Get Mystery Box with random crypto!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት 114 ባለሀብቶች ጠፍተዋል አለ! በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 11 | TRUTH

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት 114 ባለሀብቶች ጠፍተዋል አለ!

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 114 የፕሮጀክት ባለቤቶች መጥፋታቸውን ተከትሎ ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ግብር ማጣቱን የክልሉ መንግሥት የገጠር መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት የገጠር መሬት አስተዳደር እና ኢንቨስትመት ቢሮ ኃላፊ አመንቴ ገሽ ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ በክልሉ በእርሻ፣ በማዕድን እና በሌሎች ኢንቨስትመንቶች ከዘጠኝ መቶ በላይ ፕሮጀክቶች በሥራ ላይ ይገኛሉ።

ከእነዚህ መካከል ከ2010 ጀምሮ እስከ 2014 ባለው ጊዜ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኹለት ቢሊዮን ብር በላይ ብድር በመውሰድ ወደ ሥራ ገብተው የነበሩ 114 የኘሮጀክት ባለቤቶች ጠፍተዋል። ለዚህም ዋናው ምክንያት በክልሉ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት መሥራት አልቻልንም በማለት እና በፍላጎታቸው ሥራ አቁመው መጥፋታቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል።