Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikivah_ethiopiaa — TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2) T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tikivah_ethiopiaa — TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)
የሰርጥ አድራሻ: @tikivah_ethiopiaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.01K
የሰርጥ መግለጫ

@tikivh_ethiopia

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-05-31 20:34:41 https://vm.tiktok.com/ZMN1nLjsb/?k=1

open
2.0K viewsedited  17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 15:08:32 https://vm.tiktok.com/ZMLTpCqsM/?k=1
3.0K views12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 12:06:08
#AmharaRegion #እንድታውቁት

ከዛሬ ግንቦት 9 ጀምሮ በአማራ ክልል የጦር መሳሪያ ምዝገባ ይካሄዳል።

ይኸው የጦር መሳሪያ ምዝገባ ለአራት ቀናት የሚቆይ ሲሆን በክልሉ ከዚህ በፊት ያልተመዘገበ መሳሪያ የታጠቀ ግለሰብ በአካባቢው ባሉ የምዝገባ ማዕከላት መሳሪያውን ማስመዝገብ እንዳለበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምዝገባው የአማራን ህዝብ ደህንነት ለማስጠበቅ አጋዥ ኃይል ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ አመልክቷል።

@tikivah_ethiopiaa
3.3K views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 15:05:06 https://vm.tiktok.com/ZMLvs47CG/?k=1
3.3K views12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 10:25:02
#Update

" ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለን እንጠብቃለን " - የNATO ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶለተንበርግ

ከሩስያ ጋር 1300 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር የምትጋራው ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል የአባልነት ጥያቄዋን የፊታችን እሁድ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።

ስውዲንም የአባልነት ጥያቄዋን በተመሳሳይ ቀን ታቀርባለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

የNATO ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶለተንበርግ ፥ ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

ከሩስያ ጋር ክፉኛ የተቃቃረችው አሜሪካ የ2ቱን አገራት የአባልነት ጥያቄ እንደምትደግፍ አስታውቃለች ፤ ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይም ሁለቱ ሀገራት የNATO አባል እንዲሆኑ ፍላጎት አላቸው።

NATOን ለመቀላቀል ፍላጎት ካሳየችው ዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው እና ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደች የምትገኘው ሩስያ የፊንላንድ እና ስውዲን እንቅስቃሴ ክፉኛ አስቆጥቷታል።

ሩስያ ፤ የፊንላንድ የNATO አባልነት ጥያቄ የሩሲያ-ፊንላንድን የሁለትዮሽ ግንኙነትን እጅጉን እንደሚጎዳውን እና ለሰሜን አውሮፓ ቀጠና መረጋጋት እና ሰላም አደጋ እንደሆነ አስገዝባለች።

ይህንን የደኅንነት ስጋት ለማስወገድም ቴክኒካዊ የሆነ #የጦር እና ሌላ መልክ ያለው የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ እንደምትገደድ ዝታለች።

መረጃው ከቢቢሲ / ከሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተውጣጣ ነው።

@tikivah_ethiopiaa
3.0K views07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 17:08:06 ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

ነገ ሚያዚያ 24 ቀን 2014 ዓ.ም ዓ.ም በአዲስ አበባ የዒድ ሶላት ተጀምሮ እሰከሚጠናቀቀ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት፡-

ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ ስታዲዩም የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አከባቢ፤

ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ፤

ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ባሻ ወልዴ ችሎት ወይም ፓርላማ መብራት፤

ከፒያሣ አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቸርችር ጎዳና ቴዎድሮስ አደባባይ፤

ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ ስታዲየም የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ፤

ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር አካባቢ፤

ከሲኒማ ራስ በጎላ ሚካኤል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ጎላ ሚካኤል መስቀኛ፤

ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ፤

ከባሻ ወልዴ ችሎት በኦርማ ጋራዥ ወደ ፍል ውኋ መስኪድ የሚወስደው መንገድ ንግድ ማተሚያ ቤት፤

ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ፤

ከጦር ኃይሎች፣ ልደታ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ሜክሲኮ አደባባይ፤

ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ መንገዱ የሚዘጋ ሲሆን

ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ዝግ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ ከሳሪስ እና ከጎተራ ወደ አዲስ አበባ ስታዲዩም ለሚመጡ ከባድ ተሸከርካሪዎች መንገዱ አጎና ሲኒማ ጋር የሚዘጋ ይሆናል፡፡

ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

@tikivah_ethiopiaa
3.5K views14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-25 14:51:16 #AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ በዋዜማው እና በትንሣዔ በዓል እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲካ ፋንታ ገልጸዋል። (walta tv)

@tikivah_ethiopiaa
3.7K views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 19:55:02
የበዓል ገበያው እንዴት ይዟችኃል ?

በየጊዜው እየታየ ያለው የዋጋ ንረት የበዓሉን ድባብ እንደሚያቀዘቅዘው እሙን ነው።

ምን ያህሎቻችን ባለው የዋጋ ንረት ሳቢያ ኑሮ ፈተና እንደሆነብን እናውቀዋል፤ ምንም ያህል የዋጋ ንረቱ በአስፈሪ ሁኔታ ቢያሻቅብም በዓል ነውና በአቅም ሸምቶ ለማሳለፍ የሚሮጠው ብዙ ነው።

የዘንድሮው ገበያ ግን ከአምናውም በእጅጉ የተለየ ነው።

በተለይም በሀገራችን አንዳድን አካባቢዎች የእንስሳት ግብይት ዋጋ የማይቀመሥ ሆኗል። በርካቶችም ባለው የዋጋ ውድነት ሳቢያ ገዝቶ ከቤተሰብ ጋር ተደስቶ በዐል ለማሳለፍ ፈተና ሆኖባቸዋል።

ለአብነት ዛሬ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ወረዳ ያለውን ውድነት እንመልከት ፤ በባለፈው ዓመት በበዓል ገበያ 20 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረ በሬ በዘንድሮው ዓመት ከእጥፍ በላይ ጨምሮ በ45 ሺህ ብር ተሽጧል።

በባለፈው ዓመት የበዓል ገበያ አንደኛ ደረጃ በሬ 42 ሺህ 667 ብር የተሸጠ ሲሆን ዘንድሮው የበዓል ዋዜማ ገበያ በአማካኝ 59 ሺ 333 ብር ተሸጧል። የ16 ሺህ 666 ብር ጭማሪ አሳይቷል።

የበግ ሙክትን ባለፈው ዓመት የበዓል ገበያ 4 ሺህ 766 ብር የተሸጠ ሲሆን በዘንድሮው ዓመት የበዓል ዋዜማ ገበያ 8 ሺህ ብር ተሸጧል። ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በበግ የ3 ሺህ 234 ብር ጭማሪ አሳይቷል።

የደጀን ወረዳ ንግድ ገበያ ልማት ጽ/ቤት ፤ የዋጋ ጭማሪው መንስኤ የእንስሳት መኖ እጥረት እንደሆነ ማስረዳቱን ከደጀን ወረዳ ኮሚኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ውድ ቤተሰቦቻችን በአካባቢያችሁ ያለው የበዓል ገበያው እንዴት ይዟችኃል ? ዘይቱ ፣ እንቁላሉ ፣ ዶሮው ፣ በጉ ፣በሬው ስንት እየተባለ ነው
@tikivah_ethiopiaa
4.3K viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 21:41:12
#ትኩረት

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞንና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አዋሳኝ አካባቢዎች ያገረሸው የፀጥታ ችግር ነዋሪዎች ላይ የከፋ የደህንነት ስጋት ደቅኗል።

ከትላንት አንስቶ ባለው ሁኔታ የጉዳት ሪፖርቶች ያሉ ሲሆን የተሟላ መረጃ ለማግኘት ግን ለጊዜው አልቻልም።

" በአካባቢው ላይ ከዚህ በፊት በተከሰቱ ችግሮች እጅግ ከፍተኛ ስቃይ አይተናል ፤ ሴቶች ፣ ህፃናት፣ አረጋዊያን ያሳለፉትን መከራ በቃላት ለመግለፅ የማይቻል ነው " ያሉት በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ችግሩ ሳይስፋፋ በፍጥነት እልባት እንዲሰጠው ተማፅነዋል።

እስካሁን በክልል መንግስት ሆነ በዞንም ደረጃ ስላለው ሁኔታ የተባለ ነገር የለም።

በአዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ባለው ችግር ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መስመር ለደህንነት ስጋት በመደቀኑ በርካታ የህዝብ ተሽከርካሪዎች ለመቆም መገደዳቸውን እና በዚህም ከፍተኛ መጉላላት እየተፈጠረ መሆኑ ጥዋት ማሳወቃችን ይታወሳል።

ዛሬ ማምሻውን የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፤ ባለው ነባራዊ ሁኔታ ነዋሪዎች በየአካባቢያቸው ለዝርፊያ እና ለወንበዴ እንዳይጋለጡ ወጣቶች፣ የፀጥታ መዋቅሮች ሌሎችም አካላት ተደራጅተው አካባቢያቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፏል።

#TikvahFamily
@tikivah_ethiopiaa
3.6K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-18 20:28:44
" ሰው እየተሰቃየ ጡንቻን ማሳየት ይብቃ " - ፖፕ ፍራንሲስ

በዓለም ዙሪያ ያሉ ጦርነቶች እና ግጭቶች እንዲያበቁ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስትያን ሊቀ ጳጳሳ ፖፕ ፍራንሲስ አሳስበዋል።

ይህን ያሳሰቡት ትላንትና የትንሳኤን በዓል አስመልክቶ ባሰሙት ቡራኬ ነው። ዕለቱን " በጦርነት የተወረሰ የትንሳኤ በዓል " ያሉት ሲሆን ዐለም ለክፋት እና ለብጥብጥ እንዳይንበረከክ ተማጽኖ አቅርበዋል።

100,000 የሚጠጉ ምእመናን ፊት በሮም የጴጥሮስ አደባባይ ቆመው " ብዙ ደም መፋሰስ፣ ብዙ ዓመፅ አይተናል " ያሉት ፖፕ ፍራንሲስ " ብዙ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ራሳቸውን ከቦምብ ለመከላከል ሲሉ በአሁኑ ሰዓት ተሸሽገው ይገኛሉ " ሲሉ ስለ ዩክሬን ጦርነትና ለጦርነቱ ሰለባዎች አፅኖት ሰጥተው አሳስበዋል።

በሌሎች አካባቢዎች እንደ መካከለኛው ምስራቅ ፣ ሊባኖስ ፣ ሶሪያ ፣ የመን ፣ ኢራቅ ፣ አፍጋኒስታን፣ ሊቢያ እና አንዳንድ የአፍሪካ ክፍሎች ባሉ ግጭቶች ብዙ ሰዎች ስቃይ ላይ እንደሆኑም በማስታወስ ፤ ሰላም ማስፈን ይቻላል፣ ሰላም ግዴታ ነው፣ ​​ሰላም ቀዳሚ እና የሁሉም ሰው ሀላፊነት " ነው ብለዋል።

" ዐለም ጦርነትን መላመድ የለበትም፥ አዲስ የተስፋ ቀን ይምጣ፥ ለሰላም በቁርጠኝነት እንቁም ፥ ሰው እየተሰቃየ ጡንቻን ማሳየት ይብቃ " ያሉት የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ " የዐለም መሪዎች የህዝቡን ተማጽኖ ይሰማሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

መረጃው ከቪኦኤ እና ዶቼ ቨለ የተውጣጣ ነው።

@tikivah_ethiopiaa
2.8K views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ