Get Mystery Box with random crypto!

#Update ' ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለ | TIKVAH-ETHIOPIA️🇪🇹-(2)

#Update

" ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለን እንጠብቃለን " - የNATO ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶለተንበርግ

ከሩስያ ጋር 1300 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር የምትጋራው ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል የአባልነት ጥያቄዋን የፊታችን እሁድ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።

ስውዲንም የአባልነት ጥያቄዋን በተመሳሳይ ቀን ታቀርባለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

የNATO ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶለተንበርግ ፥ ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።

ከሩስያ ጋር ክፉኛ የተቃቃረችው አሜሪካ የ2ቱን አገራት የአባልነት ጥያቄ እንደምትደግፍ አስታውቃለች ፤ ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይም ሁለቱ ሀገራት የNATO አባል እንዲሆኑ ፍላጎት አላቸው።

NATOን ለመቀላቀል ፍላጎት ካሳየችው ዩክሬን ጋር ጦርነት ውስጥ ያለችው እና ወታደራዊ እርምጃ እየወሰደች የምትገኘው ሩስያ የፊንላንድ እና ስውዲን እንቅስቃሴ ክፉኛ አስቆጥቷታል።

ሩስያ ፤ የፊንላንድ የNATO አባልነት ጥያቄ የሩሲያ-ፊንላንድን የሁለትዮሽ ግንኙነትን እጅጉን እንደሚጎዳውን እና ለሰሜን አውሮፓ ቀጠና መረጋጋት እና ሰላም አደጋ እንደሆነ አስገዝባለች።

ይህንን የደኅንነት ስጋት ለማስወገድም ቴክኒካዊ የሆነ #የጦር እና ሌላ መልክ ያለው የአጸፋ እርምጃ ለመውሰድ እንደምትገደድ ዝታለች።

መረጃው ከቢቢሲ / ከሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተውጣጣ ነው።

@tikivah_ethiopiaa