የክህነት ሹመት
ለዘለዓለም ካህን  ነህ" ዕብ 7:17

የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን

የዲያቆን በቴ (ያዕቆብ) ጌቱ የማዕረገ ክህነትና እንዲሁም ኢዮብ ስዩም የማዕረገ ድቁና ቅዳሜ መስከረም 7 ቀን 2015 ዓ.ም በመቂ ካቶሊክ ኪዳነምህረት ካቴድራል በብፁዕ ሊቃ ጳጳስ አንቱአን ከሚለሪ, የቫቲካን አምባሳደር በኢትዮጲያ እጅ ስለሚቀበሉ እርሶም በዕለቱ  ከጥዋቱ 2 ፡ 30 በሚደረገው መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ እንድትገኙልን በማክበር ጠርተንዎታል።

( መቂ ሃገረስብከት )


" You are a Priest forever, according to the order of Melchizedek" Heb 7 ፡ 17

You are Cordially invited on the Joyful Occasion of the Priesthood Ordination of Deacon Bete ( Yaqob) Getu and the Ordination of Deaconate Eyob Siyum by his Grace Archbishop Antoine Camilleri, Apostolic Nunico to Ethiopia which will be held on Saturday the 17rd of September, 2022 at 8 ፡ 30 Am in Meki Kidane Mhiret Cathedral.

(Apostolic Vicariate of Meki)



https://t.me/YariedDessale/5214




The Universal Catholic Church Teaching Channel.
307 viewsedited  19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:06:37 Do You Believe? Yes, I believe!!

#Proud_to_be_Catholic, a great worship song!


African Credo - #I_Believe
(Catholic Television of Nigeria)







The Universal Catholic Church Teaching Channel.


https://t.me/YariedDessale/5212



The Universal Catholic Church Teaching Channel.
371 viewsedited  18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:17:42 #አንተ_በኔ_ልትኖር

(ዘማሪት የምስራች አበበ)




352 views17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ