Get Mystery Box with random crypto!

TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)

የቴሌግራም ቻናል አርማ tikivah_ethiopiaa — TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2) T
የቴሌግራም ቻናል አርማ tikivah_ethiopiaa — TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)
የሰርጥ አድራሻ: @tikivah_ethiopiaa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.01K
የሰርጥ መግለጫ

@tikivh_ethiopia

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-07-10 20:24:34 www.tiktok.com/@mobile_clinic1/live?source=h5_m&_r=1&user_id=7084471159593239558&sec_user_id=MS4wLjABAAAAMHc-670eCnOvy6BveGMu4hRT_lHk9q0GxYWb1OvXqD-YVEycbA-bFethZJhTYsfd&utm_source=more&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7116464247089104646&share_link_id=a218fcf1-091b-41ed-8672-1d777d7964cb&share_app_id=1233&ugbiz_name=Live
317 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 08:43:58
#NewsAlert #ኢዜማ

ፕሮፌሰር ብርሃኑ መሪ ፤ አርክቴክት ዮሐንስ ደግሞ ምክትል መሪ ሆነው ተመረጡ።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) አንደኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ባደረገው ምርጫ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋን እና አርክቴክት ዮሐንስ መኮንንን የኢዜማ #መሪ እና #ምክትል_መሪ አድርጎ መርጧል፡፡

በጉባኤው ላይ ወደ 900 ገደማ የፓርቲው አባላት ያተሳተፉ ሲሆን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ 549 ድምፅ ማግኘታቸው ተገልጿል።

ከፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር ለመሪነት የተወዳደሩት አቶ አንዱአለም አራጌ 326 ድምፅ ነው ያገኙት። አቶ አንዱአለም ከፓርቲው ምስረታ አንስቶ የፓርቲው ምክትል መሪ ሆነው ቆይተዋል።

ለምክትል መሪነት የተወዳደሩት አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን በጉባኤው የተመረጡ ሲሆን ለቦታው በተፎካካሪነት ቀርበው የነበሩት አቶ ሀብታሙ ኪታባ ነበሩ።

@tikivah_ethiopiaa
1.3K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 14:33:01 https://vm.tiktok.com/ZMNSRx2vx/?k=1
1.4K views11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 17:23:31
#MoE

በቻይና ሀገር ትምህርታቸው ሲከታተሉ የነበሩ ተማሪዎች ያቋረጡትን ትምህርት እንዲከታተሉ ተፈቅዷል።

ትምህርት ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ይሄንን ተከትሎ የቻይና መንግስት ባወጣው የኮቪድ- 19 ፕሮቶኮል ምክንያት በአጋጣሚ ወደሀገራቸው መጥተው መመለስ ያልቻሉ ተማሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት እና በቻይና ሀገር የሚገኘው ኤምባሲ ባደረጉት ጥረት የቻይና መንግስት ተማሪዎች ተመልሰው ያቋረጡትን ትምህርት እንዲከታተሉ መፍቀዱን አሳውቋል።

ስለሆነም ከዚህ ጋር በተያያዘው ፎርም መሰረት ተማሪዎች አስፈላጊ መረጃዎችን በመሙላት እጅግ ቢዘገይ እ.ኤ.አ. እስከ June 20/2022 ብቻ በሚከተለዉ ማስፈንጠሪያ በመግባት ፎርሙን ሞልተው በተከታዩ ኢሜይል አድራሻ እንዲልኩ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

Link- https://moe.gov.et/AddReso

Email፡ daddiketema@gmail.com,
educationattache@ethiopianembassy.org.cn

#ትምህርት_ሚኒስቴር

@tikivah_ethiopiaa
2.5K views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 14:38:16
#ድርድር

ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ መንግስት ከTPLF ጋር ድርድር ሊያደርግ እንደሆነ የተለያዩ ምንጫቸው በግልፅ ያልተገለፁ/ ያልተረጋገጡ መረጃዎች ሲወጡ ነበር።

ዛሬ ከህ/ተ/ም/ቤት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ድርድርን በተመለከተ መረጃ ሰጥተዋል።

" ከማንም ጋር ሰላም ነው የምንፈልገው። " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ፤ " እያንዳንዷ የሰላም ቀን ለእኛ ትርፍ ታስገኝልናለች። ሕዝብ ሳያውቀው የሚደረግ ድርድር የለም። " ብለዋል።

አክለውም ፥ " በይፋ የታወቀ አጥኚ ኮሚቴ ተቋቁሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካኝነት እየተመራ ሲሆን፣ እስካሁን ውጤቱን አላሳወቀም። የሚደራደረው ኮሚቴም ይሄ ነው። " ብለዋል።

" ውጊያ ሲመጣ ለሕዝብ አሳውቀን የጀመርን ሰዎች፣ ድርድር ከተጀመረ የሚያስደብቀን ነገር የለም። ነገር ግን፣ የብቻ ጠላት የለም የሀገር ጠላት እንጂ፣ ለብቻም የሚሰራ ሥራ የለም በጋራ እንጂ። " ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

የእኛም የሕዝባችንም ፍላጎት ለጥይት የሚወጣ ውጪ ለልማት እንዲወጣ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ሰላም እንፈልጋለን ማለታችን የተደበቀ ድርድር እናደርጋለን ማለት አይደለም " ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ፦
- በፀጥታ ተቋማት ዝግጅት፣
- በህግ ማስከበር፣
- በ ' ተረኝነት ' ጉዳይ ፣
- በማህበራዊ ሚዲያዎች ጉዳይ ፣
- ሌብነትን በተመለከተ፣
- የብሄራዊ ምክክሩን በተመለከተ የሰጧቸው ምላሽ እና ማብራሪያዎች በዚህ ታገኛላችሁ https://telegra.ph/PM-Abiy-Ahmed-06-14-2 (#PMOEthiopia)

@tikivah_ethiopiaa
2.0K views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 14:28:31
#Update : ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የሁለትዮሽ ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችሉ በፖለቲካ ፣መከላከያ፣ በባህልና በቱሪዝም፣ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

ስምምነቱ የተፈረመው ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ በቆየው 3ኛው የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ማጠናቀቂያ ላይ ነው።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ ኩል በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ፍሰሃ ሻዉል እና በናይጄሪያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ የሁለትዮሽ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ሁመር ዘናባ ፈርመውታል።

ሀገራቱ በመገናኛ ብዙሃን አስተዳደር እና አመራር በተለይም ፣የወጣቶች ተሳትፎ በማሳደግ እና የፖን-አፍሪካዊነትን የሚዘክሩ ይዘቶችን ለማበልፀግ በሚቻሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ በኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ መካከል ያለውን ፀጋ በመጠቀም ለሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች ተጠቃሚነት እንዲዉል ያስችላል ተብሏል።

ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ በአፍሪካ ያለዉን እምቅ የሰዉ ሀብት እና ገበያ በጋራ ማልማት እና መጠቀም በስምምነቱ ዉስጥ የተካተቱ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

የ4ተኛ የሁለቱ አገሮች የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ እ.ኤ.አ.2024 አቡጃ ከተማ- ናይጄሪያ እንደሚካሄድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikivah_ethiopiaa
1.6K viewsedited  11:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 22:11:34
ዜና እረፍት

#DawitNega

በትግርኛ የሙዚቃ ስራዎች በእጅጉ የሚታወቀው አርቲስት ዳዊት ነጋ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ተሰማ።

አርቲስት ዳዊት ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደነበር ተነግሯል።

የአርቲስት ዳዊት ነጋ የሙዚቃ ስራዎች የትግርኛ ቋንቋ ከሚያደምጡ ሰዎች ባለፈ ቋንቋውን በማያዳምጡትም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩ ናቸው።

ከሙዚቃ ስራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዘመይ፣ ቸቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ደስ ይበለኒ'ሎ፣ ቕዱስ ፀባያ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

@tikivah_ethiopiaa
1.7K viewsedited  19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 18:21:31
#Update

የደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለማቋቋም የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በሀድያና ስልጤ ዞን በቃጠሎና ምዝበራ የወደመውን የደብረ ኃይል ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን መልሶ ለማቋቋም የመሠረት ድንጋይ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ተቀምጧል።

በዚሁ ወቅት ፤ የስልጤ ዞን የሃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢ ሀጂ መሐመድ ከሊል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የክርስትና እምነት ተከታዮችንም ማፅናናተቸው ተነግሯል።

ሀጂ መሐመድ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት "ችግሩን የፈጠርነው እኛው ነን ችግሩን የምንፈታውም እኛው እንሆናለን" ሲሉ ተናግረዋል። " ቤተ ክርስቲያንና መስጂድ ግጭት ፈጥረው አያውቁም " ያሉት ሀጂ መሐመድ "እንዲህ አይነቱ ችግር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመጣ ነው " ብለዋል።

የፖለቲካና የራሳቸውን ፍላጎት ለማስፈፀም በየፌስ ቡክ የሚወራው እና የሚተላለፈው መልዕክት ለዚህ አብቅቶናልም ብለዋል። መስጂድንም ሆነ ቤተ ክርስቲያንን ከሚያፈርሱ ሰዎች ፈጣሪ ይጠብቃችሁ ሲሉ ተናግረዋል።

እንዲህ አይነት ክፋት ሲፈፀምም ፈጣሪ ዘብ ያድርን ያሉት ሀጂ መስጂድ ፈርሶ ቤተ ክርስቲያን ይኖራል ቤተክርስቲያን ፈርሶ መስጂድ ይኖራል የሚል እምነት ፈፅሞ የለንም ያሉ ሲሆን የራሱን የሚወድ የሌላውንም ይወዳል ብለዋል።

ሀጂ መሐመድ እነዚህ ቤተ ክርስቲያንን ላጥፋ የሚሉ እኛ የማናውቃቸው ከእምነት አስተምሮ ውጪ የሆኑ አጥፊዎች ናቸውም ብለዋል። አክለውም ፌስቡኩ በወሬ ቢሰራም እኛ በወሬ ሳይሆን በተግባር ለመፍታት እየታገልን ነው ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/EOTC-06-12

(EOTC)

@tikivah_ethiopiaa
1.6K views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 09:06:27
ሩሲያ ምዕራባዊያን ለዩክሬን የጦር መሳሪያ መስጠታቸውን እንዲያቆሙ አስጠነቀቀች

የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አሜሪካ እና ሌሎች ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዳይለግሱ አሳስበው ልገሳቸውን ከቀጠሉ ግን እርምጃ መውሰዴን እንደሚቀጥሉ አስጠንቅቀዋል።

በተለይም ምእራባዊያን ሀገራት ረጅም ርቀት ተወንጫፍ ሚሳኤሎችን እንዳይለግሱ የተናገሩት ፕሬዝዳንት ፑቲን ሩሲያ ደህንነቷን ለመጠበቅ ስትል እርምጃ ትወስዳለች ብለዋል።

የሩሲያ ጦር ከአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን የተለገሱ የጦር መሳሪያዎችን ማውደሙን አስታውቋል።
2.1K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 20:55:12
#NewsAlert

አሜሪካ አዲስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሾመች።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ፤ በአምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ምትክ አምባሳደር ማይክ ሀመር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው እንደሚሾሙ አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ አምባሳደር ሳተርፊልድ በስልጣን ቆይታቸው ላበረከቱት አስተዋፆ ምስጋናቸውን አቅርበው አዲሱ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ሀመር አሜሪካ በቀጠናው የጀመረችውን ዲፕለማሲያዊ ጥረት እንደሚያስቀጥሉ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

የአምባሳደር ሀመር መሾም አሜሪካ በአካባቢው እያደረገች ያለችውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት መጠናከር መንግሥታቸው ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ብሊንከን አመልክተዋል።

" ከሁሉም በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ሰላም የሚወስደውን ሁሉን አካታች የሆነ የፖለቲካ ሂደት፣ የጋራ ደኅንነትና የመላ ኢትዮጵያዊያንን ብልጽግናን የሚደግፍ ነው " ብለዋል ብሊንከን።

አስተዳደራቸው " መላ ትኩረቱን ግጭት እንዲቆም፣ ሰብዓዊ ድጋፍ ባልተገደበ ሁኔታ እንዲደርስ፣ በሁሉም ወገኖች በተፈፀሙ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና ጥቃቶች ላይ ግልፅ ምርመራ እንዲደረግና ለግጭቱ መፍትሄ ለማምጣት ድርድር እንዲካሄድ ያደርጋል " ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

ከዚህ ቀደም የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዴቪድ ሳተርፊልድ ከሰኔ በፊት ከስልጣናቸው እንደሚለቁ መግለፁ ይታወሳል።

@tikivah_ethiopiaa
2.6K views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ