2022-08-03 11:52:53
የካቢኔ አባል የተደረጉት የቀድሞ የአልሸባብ ከፍተኛ አመራር ማንናቸው ?
በትላንትናው ዕለት የሶማሊያ ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ 26 አባላት ያሉትን ካቢኔ ይፋ አድርገዋል።
ጠ/ሚስትሩ በጠ/ሚኒስትርነት ከተሾሙ በኃላ ካቢኔያቸውን የሚያሳውቁበት ቀን በሶማሊያውያን ዘንድ በብዙ ሲጠበቅ ነበር።
ትላንት ይፋ ባደረጉት የካቤኔ አባላት ዝርዝር ግን አንድ የቀድሞ የአልሸባብ ከፍተኛ አመራርን ማካተታቸው የሚዲያዎችን ትኩረት ስቧል።
የሶማሊያ ካቢኔ ሹመት ያገኙት መክታር ሮቦው ናቸው።
ሙክታር ሮቦው፤ የቀድሞ የአልሸባብ ምክትል መሪ የነበሩ ሲሆን አሁን የሀይማኖት ጉዳዮች ሚኒስትር ተደርገው ነው በካቢኔው የተካተቱት።
ሮቦው ከ3 ዓመታት በላይ በሶማሊያ ብሔራዊ መረጃና ደኅንነት ኤጀንሲ (NISA) በቤት ውስጥ የቁም እስረኛ ሆነው አሳልፈዋል፤እንሆ ከ3 ዓመት በኃላ ወደ ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ መመለሳቸው ነው የተነገረው።
በአንድ ወቅት አሜሪካ ሮቦውን ለጠቆማት 5 ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ ገልፃ ነበር
ሮቦው በታህሳስ 2018 በቀድሞው የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሞሀመድ አብዱላሂ ሞሀመድ (ፋርማጆ) አስተዳደር ሊታሰር ችሏል
የቀድሞው የአልሸባብ መሪ በሶማሊያና በኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች (AU) ጥምረት ነው በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በNISA የቤት ውስጥ እስረኛ ሆነው ቆይተዋል።
በጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ የካቢኔ አባል ተደርገው የተመረጡት ሮቦው የአልሸባብ ታጣቂዎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመዋጋት መንግስትን ይረዳሉ ተብሎ ይጠበቃ
ፕ/ት ሀሰን ሼክ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የአልሸባብ ታጣቂዎችን በብቃት ለመታገል ቃል መግባታቸው ይታወቃል
NB : የካቢኔ አባላቱ ሹመት ወደፓርላማ ቀርቦ አፀደቀም። መቼ ፓርላማው እንደሚያፀድቀው አልታወቀም
975 viewsedited 08:52