Get Mystery Box with random crypto!

ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬን ወታደሮች መሳሪያቸውን አውርደው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ አሳስብዋል!! የ | 🇸 🇲 🇮 🇱 🇪

ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬን ወታደሮች መሳሪያቸውን አውርደው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ አሳስብዋል!!

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቪላድሚር ፑቲን በሰጡት አጭር መግለጫ “ሊስቆመን የሚሞክር፣ በሀገራችን እና በህዝባችን ላይ ተጨማሪ አደጋ የሚጥል ማንኛውም አካል በታሪኩ አይቶት የማያውቀው እጣፋንታ ይገጥመዋል” ብለዋል፡፡

የሩሲያ ምላሽ ፈጣን እንደሚሆን የገለጹት ፕሬዝዳንት ፑቲን የወታደራዊ ዘመቻው አላማ በኪቭ አስተዳደር ለበርካታ አመታት ጥቃት እና የዘር ማጥፋት ሲፈጸምባቸው የነበሩትን ዜጎች መታደግ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ፑቲን የዩክሬን ወታደሮች መሳሪያቸውን አውርደው ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ አስገንዝበዋል፡፡

የዩክሬን ወታደሮች ትጥቃቸውን የሚፈቱ ከሆነ ከጦርነት ቀጣናው ለቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀል እንደሚችሉ ፕሬዝዳንት ፑቲን አስታውቀዋል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ግዛት ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ ተገንጣይ ግዛቶች እውቅና ከሰጠች በኋላ በዩክሬን ላይ ሙሉ ጦርነት ከፍታለች፡፡ ተገንጣይ ግዛቶች ከሩሲያ ወታደራዊ ድጋፍ መጠየቃቸው ሩሲያ ወደ ዩክሬን ግዛት ለመግባቷ አንደኛው ምክንያት ነው፡፡

በሌላ ዜና የዩክሬን መከላከያ 50 የሩሲያ ወታሮችን መግደሉን አስታውቋል፡፡ የዩክሬን መከላከያ ለሀገሪቱ ዜጎች “ተረጋጉና በዩክሬን ወታደራዊ ኃይል ተማመኑ” ሲል ባወጣው መግለጫ ገልጿል። እስካሁን ዩክሬን አምስት የሩሲያ አውሮፕላኖች እና ሄሊኮፕተሮች መታ እንደጣለች ስትናገር፤ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ነገሩን አስተባብሏል፡

የዩክሬን ወታደራዊና የደኅንነት ተቋማት በሩሲያ የሚሳኤል ጥቃቶች ዒላማ መደረጋቸውን እና ሩሲያ የዩክሬን ወታደራዊ የጦር ሰፈሮች ላይ ኢላማዋን እንዳነጣጠረች ተገልጿል።

መረጃዎቻችንን ሼር በማለት ለሌሎች ያጋሩ።
@bbc_amharic1