Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa Education Bureau

የሰርጥ አድራሻ: @wwwaddisababaeducationbureau
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 106.72K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-12-16 11:59:59
ለ1ኛ እና ለ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለዋና እና ለምክትል ርዕሰ መምህርነት ለመወዳደር ለተመዘገቡ ተወዳዳሪዎች በከተማ ደረጃ የተዘጋጀ የፅሁፍ ፈተና ተሰጠ።

(አዲስ አበባ ታህሳስ 6/2016 ዓ.ም) የፈተና ሂደቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት በሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ተዘዋውረዉ ተመልክተዋል፡፡



የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ውድድሩ በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚካሄድ መሆኑን ጠቅሰው የፅሁፍ ፈተናዉን ገለልተኛ በሆነ አካል በከተማ ደረጃ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ የመንግስት ት/ቤቶችን ለመምራት የሚፈለገዉን እውቀት ብቃትና ክህሎት ያላቸዉን አመራሮች በውድድር ለመመደብ ፈተናዉ ያግዛል ብለዋል፡፡ ፈተናው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ፋይዳዉ የጎላ መሆኑንና 4335 ተወዳዳሪዎች በአራት የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናዉ የተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡


የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸዉ የከተማ አስተዳደሩ መምህራን ማህበር በገለልተኝነት በተዘጋጀዉ ፈተና ላይ የተሳተፈ መሆኑን በመግለጽ ማህበሩ በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ በሚካሄደዉ ውድድርም የአብይና የንዑስ ኮሚቴ አባል በመሆን እየሰራ መሆኑን ተናግረል፡፡
13.5K views08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-15 18:05:57 መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.4K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-15 18:05:53
በኦቲዝም ምንነት ጽንሰ ሀሳብና በኢቲዝም የተጠቁ ህጻናት ተማሪዎችን መንከባከብን መሰረት ያደረገ የግንዛቤ መስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።

(አዲስ አበባ ታህሳስ 5/2016 ዓ.ም) የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በኦቲዝም ምንነት ጽንሰ ሀሳብና በኢቲዝም የተጠቁ ህጻናት ተማሪዎችን መንከባከብ ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።


የጽ/ቤቱ የልዩ ፍላጎት አካቶ ት/ት እና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ትግበራ ቡድን መሪ ወ/ሮ ዘውዷ መሀሪ እንደገለፁት የስልጠናው ዓላማ በት/ቤቶቻችን የአእምሮ ውስንነት ያለባቸውና የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን መንከባከብ ብሎም ትምህርታቸውንና ማህበራዊ ግንኙነታቸው የተስተካከለ እንዲሆን መምህራንና ባለድርሻ አካላት መወጣት ያለባቸውን ሚና ምን መሆን እንዳለበት ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል።


ኦቲዝም ማለት የአእምሮ እድገት ዕክል ነው በመሆኑም በእዚህ ሁኔታ ያሉ የማህበረሰብ ክፍሎች ብዙ ጊዜ በማንኛውም ሁኔታ የተገደቡ፣ተደጋጋሚ ባህሪያትና ፍላጎት ያላቸው፣
ያልተለመደ የስሜት ህዋሳት ምላሾች የሚታይባቸው፣ ማህበራዊ ግንኙነታቸውንና መስተጋብራቸው ውስን የሆኑና ከተለያዩ ነገሮች ጋር ያለመላመድ ባህሪ ይስተዋልባቸዋል ያሉት ወ/ሮ ዘውዷ በየትኛውም ቦታና ት/ተቋም የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩረትና ፍቅር በመስጠት መንከባከብ ይገባል ብለዋል።

ተሳታፊዎቹም በኦቲዝም የተጠቁ ህጻናት ተማሪዎችን በመንከባከብና ፍቅር በመስጠት በትምህርታቸውና በማህበራዊ መስተጋብራቸው የተሻሉ እንዲሆኑ ሚናቸዉን እንደሚወጡ መግለፃቸዉን ከክፍለ ከተማው ያገኘነዉ ነረጃ ያመላክታል።
13.4K views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-15 12:09:02
የትምህርት ተቋማት የፅዳት ንቅናቄ ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሄደ።

(አዲስ አበባ ታህሳስ 5/2016 ዓ.ም) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ "ፅዳቱ የጠበቀ የመማሪያ ስፍራ፣ለመማር ማስተማር ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል" በሚል መሪ ቃል የአምስት ወራት ሳምታዊ የፅዳት ንቅናቄ ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር በወረዳ 04 በኡላዱላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተካሄደ።


በዚህ የትምህርት ተቋማት የፅዳት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ላይ ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን እንዲሁም የአካባቢያቸውን ፅዳት በመጠበቅ ጤነኛ ዜጋ ለመፍጠር የሚደረገውን ሂደት የማሳካት ተግባር እንደሚጠበቅባቸው ተመላክቷል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
13.4K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-13 17:46:45 መልስ ውድድር የተካሄደ ሲሆን ለአሸናፉ ተማሪዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በመርሀ-ግብሩም ተማሪዎች የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ጭፈራዎችን ፣ የኪነ-ጥበብ ስራዎችን በመነባንብ ፣ በስነ-ግጥምና በጭውውት አቅርበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
13.5K views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-13 17:46:40
የጸረ-ጾታዊ ጥቃት/ነጭ ሪቫን ቀን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በአብዮት እርምጃ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከበረ።

(አዲስ አበባ ታህሳስ 3 ቀን 2016 ዓ.ም) "መቼም ፣ የትም፣ በምንም ሁኔታ ጾታዊ ጥቃትን ዝም አንበል!" በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ32ኛ በሀገራችን ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረው የጸረ-ጾታዊ ጥቃት/ነጭ ሪቫን ቀን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረፅና ማካታት ባለሙያ ወ/ሮ ትዕግስት በሪሁን ፣ የቂርቆስ ከፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የልዩ ፍላጎትና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ቡድን መሪ አቶ ኤርሚያስ አካሉ ፣ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር መ/ሪት ፋሲካ ወርቁ እንዲሁም መምህራን፣ተማሪዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰርዓተ ጾታ ማስረፅና ማካተት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ትዕግስት በሪሁን በትምህርት ቤቶች አከባቢ የሚደረሱ ጾታን መሰረት የደረጉ ጥቃቶችን በመከላከል ብቁና የተሻለ ትውልድ መፍጠር የሁሉም ዜጋ ኃላፍነት መሆኑን ገልጸዋል።

በዓሉን በማስመልከት በተማሪዎች መካከል የጥያቀና
12.6K views14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-10 10:31:56 በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር አውጎስቲኖ ፓላሴ በበኩላቸው ኤምባሲው በወንዝ ዳርቻ ልማት እና በሌሎችም መስኮች ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ግንኙነት አጠናክረን እንቀጥላለንም ብለዋል።


ዛሬ የተመረቀው ቤላ የህፃናት እና ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ የእግር ኳስ፣ የእጅ ኳስ መጫወቻ፣ የመረብ ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ እና  የቮሊቦል ሜዳዎችን የገላ መታጠቢያዎችን እና የጂም መስሪያ ቦታውችን ያካተተ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሼን ዘግባል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com    
Instagram: -  https://www.instagram.com/aacaeb/
15.2K views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-10 10:31:45
"ለልጆች የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንዲሁም በስፖርትና ሥነ-ምግባር የተካኑ ሀገር ተረካቢዎችን ለማፍራት ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ ይገኛል" ከንቲባ አዳነች አቤቤ


(አዲስ አበባ ህዳር 30/2016 ዓ.ም ) የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲኖ ፓሌሴ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ-3 ቤላ የህፃናትና ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራን መርቀው ከፍተዋል።


በአዲስ አበባ ከ1ሺ 100 በላይ መሰል የስፖርት ማዘውተሪያዎች መገንባታቸውን በመድረኩ ላይ የተናገሩት ከንቲባ አዳነች፣ ከዚህ ውስጥ ከ500 በላይ የሚሆኑት ከለውጡ ወዲህ መገንባታቸውን ተናግው ለልጆች የተሻለች ኢትዮጵያን ለመገንባት እንዲሁም በስፖርትና ሥነ-ምግባር የተካኑ ሀገር ተረካቢዎችን ለማፍራት ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።


በከተማዋ አሁንም በቂ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደሌሉ የተናገሩት ከንቲባ አዳነች ይህንን በመገንባቱ ረገድ የከተማ አስተዳደሩ ከሚያከናውነው ተግባር ጎን ለጎን የተለያዩ ተባባሪ አካላት እንዲሳተፉ በቀረበው ጥሪ መሰረት የጣልያን ኤምባሲ ጥሪውን ተቀብሎ የስፖርት ማዘውተሪያውን ገንብቶ ማቅረቡን ጠቅሰው በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።


ይህ የህፃናት እና ወጣቶች ስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራ ያስመረቁት ይህ የስፖርት ማዘወተሪያ ስፍራበጣልያን አለም አቀፍ የልማት ትብብር እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሮጀክቶች ድጋፍ ጽህፈት ቤት ትብብር የተገነባ ነው።
14.0K views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-09 22:01:50 ባለሥልጣኑ ያዘጋጀው ሥልጠናም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ይህንን እንዲያውቁና እንዲከላከሉ ማስቻል መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ራስን ከጥላቻ በማጽዳት አብሮነት የተጠናከረባት ሀገር መገንባት እንደሚገባ ገልጸው ፥ በዚህ ሂደት በተለይም ወጣቱ ትውልድ ለሀገር ግንባታ አዎንታዊ ሚና የሚጫወት ሊሆን እንደሚገባም ነው ያመላከቱት።


ሥልጠናው በቀጣዮቹ ጊዜያትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የዘገበው ኢዜአ ነው።




መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com    
Instagram: -  https://www.instagram.com/aacaeb/
14.6K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-09 22:01:48
በማኅበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል እየተሰራ መሆኑ ተጠቆመ።


(አዲስ አበባ ህዳር 29/2016 ዓ.ም ) በማኅበራዊ ሚዲያ የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትየጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ገለጸ።

ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ መከላከል ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል።


ሥልጠናው በዋናነት የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ ምንነት፣ የማኅበራዊ ሚዲያ ባህሪያት፣ እውነትን ማጣራት የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።


የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር መሐመድ እድሪስ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ፥ ባለሥልጣኑ ከሚያከናውናቸው ሥራዎች ውስጥ አንዱ የሃሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግር ሥርጭትን መከላከል የሚያስችል ግንዛቤ ማስጨበጫ ነው።


አሁን ላይ የማኅበራዊ ሚዲያ መስፋፋትን ተከትሎ በአንዳንድ የማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚተላለፉ የሃሰተኛ መረጃዎችና የጥላቻ ንግግሮች አብሮነትን የሚሸረሽሩ ግለሰቦችን ለተሳሳተ ውሳኔ የሚያጋልጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።


በመሆኑም እነዚህን ድርጊቶች ለመከላከል በተለይም ታዳጊ ተማሪዎች ሃሰተኛ መረጃዎችንና የጥላቻ ንግግሮችን የመለየት የመከላከል ክህሎትን በመጨበጥ እንዳይሰራጭ በማድረግ የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸውም ነው ያስረዱት።
14.4K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ