2022-06-06 07:22:35
ሩሲያ ከአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟን ገለፀች
ሩሲያ ከሰሞኑ ከአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር ተሽከርካሪዎችን እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟን የሀገሪቱ ዜና ወኪል ታስ ዘግቧል።
የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳይለግሱ አሳስበው ልገሳቸውን ከቀጠሉ ግን እርምጃ መውሰዴን እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቀዋል።
በተለይም ምእራባዊያን ሀገራት ረጅም ርቀት ተወንጫፍ ሚሳኤሎችን እንዳይለግሱ የተናገሩት ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ደህንነቷን ለመጠበቅ ስትል እርምጃ ትወስዳለች ብለዋል።
አሜሪካ፣ ስፔን እና ሌሎች የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ለዩክሬን ሚሳኤሎች እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ለግሰዋል ተብሏል።
እንደ ሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ከሆነ ምዕራባዊያን ለዩክሬን የጦር መሳሪያ በመለገስ ጦርነቱን የማራዘም እቅድ እንዳላቸው ተገልጿል።
Via Alain
92 viewsTurth Quset, 04:22