Get Mystery Box with random crypto!

ራስን መቀበል - ክፍል አንድ ራስን መሆን (በ ዶ/ር ኢዮብ) ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀ | 🇸 🇲 🇮 🇱 🇪

ራስን መቀበል - ክፍል አንድ
ራስን መሆን (በ ዶ/ር ኢዮብ)

ራስን መሆን ማለት፣ ማንነትን ተቀብሎ፣ ሳይደባብቁና ሌላውን ሰው ለመሆን ሳይሞክሩ በነጻነት መኖር ማለት ነው፡፡ ራስን የመሆን ጉልበት የሚመነጨው ማንነቴን የሰጠኝ ፈጣሪ እንደሆነ ከማመን ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ራሳቸውን ስለማይቀበሉ ራሳቸውን ሆነው መኖር አይችሉም፡፡ ራሱን መቀበል ያስቸገረው ሰው ላይ የሚታየው የመጀመሪያው ምልክት ራስን አለመሆን ነው፤ የማይቀበሉትን ማንነታቸውን ለውጠው ለመታየት ሲሞክሩ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡
ፈጣሪ በሰጠን ማንነት ስንደላደልና ስንቀበለው ቀና ብለን መኖር እንጀምራለን፡፡

ራስህን ለመሆን መውሰድ የምትችላቸው እርምጃዎች፡-
1. መለወጥ ወይም ማሻሻል የምችለውን መለወጥና ማሻሻል፡፡
በማንነቴ ላይ የማልቀበለውን ነገር ለማሻሻል ጤናማ መንገዶችን መሞከሩ ክፋት አይኖረውም፤ ከተሳካልኝ፡፡ ቁም ነገሩ፣ አሻሻልኩbትም አላሻሻልኩት ራሴን ወደ መቀበል መምጣቴና ጤናማ የሕብረተሰቡ አካል ሆኜ መኖሬ ነው፡፡

2. መለወጥ ወይም ማሻሻል የማልችለውን መቀበል፡፡
ዘሬን፣ መልኬን፣ አወላለዴንና የመሳሰሉትን ከፈጣሪ የተቀበልኩትን አሁን የሆንኩትን ማንነት ለመቀየር አስቸጋሪ ወይም የማይቻል እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ምርጫዬ አንድ ነው፣ ራሴን ተቀብዬ፣ በተደላደለ አመለካከት ዓላማዬ ላይ በማተኮር በሰላም መኖር፡፡

3. አዎንታዊነትን ማዳበር፡፡
በራሳችን ላይም ሆነ በኑሯችን ላይ ያለንን አመለካከት ከጨለምተኝነት አውጥተን ወደ አዎንታዊነት የማሸጋገር ስራ ካለማቋረጥ መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ይህ ነገሬ ጎዶሎ ነው እያልን ስንጨናነቅ ከመኖር፣ ከላይ የተጠቀሱትን ሁለት መመሪያዎች እየተከተልን አዎንታዊነትን ማዳበር ተመራጭ ነው፡፡

ይቀጥላል . . .