Get Mystery Box with random crypto!

🇸 🇲 🇮 🇱 🇪

የቴሌግራም ቻናል አርማ smilestube — 🇸 🇲 🇮 🇱 🇪
የቴሌግራም ቻናል አርማ smilestube — 🇸 🇲 🇮 🇱 🇪
የሰርጥ አድራሻ: @smilestube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 91
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን ደህና መጡ...🙏
የቻነላችን ቋሚ መርሀግብሮች
ቀልዶች
አስቂኝ አስገራሚ ምስሎች እና ቪዲዮዎች
ውብ አጫጭር እና ረጃጅም ታሪኮች ....
ሁሌም ፈገግ በሉልኝ😊😊😊

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-18 08:34:50 ከጎና ተቀምጬ ፎቶ ፖስት አድርጋ ያምራል እላታለሁ

"#ኮሜንት_ላይ_በለኝ" ትለኛለች
40 views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 18:32:14 ........አለም አላሚ በማጣት የሚንከራተቱ ሕልሞች ስብስብ ናት" @smilestube
48 views15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-10 20:14:00
ጨርሰው ሳያነብቡ እንዳያቋርጡት፡፡
እንዲሁም ለሚወዱት ሰው ሁሉ ሼር ያድርጉት።

የማናስተውላቸው ልምዶቻችን አንዳንዶቹ ለከፋ የጤና ችግር እንደሚዳርጉ አስበውት ያውቃሉ? ለጥንቃቄ ይቺን ጽሁፍ እነሆ ብለናል፡፡

መድኃኒት በቀዝቃዛ ውሃ አይውሰዱ፡፡
ውሃ ጠዋት አብዝተው ማታ ግን በጥቂቱ ይጠጡ፡፡
መድኃኒት ከወሰዱ ወይም ከተመገቡ በኋላ ወዲያው አይተኙ፡፡
ፕላስቲክ 'React' ስለሚያደርግ ሻይ በፕላስቲክ ዕቃ አይጠጡ ምግብንም በPolythene ወረቀት ላይ አይመገቡ፡፡
የስልክዎ ባትሪ መጠን እጅግ ዝቅተኛ ከሆነ ስልክ አያንሱ፡፡ ምክንያቱም በዚህ ሰዓት 'ራዴሽኑ' በ1000 እጥፍ ይጠነክራል፡፡
የሞባይል ካርድ ሲገዙ በጥፍርዎ አይፋቁት፡፡ ምክንያቱም ቁጥሩ የተሸፈነው በሲሊቨር ናይትሮ ኦክሳይድ ስለሆነ ለቆዳ ካንሰር ተጋላጭ ያደርጎታል፡፡
ሞባይሎትን በፍጹም ቻርጅ ላይ አድርገው አይጠቀሙ
በሞባይል ስልክ ሲነጋገሩ በግራ ጆሮዎ ብቻ ይነጋገሩ፡፡
የተሻለ የእንቅልፍ ሰዓት የሚባለው ከምሽቱ 4:00 ሰዓት እስከ 10:00 ያለው ነው፡፡
ከቀኑ 11:00 ሰዓት በኋላ ከበድ ያለ ምግብ አይውሰዱ፡፡

ሼርርርር

@smilestube
68 views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 21:34:06 አጫጭር መረጃዎች የዩክሬን-ራሺያን ቀዉስ በተመለከተ

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ዜጎች እንዲዋጉ ጥሪ በማቅረብ መሳሪያ ለሚፈልጉት ሁሉ እንደሚሰጥ እና ዩክሬን ታሸንፋለች በማለት ተናግረዋል፡፡በተጨማሪም ጊዜያዊ የጦር አስተዳደር አውጀዋል።

እንግሊዝ ዋና ዋና የሩሲያ ባንኮች ንብረታቸው እንዲታገድ እና ከዩናይትድ ኪንግደም የፋይናንስ ስርዓት እንዲገለሉ የሚያስቻ ውሳኔ አሳልፋለች።በሌላ በኩል የእንግሊዝ የተቃዋሚው ሌበር ፓርቲ መሪ ሰር ኪር ስታርመር ዩክሬን የጦር መሳሪያ ያስፈልጋታል ሲሉ ተናግረዋል።

የሩስያ ፖሊስ ጦርነቱን ተቃውመው ሰልፍ የወጡ ከ650 በላይ ሰዎችን ማሰሩን የተቃውሞ ተቆጣጣሪ ቡድን ኦቪዲ-ኢንፎ አስታውቋል። ቡድኑ ሞስኮን ጨምሮ በ40 የተለያዩ ቦታዎች ሰልፎች መካሄዳቸውን ይፋ አድርጓል።

ሩሲያ 74 የዩክሬን ወታደራዊ ተቋማትን ማውደሟን አስታዉቃለች።የሩስያ የመከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በዛሬዉ እለት በዩክሬን የሚገኙ 74 ወታደራዊ መሠረተ ልማት አውታሮችን ያወደሙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል 11 የበረራ ማኮብኮቢያና ማረፊያ መውደማቸውን ኖቮስቲ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ ከንቲባ በከተማው የሰዓት እላፊ ጥለዋል፡፡የኪየቭ ከንቲባ የቪታሊ ክሊችኮ ለሩሲያ ጥቃት ምላሽ ለመስጠት በዩክሬን ዋና ከተማ የሰዓት እላፊ መታዘዙን የተናገሩ ሲሆን የከተማዋ ነዋሪዎች በመኪና ለመሸሽ ሲሞክሩ የሚያሳዩ ምስሎችን መሰራጨቱን ተከትሎ ነዉ፡፡

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ኔቶ ዋና ጸሀፊ ስቶልተንበርግ  ኔቶ ወታደሮቹን ወደ ዩክሬን የመላክ እቅድ የለውም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ኔቶ በዩክሬን ውስጥ ምንም ወታደር እንደሌለው በመግለጽ በሞስኮ ወረራ ምክንያት አዲስ ማዕቀብ የሚጣልበት የአውሮጳ ህብረት አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት ስብሰባ ጠርተዋል፡፡ብሄራዊ የጸጥታ ምክር ቤቱ እንዲሰበሰብ የተፈለገዉ በዩክሬን ጉዳይ ለመወያየት መሆኑን የዋይት ሀውስ ባለስልጣናት አስታዉቀዋል፡፡

የሩሲያ የማዘጋጃ ቤት ተወካዮች፣ ጋዜጠኞች እና ሳይንቲስቶች ወረራውን የሚቃወሙ ግልፅ ደብዳቤን ፅፈዋል። የሞስኮ፣ ሴንት ፒተርስበርግ፣ ሳማራ እና ቮልጎግራድ ከተሞችን ጨምሮ ከ180 በላይ የማዘጋጃ ቤት ተወካዮች የፑቲንን ዩክሬን የመውረር ውሳኔ አጥብቀው አውግዘዋል።

የዩክሬን ጦር ወደ 50 የሚጠጉ የሩስያ ወታደሮችን ገድያለሁ እና ቢያንስ 6 የሩሲያ አውሮፕላኖችን መመታቱን ቢያሳዉቅም በገለልተኛነት አካል ግን አልተረጋገጠም፡፡

የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከሩሲያ አምባሳደር ጋር 'አስጨናቂ' ውይይት ማድረጋቸዉን ተናግረዋል፡፡

የዩክሬንን ሰማያዊ እና ቢጫ ባንዲራ የያዙ ሰልፈኞች ጸረ-ሩሲያ መፈክሮችን በማሰማት በለንደን ኋይትሆል ከዳውኒንግ ስትሪት ፊት ለፊት ተሰብስበዋል።"አሸባሪ" እና "ነፍሰ ገዳይ" ከሚሉት ቃላት ጎን ለጎን የቭላድሚር ፑቲን ምስል የያዙ ሰልፈኞች በስፍራዉ ድምጻቸዉን አሰምተዋል፡፡

የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሩሲያ ለውይይት ዝግጁ ትሆናለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡እንደ አለመታደል ሆኖ ምዕራባውያን ጓደኞቻችን ዓለም አቀፍ ህግን አያከብሩም፣ ለማጥፋት እና ደንቦችን መሰረት ያደረገ ስርዓት የሚሉትን ለማስተዋወቅ አይሞክሩም ሲሉ ላቭሮቭ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ፈረንሳይ ከዩክሬን ጎን እንደምትቆም እና ሩሲያ በጎረቤቷ ላይ የምታደርሰው ወረራ ለአውሮጳ አህጉር ዘላቂ እና ጥልቅ መዘዝ እንደሚያስከትል አስጠንቅቀዋል፡፡

የዩክሬን ዲፕሎማት ከጎናችን ቆመሻል በማለት ኬንያን አመሰግናለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡በናይሮቢ የዩክሬን አምባሳደር አንድሪ ፕራቬድኒክ በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት የምታደርጉትን ድጋፍ በጣም እናደንቃለን ብለዋል።

የዩክሬን የድንበር ባለስልጣናት እንደተናገሩት የሩሲያ ሃይሎች ወደ ዩክሬን ኪየቭ ክልል እና ዚዮቶሚር ወደ ሚባለዉ ክልል ለመግባት እየሞከሩ ነው ሲሉ አስታዉቀዋል።

ከ4,000 የሚበልጡ ሰዎች በተለይም ሴቶች እና ህጻናት እስካሁን ዩክሬን ለቀው ወደ ሞልዶቫ የተሰደዱ ሲሆን እዚያው ሞልዶቫ ለመቆየት ወይም ወደ ሮማኒያ ሊሻገሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዜለንስኪ አማካሪ ኦሌክሲይ አሬስቶቪች ሞስኮ ጥቃት በከፈተች በሰአታት ውስጥ ከ40 በላይ የዩክሬን ወታደሮች ሲገደሉ፣ በርካቶች መቁሰላቸው እስከ 10 የሚደርሱ ንፁሀን መገደላቸውን ተናግረዋል።

@bbc_amharic1
53 views18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 21:32:01
ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬን ወታደሮች መሳሪያቸውን አውርደው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ አሳስብዋል!!

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን በሰጡት አጭር መግለጫ “ሊስቆመን የሚሞክር፣ በሀገራችን እና በህዝባችን ላይ ተጨማሪ አደጋ የሚጥል ማንኛውም አካል በታሪኩ አይቶት የማያውቀው እጣፋንታ ይገጥመዋል” ብለዋል፡፡

የሩሲያ ምላሽ ፈጣን እንደሚሆን የገለጹት ፕሬዝዳንት ፑቲን የወታደራዊ ዘመቻው አላማ በኪቭ አስተዳደር ለበርካታ አመታት ጥቃት እና የዘር ማጥፋት ሲፈጸምባቸው የነበሩትን ዜጎች መታደግ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬን ወታደሮች መሳሪያቸውን አውርደው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ አስገንዝበዋል፡፡

የዩክሬን ወታደሮች ትጥቃቸውን የሚፈቱ ከሆነ ከጦርነት ቀጣናው ለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀል እንደሚችሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን አስታውቀዋል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ግዛት ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ተገንጣይ ግዛቶች እውቅና ከሰጠች በኋላ በዩክሬን ላይ ሙሉ ጦርነት ከፍታለች፡፡ ተገንጣይ ግዛቶች ከሩሲያ ወታደራዊ ድጋፍ መጠየቃቸው ሩሲያ ወደ ዩክሬን ግዛት ለመግባቷ አንደኛው ምክንያት ነው፡፡

በሌላ ዜና የዩክሬን መከላከያ 50 የሩሲያ ወታሮችን መግደሉን አስታውቋል፡፡ የዩክሬን መከላከያ ለሀገሪቱ ዜጎች “ተረጋጉና በዩክሬን ወታደራዊ ኃይል ተማመኑ” ሲል ባወጣው መግለጫ ገልጿል። እስካሁን ዩክሬን አምስት የሩሲያ አውሮፕላኖች እና ሄሊኮፕተሮች መታ እንደጣለች ስትናገር፤ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ነገሩን አስተባብሏል፡

የዩክሬን ወታደራዊና የደኅንነት ተቋማት በሩሲያ የሚሳኤል ጥቃቶች ዒላማ መደረጋቸውን እና ሩሲያ የዩክሬን ወታደራዊ የጦር ሰፈሮች ላይ ኢላማዋን እንዳነጣጠረች ተገልጿል።

መረጃዎቻችንን ሼር በማለት ለሌሎች ያጋሩ።
@bbc_amharic1
39 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-26 16:37:49
ራስን መቀበል - ክፍል አንድ
ራስን መሆን (በ ዶ/ር ኢዮብ)

ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀብሎ፣ ሳይደባብቁና ሌላውን ሰው ለመሆን ሳይሞክሩ በነጻነት መኖር ማለት ነው፡፡ ራስን የመሆን ጉልበት የሚመነጨው ማንነቴን የሰጠኝ ፈጣሪ እንደሆነ ከማመን ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ስለማይቀበሉ ራሳቸውን ሆነው መኖር አይችሉም፡፡ ራሱን መቀበል ያስቸገረው ሰው ላይ የሚታየው የመጀመሪያው ምልክት ራስን አለመሆን ነው፤ የማይቀበሉትን ማንነታቸውን ለውጠው ለመታየት ሲሞክሩ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡
ፈጣሪ በሰጠን ማንነት ስንደላደልና ስንቀበለው ቀና ብለን መኖር እንጀምራለን፡፡

ራስህን ለመሆን መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-
1. መለወጥ ወይም ማሻሻል የምችለውን መለወጥና ማሻሻል፡፡
በማንነቴ ላይ የማልቀበለውን ነገር ለማሻሻል ጤናማ መንገዶችን መሞከሩ ክፋት አይኖረውም፤ ከተሳካልኝ፡፡ ቁም ነገሩ፣ አሻሻልኩbትም አላሻሻልኩት ራሴን ወደ መቀበል መምጣቴና ጤናማ የሕብረተሰቡ አካል ሆኜ መኖሬ ነው፡፡

2. መለወጥ ወይም ማሻሻል የማልችለውን መቀበል፡፡
ዘሬን፣ መልኬን፣ አወላለዴንና የመሳሰሉትን ከፈጣሪ የተቀበልኩትን አሁን የሆንኩትን ማንነት ለመቀየር አስቸጋሪ ወይም የማይቻል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምርጫዬ አንድ ነው፣ ራሴን ተቀብዬ፣ በተደላደለ አመለካከት ዓላማዬ ላይ በማተኮር በሰላም መኖር፡፡

3. አዎንታዊነትን ማዳበር፡፡
በራሳችን ላይም ሆነ በኑሯችን ላይ ያለንን አመለካከት ከጨለምተኝነት አውጥተን ወደ አዎንታዊነት የማሸጋገር ስራ ካለማቋረጥ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ይህ ነገሬ ጎዶሎ ነው እያልን ስንጨናነቅ ከመኖር፣ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት መመሪያዎች እየተከተልን አዎንታዊነትን ማዳበር ተመራጭ ነው፡፡

ይቀጥላል . . .
59 views13:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-15 18:00:50 ምክንያት አታብዛ !

የአንተ ምክንያት የትም አያደርስህም ላለመቀየርህ የምትደረድራቸው ሰበቦችህ የሚጠቅሙህ ስታረጅ ቁጭትህን ለማውራት ብቻ ነው (ሰውም ያኔ ያዝንልሀል ) ። ምክንያት አያድንህም ! የቻልከውን ሁሉ አድርገህ ራስህን ከ አሁኑ ቀይር ያኔ ነገ ለሚያሳዝኑህ ሰዎችም ጀባ ትላቸዋለህ።
Join & share @smilestube
60 views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-09 18:30:06 አንድ ጀለስ አለ እና ሁሌ ይቋጥራል። ቺክ ከሆነች ግን ተበድሮም ቢሆን ያደርጋል። እና አንድ ቀን ምሳ በልተን ስንነሳ ሂሳብ አዋጣ ሲባል "ይቅርታ ዝርዝር ስለሌለኝ ለዛሬዉ እናንተ ክፈሉ" ብሎ ላሽ ሊል ሲል አንዱ ተናዶ ምን ቢለዉ ጥሩ ነዉ...
.
.
አታመንዝር እንጂ አትመንዝር አልተባለምኮ ሂሳብ አምጣ
72 views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-23 20:28:26 "ለአንዳንድ ሰው ስኬት አግብቶ ልጅ መውለድ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንድ ሰው ደግሞ ተምሮ ዲግሪውን መያዝ ሊሆን ይችላል፣ ለአንዳንዱ ደግሞ ደግሞ ሚሊዮን ብር ባንክ ማስቀመጥ ሊሆን ይችላል፣ ለእኔ ስኬቴ በየቀኑ ራሴን ማሸነፌ ነው፣ ወደ አልጋዬ ስሄድ ህሊናዬ ዛሬ ምን ሰርተሻል ብሎ ለጠየቀኝ ጥያቄ መልስ መስጠት ነው። በዛ ረገድ ደስተኛ ነሽ ወይ ከተባልኩ አዎ ስኬት ግን መንገድ ነው ብትሄጂበት ጥግ የለውም፣ ደግሞ ደስ የሚለው መንገዱ ነው።"

ተወዳጇ አርቲስት ሳያት ደምሴ
92 views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-18 17:14:30 #የፌስቡክ_ፕሮፋይላችንን_እንዴት_መቆለፍ_እንችላለን?

የፌስቡክ ፐሮፋይላችሁን እንድትቆልፉ እመክራለሁ፡፡

ፌስቡክ ላይ ፖስት የምታደርጉት ፎቶ፤ቪዲዮ፤ ወይም መልዕክት ከፌስቡክ ጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያየው ለማድረግ ፐሮፋይላችንን መቆለፍ ይኖርብናል፡፡

እንዲሁም ፕሮፋይላችንንም ከጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያይ ፕሮፋይላችንን መቆለፍ አለበት፡፡

ለአንድሮይድ ስልኮች ላይ ብቻ ነው ይሄ አገልግሎት ያለው፡፡iOS ስልኮች ላይ አይገኝም፡፡

እንዴት ነው የፌስቡክ ፕሮፋይላችንን ሎክ /መቆለፍ የምንችለው?

1ኛ፦ፌስቡክ አፕሊኬሽን እንከፍትና ወደ ፕሮፋይላችንን እንገባለን

2ኛ፦ በቀኝ በኩል በመደዳ የሚታዩትን ሶስት ነጥቦችን ክሊክ ማድረግ፤

3ኛ፦ “Lock Profile” የሚል አማራጭ ሲመጣ እሱን ክሊክ ማድረግ፤

4ኛ፦ ቀጥሎ “Lock Your Profile“ የሚል ምርጫ ከስር ይመጣል፡እሱን ክሊክ ማድረግ፤

5ኛ፦ በመጨረሻ‘You Locked Your Profile' የሚል ይመጣል፤እዛው ላይ OK ብለን እንጨርሳለን፡፡

አሁን ፌስቡክ ፕሮፋይላችን ተቆልፋል፡፡

ፕሮፋይላችንን ጨምሮ ፖስት የምናደርጋቸው ፎቶዎች፤ቪዲዮዎች እና መልዕክቶች ከፌስቡክ ጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ማንም ሰው ማየት አይችልም፡፡

ከወደዱት ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉልን!

Join us @smilestube
95 views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ