Get Mystery Box with random crypto!

ሩሲያ ከአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟን ገለፀች ሩሲያ ከሰሞኑ | TRUTH

ሩሲያ ከአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟን ገለፀች

ሩሲያ ከሰሞኑ ከአውሮፓ ሀገራት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር ተሽከርካሪዎችን እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ማውደሟን የሀገሪቱ ዜና ወኪል ታስ ዘግቧል።

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳይለግሱ አሳስበው ልገሳቸውን ከቀጠሉ ግን እርምጃ መውሰዴን እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቀዋል።

በተለይም ምእራባዊያን ሀገራት ረጅም ርቀት ተወንጫፍ ሚሳኤሎችን እንዳይለግሱ የተናገሩት ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ደህንነቷን ለመጠበቅ ስትል እርምጃ ትወስዳለች ብለዋል።

አሜሪካ፣ ስፔን እና ሌሎች የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ለዩክሬን ሚሳኤሎች እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን ለግሰዋል ተብሏል።
እንደ ሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ከሆነ ምዕራባዊያን ለዩክሬን የጦር መሳሪያ በመለገስ ጦርነቱን የማራዘም እቅድ እንዳላቸው ተገልጿል።

Via Alain