Get Mystery Box with random crypto!

ጌታዬ ሁለመናዬ!

የቴሌግራም ቻናል አርማ yarieddessale — ጌታዬ ሁለመናዬ!
የቴሌግራም ቻናል አርማ yarieddessale — ጌታዬ ሁለመናዬ!
የሰርጥ አድራሻ: @yarieddessale
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.11K
የሰርጥ መግለጫ

ስለ አንዲት፡ ቅድስት፡ ሐዋርያዊትና ኩላዊት ቤተ-ክርስቲያን ምንነትና ምን እንደምታስተምር ለማወቅ፣ ስለ ቤተክርስቲያን ታሪክ፤ ስለመላዕክት፣ ስለቅዱሳን-ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃ፣ ተዓምራት፤ የር.ሊ.ጳ ፍራንችስኮስን ወቅታዊ ትምህርቶች፤ መንፈሳዊ ፊልሞችን ሁሉ በቀላሉ ያገኙበታል፡፡ #ክርስትናን_ክርስቶስን_እንወቅ፡፡
“አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፡፡” (ማቴ. 6:33)

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-19 06:21:07 " ከማመስገን ጋር በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ።"
(ወደ ቆላስይስ ሰዎች 4:2)
753 views03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 23:06:32



ሉቃ 6፡1-19
(( በክቡር አባ ምስራቅ ጥዩ*የተዘጋጀ))

የእሑድ ሐምሌ 10/2014 ዓ.ም.




የወንጌሉ ዐቢይ መልእክት:

1. በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነውን ወይስ ክፉ? ነፍስን ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት? (ሉቃ 6፡9)
2. የማዳን ኀይል ከእርሱ እየወጣ ሁሉንም ይፈውስ ስለነበር፣ ሰዎቹ ሁሉ ኢየሱስን ለመንካት ይፈልጉ ነበር(ሉቃ 6፡19)፡፡

#የኢየሱስ_ተልእኮ:
ኢየሱስ ሲናገር “እኔ የተላክሁት ለዚህ (ለማዳን) ስለሆነ ወደ ሌሎችም ከተሞች ሄጄ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል ማብሠር ይገባኛል” በማለት ያስተምራል፤ ይፈውሳል፤ ሰዎችን ይቀበላል፤ ሸክማቸውን ያቃልላል፤ በሰንበት ዕለት እንኳ የወደቀውን ያነሣል፤ ተጐሳቁሎ የኖረውንም ስብራቱን ይጠግንለታል፡፡ በኢየሱስ ዘንድ የሚባክን ምንም ዓይነት ጊዜ የለም፤ እንዲህ ነው የጌታ ኢየሱስ አገልግሎት፡፡


#የሙሴ_ሕግ_መምህራንና ፈሪሳውያን:

የሙሴ ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን የሚያዩትና የሚያከብሩት ሕይወትን ሳይሆን ሥርዓትን ነው፤ ትኩረታቸው በእውነተኛ መንፈስ የተሞላ ጸሎት ላይ ሳይሆን እንዲያው ውጫዊ የሆነ ሥርዓት ለመፈጸም መመላለስ ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ የሚያድነውን ኢየሱስን ማጥመድ፣ መክሰስና አሳልፎ መስጠት ይፈልጉ ነበር፤ ምክንያቱም እርሱ በሰንበት ዕለት ይፈውሳል፤ መፈወስ ደግሞ እንደ ሥራ ስለሚቈጥሩት “ሰንበትን ሻረ ወይም አረከሰ” በማለት ይከታተሉታል፡፡


#ሰንበት_ምን_ማለት ነው?
ሰንበት ማለት “ማቆም”፣ “መተው”፣ “ማቋረጥ” ነው፤ በመሆኑም በሰንበት ዕለት ሁሉም ነገር ይቆማል፡፡ ሰንበት መከበር የጀመረውም ገና ከኦሪት ጊዜ ነው(ዘጸ 20፡11፤ ዘዳ 5፡15)፡፡ ሰንበት በዋናነት የሚከበረውም ድንቅ የሆነው የእግዚአብሔር ሥራ ለማስታወስ ነው፤ ይህም ከግብጽ የባርነት ሕይወት ወደ ነፃነት የተሸጋገሩበት ነው፡፡ በእርግጥ እግዚአብሔር ራሱ ለስድስት ቀናት ያህል የመፍጠርን ሥራ ከሠራ በኋላ ሰንበትን አክብሮታል፡፡ ከክርስቶስ ትንሣኤ በፊት ሰንበት ቅዳሜ ቀን ነበር፡፡
ኢየሱስ ምንም እንኳ ሰንበትን በማክበር ወደ ምኲራብ በመሄድ ሃይማኖታዊ ሥርዓት በመፈጸምና በማስተማር ሥራ ቢሳተፍም የፈሪሳውያን የሰንበት አከባበር ግን በተለያየ ጊዜ ሲቃወመው ኖሮአል፡፡ በተለይም በሰንበት ቀን የማዳን ሥራውን ይተቹትና ይቃወሙት ለነበሩት ምላሽ ሲሰጣቸውና እርሱም በሰንበት ዕለት ሰዎችን ሲፈውስ ነበር፡፡


#የኢየሱስ_ጥያቄ

በሰንበት ቀን የተፈቀደው መልካም ማድረግ ነውን ወይስ ክፉ? ነፍስን ማዳን ነውን ወይስ ማጥፋት? (ሉቃ 6፡9)፡፡
ቀጥሎም ኢየሱስ እጀ ሽባውን “እጅህን ዘርጋ” አለው፡፡ እርሱም እጁን በዘረጋው ጊዜ ዳነለትና እንደ ሌላው እጅ ደህና ሆነ(ሉቃ 6፡10)፡፡ ይህ ሰው ሲፈወስ ምን ይሰማው ይሆን? ያፍርበት የነበረውን ዛሬ በጌታ ኢየሱስ ምላሽ ሲያገኝ እንዴት ይደሰት ይሆን? ክብሩን አጥቶ ሲሳቀቅ የኖረው ጌታ ሲያከብረውና ታሪኩን ሲለውጠው እንዴትስ ያመሰግን ይሆን?

#ከወንጌሉ_ቃል_ምን_እንማራለን?
ሕይወት ከሁሉም ይበልጣል፡፡ ሰንበት ማክበሩ መልካም ቢሆንም ሕይወት ግን ከምንም ጋር ሊወዳደር ወይም ሊነጻጸር አይችልም፡፡ በመሆኑም ለራሳችንና በዙሪያችን ላሉት ሰዎች ሁሌም ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ ነው፡፡ ሕመማቸውና ሥቃያቸው መረዳት ይገባል፡፡ አገራችን ከሃይማኖት አኳያ (ክርስትናም እስልምና) ሥርዓት ታከብራለች፤ ብዙ ትሰብካለች፤ ሰንበታትን ታከብራለች፡፡ ይህ መልካም ነው፡፡ ሆኖም ግን ለወንድሞቻችን ሕይወት ማሰብ ትተን እነሱን በዘራቸውም ሆነ በሌላ ምክንያት የምናሳድዳቸው ከሆነ ታዲያ ከሙሴ ሕግ መምህራንና ከፈሪሳውያን በምኑ ተሽለን ተገኘን?
ሌላው ደግሞ ኢየሱስ እጀ ሽባውን እንደፈወሰው ሁሉ ዛሬም በእኛም ሕይወት ውስጥ ሽባ መስሎ የሚታየውን ነገር መፈወስ ይፈልጋል፡፡ ለእጀ ሽባው “እጅህን ዘርጋ” በማለት እጁን በመዘርጋት እንዲተባበር ጠየቀው፡፡ ቅዱስ አውግስጢኖስ ሲናገር “ያለፈቃድህ የፈጠረህ አምላክ ያለ አንተ ትብብር አያድንህም” ይላል፡፡ ስለዚህ እኛም በሕይወታችን ውስጥ መፈወስ፣ መዳን፣ መፈታት ያለበት ነገር ካለ ወደ ኢየሱስ መቅረብ፣ የሚጠበቅብንን ተግባር ማከናወንና አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ሁሉ ከፍለን ከእርሱ ጋር መሆን ያስፈልጋል፡፡ አዎን ኢየሱስ ያድናል፤ ሆኖም ግን የእኛም ትብብርና ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡
“እጅህን ዘርጋ” የሚለው ዛሬ “ልብህን ክፈት”፣ “በልብህ ውስጥ ያለውን አጽዳ” እንደማለትም ሊተረጐም ይችላል፤ ከዚያም ኢየሱስ ቀሪውን ሥራ ይሠራዋል፡፡
ዛሬም ከጌታ ኢየሱስ የሚፈውስና የሚያድን ኀይል ይወጣል፤ ስለዚህ ልክ “ሰዎቹ ሁሉ ኢየሱስን ለመንካት ይፈልጉ ነበር”(ሉቃ 6፡19) እንዳለው እኛም በሙሉ ኀይላችን እንፈልገው፤ የጥያቄዎቻችን ምላሽ ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ ነውና፡፡
እርሱም ፈልጉ ታገኛላችሁ ብሎናልና(ማቴ 7፡7)፡፡ በሕይወታችን ውስጥ ሽባ መስሎ የሚታየውን ነገር ከጌታ ኢየሱስ ጋር በመተባበር እናቅናው፡፡

የተባረከና የተቀደሰ ዕለተ ሰንበት ይሁንልን! አሜን!!!

ለተለያዩ የካቶሊካዊት ኩላዊት ቤተክርስቲያን አስተምህሮዎችን በተከታታይ ለማግኘት ታች ያላውን ሊንክ በመጫንና #Join & #Share በማድረግ በቴሌግራም ቤተሰብ ይሁኑን፡፡




https://t.me/YariedDessale/5074





The Universal Catholic Church Teaching Channel.
863 viewsedited  20:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ