Get Mystery Box with random crypto!

የጃፓኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በተፈጸመባቸው ጥቃት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!! የቀ | TRUTH

የጃፓኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በተፈጸመባቸው ጥቃት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!!

የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በናራ ከተማ በዕጩ ቅስቀሳ ወቅት ከኋላቸው በጥይት ተመተው ሆስፒታል መግባታቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሆስፒታል ጥብቅ የህክምና ክትትል ሲደግላቸው ቢቆይም ህይወታቸው ሊተርፍ እንዳልቻለ ተነግሯል፡፡

ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው ግለሰብም ከእነ መሳሪያው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የ67 አመቱ ሺንዞ አቤ ጃፓንን ከ2012 እስከ 2020 ድረስ በነበሩት ስምንት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት መምራታቸው አይዘነጋም።

ሺንዞ አቤ ከጤና እክል ጋር በተያያዘ በፈረንጆቹ 2020 ላይ በገዛ ፍቃዳቸው ከስልጣን መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡

https://t.me/Tquset