2022-07-20 12:23:13
የመቁጠርያ “ጠጠሮችን” (rosary beads) የያዘ ሽቦ፡-
የመቁጠርያ ጸሎታችንን መስቀሉ ያለበት ቦታን በመያዝ የሐዋርያት ጸሎተ ሃይማኖት በመድገም እንጀምራለን፣ ከዚያም በኋላ ሦስቱን ትንንሽ ድቡልቡል (ጠጠሮችን) አንድ በአንድ በመያዝ እግዚአብሔር እምነት፤ ተስፋና፤ ፍቅር እንዲሰጠን እንጠይቃለን፣ ከዚህ በኋላ ከእያንዳንዱ አሥር “ጸጋ የሞላሽ” በፊት “በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ!” የሚለዉን ጸሎት እናደርሳለን፣ አሥሩን “ጸጋ የሞላሽ” በምናደርስበት ጊዜ አሥሩን ድቡልቡሎች እንቆጥራለን፣ ከእያንዳንዱ አሥር “ጸጋ የሞላሽ” በኋላ “ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይሁን” የሚለዉን ጸሎት እናደርሳለን፡፡
I) የደስታ ምስጢራት፡
በክርስቶስ ሕይወት ዉስጥ የመጀመሪያዉ ደረጃ፡የመጀመሪያዎቹ 12 ዓመታት
1. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መጸነስ (ሉቃ. 1፡26-38)
2. የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድስት ኤልሳቤጥን መጎብኘት (ሉቃ. 1፡39-56)
3. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም በከብቶች በረት ዉስጥ መወለድ (ሉቃ. 2፡1-7)
4. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተመቅደስ መቅረብ (ሉቃ. 2፡22-32)
5. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተመቅደስ ውስጥ መገኘት (ሉቃ. 2፡41-52)
II) #የብርሃን_ምሥጢራት፡
በክርስቶስ ሕይወት ዉስጥ ሁለተኛዉ ደረጃ፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ይፋዊ ሕይወት፡
የብርሃን ምሥጢራት ክርስቶስ በመጨረሻዎቹ ሦስት ዓመታት ዉስጥ የሠራቸዉን ሥራዎች እያስታወስን እንድንጸልይ ይረዳናል፣ በዚህ ወቅት የምናደርሳቸዉ አሥሩ “ጸጋ የሞለሽ” ጸሎቶች ትንሽ ጊዜ ቆም ብለን በክርስቶስ ሕይወት የተከሰቱ ክስተቶችን እያሰብን እንድንቆይና ከማርያም ጋር ሆነን ወደ ክርስቶስ አተኩረን እንድንመለከት፤ እንዲሁም እንደ ማርያም እሱን ከልብ ማዳመጥ እንድንችል ይረዱናል፣
1. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ (ሉቃ. 3፡13-17)
2. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃና ዘገሊላ ዉሃን ወደ ወይን ጠጅ ቀየረ (ዮሐ. 2፡1-11)
3. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ሰበከ (ማር. 1፡15)
4. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ክብሩን በደብረ ታቦር ላይ ገለጸ (ማቴ. 17፡1-13)
5. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ቁርባንን ሰጠን (ሉቃ. 22፡14-20)
III) #የህማም_ምሥጢራት
በክርስቶስ ሕይወት ሦስተኛዉ ደረጃ፡ የክርስቶስ ህማማት
የህማማት ምሥጢራት ጋር መቁጠርያን በምንደግምበት ወቅት እመቤታችን ማርያም ወደ ጎልጎታ ከክርስቶስ ጋር ባደረገችዉ ጉዞ እናጅባታለን፥ ከርሷ ጋር በመሆን የመስቀል ጉዞ እስከ ልጇ መስቀል ሥር ድረስ አብረን እንጓዛለን፣
1. የኢየሱስ ሥቃይ በጌተሰማኒ አትክልት ቦታ (22፡39-46)
2. የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግንድ ላይ ታስሮ መገረፍ (ዮሐ. 19፡1-5)
3. በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራስ ላይ የእሾህ አክሊል ተደፋበት (ማር. 15፡16-20)
4. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀሉን ተሸከመ (ዮሐ. 19፡16-19)
5. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሞተ (ማቴ. 27፡45-50)
IV) #የክብ_ ምስጢራት፡
በክርስቶስ ሕይወት አራተኛዉ ደረጃ፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት ነዉ፡፡
ከክብር ምስጢራት ጋር የምንደግመዉ የመቁጠርያ ጸሎት ከክርስቶስ ጋር የምናደርገዉን ጉዞ ወደ ክብር ፍጻሜ የሚያደርስ ነዉ፣ ክርስቶስ ከሞት እንደተነሳ ሁሉ እኛም በመጨረሻዉ ቀን እንነሳለን፤ የሕይወት አክሊልንም እንደፋለን፣ ይህ ደግሞ ለእመቤታችን ማርያም የተደረገላት እዉነታ ነዉ፣ ስለዚህ እኛም ልክ እንደርሷ ክርስቶስን ከልብ መከተል ከቻልን እኛንም የሚጠብቀን ይህ ክብር ነው።
1. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሞት መነሳት (ማቴ. 28፡1-10)
2. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ ዐረገ (ሉቃ. 24፡50-53)
3. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በ50ኛዉ ቀን መንፈስ ቅዱስን ላከ (ሐሥ. 2፡1-4)
4. እመቤታችን ማርያም በክብር ወደ ሰማይ ወጣች (ራዕ. 12፡1-4)
5. እመቤታችን በሰማይ የክብር አክሊል ተቀዳጀች (ራዕ. 21፡5-7
ለተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን አስተምህሮዎችን ለማግኘት ታች ያላውን ሊንክ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑን፡፡ ሼር።
https://t.me/YariedDessale/5076
The Universal Catholic Church Teaching Channel.
802 viewsedited 09:23