Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa Education Bureau

የሰርጥ አድራሻ: @wwwaddisababaeducationbureau
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 106.72K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-12-08 17:00:59 በበአሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ ገንዘብ ደሳለኝ በበኩላቸው የዓለም አቀፍ የጸረ ኤድስ ቀንን ከማክበር ባለፈ ቫይረሱ በደማቸው ያለና ለችግር የተዳረጉ ዜጎችን መደገፍ የሁሉም ዜጎች ማህበራዊ ኃላፊነት መሆኑን አብራርተዋል :: ቀኑን በማስመልከትም ሕይወታቸውን በቫይረሱ ላጡ ወገኖች የጧፍ ማብራትና የህሊና ፀሎት ስነ-ስርዓትን መርተዋል ::

ዓለም አቀፍ የጸረ ኤድስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 36ኛ በሀገራችን ለ35 ኛ ጊዜ " የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ ኤች አይቪ መከላከል!" በሚል መሪ ቃል ተከብሯል ::

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
19.0K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-08 17:00:45
36 ኛው ዓለም አቀፍ የጸረ ኤድስ ቀን ተከበረ ::

(አዲስ አበባ ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት የኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ዓለም አቀፍ የጸረ ኤድስ ቀንን በማስመልከት ከቢሮ ሰራተኞች ጋር በተለያዩ መርሀ-ግብሮች አከበረ ::

ቀኑን አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ይህንን ቀን ስናከብር የሀገር ዜጎችን ሕይወት የቀጠፈ ፣ የሀገርን ኢኮኖሚ እድገት ያዘገየና ሕፃናትን ያለወላጅ ያስቀረ መሆኑን በመገንዘብ ራሳችንን ከቫይረሱ የመከላከልና ያወቅነውን ለሌሎች የማስተማር ኃላፊነት ከትምህርት ማህበረሰቡ የሚጠበቅ ነው ብለዋል ::

ቫይረሱን አስመልክቶ ያለው ችላ ባይነት ሰፊ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ጥላሁን መዘናጋቱን ትተን የሀገር ተስፋ የሆነውን አምራች ኃይል ለመታደግ አጋላጭ ሁኔታዎችን መቀነስ ለችግሩ የተጋለጡ ዜጎችን ማገዝና በመንከባከብ እንዲሁም ስለበሽታው በቂ ግንዛቤ በመያዝ ራስን መከላከል እንደሚገባ አሳስበዋል ::

ኤች አይ ቪ ኤድስ በሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ደረጃ በ2022 ያለውን ስርጭትና ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በመጡ የኤች አይቪ መከላከልና መቆጣጠር ሜኒስትሪሚንግ ቡድን መሪ በሆኑት አቶ ወንድሙ ደንቡ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል ::
17.4K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-08 15:13:20 የትምህርት መረጃ በትምህርት ስርዓት ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙም ሆነ ከዘርፉ ጋር በተገናኘ በየደረጃው ለሚወሰኑ ውሳኔዎች መሰረት በመሆኑ የወረዳ ባለሙያዎች ትክክለኛ መረጃ ማደራጀት እንደሚገባቸው የቢሮው የትምህርት መረጃ ባለሙያ አቶ ሀይለማርያም ቻለው አስገንዝበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
15.3K views12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-08 15:13:17
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ስርዓት ስራ አመራር ቡድን ለወረዳ የመረጃ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

(አዲስ አበባ ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም) ስልጠናው ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር የተላከ የ2016 ዓ.ም የትምህርት መረጃ መሙያ ቅጽ አሞላልን በተመለከተ የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኞቹ በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ማደራጀት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት መረጃ ባለሙያ አቶ ጋሻው አክሊሉ ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር የተላከ የትምህርት መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ አሞላልን በተመለከተ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ቅጹ በዋናነት የትምህርት ቤቶችን አጠቃላይ መረጃን ከማካተቱ ባሻገር የተማሪ ፣ የመምህር፣ የርዕሳነ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን መረጃ በአግባቡ መሙላት እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመው በየወረዳው የሚገኙ የመረጃ ባለሙያዎች በቅጹ መሰረት መረጃዎችን በመሙላት ለሚመለከተው አካል መላክ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።
15.8K views12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-08 11:32:45 #ማስታወቂያ

(አዲስ አበባ ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም) የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ እንገልፃለን ።


ማሳሰቢያ :-


• የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን

• የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች

o Website: http://Result.ethernet.edu.et

o Telegram : https://t.me/moestudentbot


ትምህርት ሚኒስቴር


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.8K viewsedited  08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-07 16:32:33 ፕሮጀክቱ ከ146 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ወጪ እየተገነባ ያለ መሆኑንና አጠቃላይ ወጪው በአርባ ምንጭ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ባለቤት የሚሽፈን መሆኑን ከትምህርት ቤቱ የተገኝ መረጃ ያሳያል ::


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
14.5K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-07 16:32:27
በቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመስክ ምልከታ ተደረገ ::

(አዲስ አበባ ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም) በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች እየተሰሩ ያሉትን ሥራዎች ምልከታ ለማካሄድ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እየተደረገ ያለው የመስክ ጉብኝት ዛሬም ቀጥሎ ውሏል ::

የመስክ ምልከታው በቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተደረገ ሲሆን የአጥር ፣ የስታዲየምና የቤተ ሙከራ ክፍሎች ግንባታ ያለበት ደረጃ ፣ የሴት ተማሪዎች መፀዳጃ ክፍሎች ሥራና የመማሪያ ክፍሎች እድሳት ስራዎች ያሉበት ደረጃ በምልከታው ውስጥ ተካቷል ::

እስካሁን ከታዩ የትምህርት ለልማት ፕሮጀክት ስራዎች ውስጥ ግዙፍና ሰፊ ስራዎች የተሰሩበት ፕሮጀክት መሆኑን የገለፁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በትምህርት ቤቱ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን አድንቀው ፕሮጀክቱ በፍጥነት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲውል አቅጣጫ አስቀምጠዋል :: ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በጊቢው የሚታየውን የውሃ እጥረት ችግር ለመቅረፍ የጉድጓድ ውሃ ቁፋሮና የማስፋፊያ ስራዎች ከውሃና ፍሳሽ ቢሮ ጋር በጋራ የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል ::

በመስክ ምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ዓለምፀሀይ ሽፈራው ፣ የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ተሾመ ባቱ ተገናኝተዋል ::
14.1K views13:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-05 11:40:36 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ታዬ ወልደ ኪዳን የስኩል ኔት ፕሮጀክቱ ከተጀመረ አንስቶ የተከናወኑ ተግባራትን ጨምሮ አስፈላጊነቱን እና በፕሮጀክቱ ውስጥ ስለሚገኙ እቃዎች በዝርዝር ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ባለሙያዎቹ በቀጣይ ወደሚመደቡባቸው ትምህርት ቤቶች በሚሄዱበት ወቅት የተበላሹ እቃዎችንም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች የጎደሉ እቃዎችን ዝርዝር ሪፖርት በአግባቡ በማቅረብ ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት በውሉ መሰረት መሰረተ ልማቱን ዳግም ስራ እንዲያስጀምር የበኩላቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
12.8K views08:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-05 09:59:55
በአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት(GEQIP-E) የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን ተሰጠ።


(አዲስ አበባ ህዳር 25/2016 ዓ.ም ) ኦረንቴሽኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት (GEQIP-E) ሪጅናል ኮርዲኔተር አቶ አሸናፊ ከበደ የሰጡ ሲሆን በመርሀ-ግብሩ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የቢሮና የክፍለከተማ የትምህርት ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡


ድጋፍና ክትትሉ በተመረጡ 1ኛ ፤ 2ኛ እንዲሁም የo ክፍልና የልዩ ፍላጎት የድጋፍ መስጫ ማዕከላት ባላቸው ትምህርት ቤቶች የሚካሄድ ሲሆን ድጋፍና ክትትሉ በዋናነት በፕሮግራሙ በዝግጅትና ትግበራ ምዕራፍ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ የሚገኙ ተግባራት አፈጻጸም ምንደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለመገምገምና ቀጣይ አቅጣጫ ለመስጠት ታስቦ የሚካሄድ መሆኑን አቶ አሸናፊ ከበደ አስታውቀዋል፡፡


አቶ አሸናፊ አክለውም በድጋፍና ክትትሉ የሚቀርቡ ግኝቶችን መሰረት ያደረገ ውይይት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚደረግና ቀጣይ አቅጣጫ እንደሚቀመጥ ገልጸው ፕሮጀክት ማስተባበሪያው የቀሪ ተግባራት አፈጻጸምን በየደረጃው የመከታተል የመደገፍና ወቅታዊ ግብረመልስ የመስጠት ተግባሩን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
13.4K views06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-04 21:07:05
በግዢና ፋይናንስ መመሪያዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ::


(አዲስ አበባ ህዳር 24/2016 ዓ.ም )የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፋይናንስ አስተዳደር ግዥና የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች በፋይናንስ አስተዳደርና ግዢ መመሪያ  እንዲሁም የጨረታ አከፋፈት ላይ ለዘርፉ ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና ሰጡ ::


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መክብብ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ እንዳሉት ስልጠናው አዲስ ስራውን የተቀላቀሉ ባለሙያዎች በአሰራሩ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በስራው ላይ የቆዩ ባለሙያዎችም ከልምድ ባለፈ ስራውን በእውቀት በመስራት ያለውን ተጠያቂነትና የስጋት አቅጣጫዎች እንዲለዩ ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል ::


ስልጠናው የፋይናንስ ቢሮ ግዥ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዮሐንስ የተሰጠ ሲሆን በአጠቃላይ ፋይናንስ አስተዳደር ደንቦችና የክፍያ ስርዓት ፣ በመንግስት ግዢ አካሄድ እንዲሁም የንብረት አያያዝ ላይ ዋና ትኩረት አድርጓል ::


ስልጠናው በሁለተኛ ቀን ውሎው በጨረታ ሰነድ አዘገጃጀትና አከፋፈት መስፈርቶችና ልዩ ባህሪ እንዲሁም የአገልግሎት ግዥና ልዩ ባህሪያቶች ላይ የፋይናንስ ቢሮ ሙያዊ ድጋፍና ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት አቶ ደሳለኝ ተሰጥቶ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል ::



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
15.3K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ