Get Mystery Box with random crypto!

الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም

የቴሌግራም ቻናል አርማ tidar_be_islam — الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም ا
የቴሌግራም ቻናል አርማ tidar_be_islam — الزواج في الإسلام /ትዳር በኢስላም
የሰርጥ አድራሻ: @tidar_be_islam
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 23.43K
የሰርጥ መግለጫ

﴿وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُم مِّنْ أَنفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِّتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُم مَّوَدَّةً وَرَحْمَةً﴾
ለማንኛዉም አስተያየት☞☞ @Tidarbaislam_bot
ለይ ያድርሱን
ለጥያቄ ☞☞ t.me/Hayatbintkedir

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 19

2022-09-08 14:27:09 እስልምና ትልቅ ክብር ሰጥቶሻል። አላህ የቤት ንጉስ አድርጎሻል።

ተገላልጠሽ አደባባይ እንድትወጪና በእኩልነት ስም በየቢሮው ከወንዶች ጋር እንድትጋፊ ጥሪ የሚያደርጉልሽ የፊትና ተጣሪዎች እንዳይሸውዱሽ።

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
2.6K views11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:49:28
በሀላል መንገድ ኒካህ ማሰር አጅር የሚያስገኝና ሪዝቅን የሚያሰፋ ሲሆን በተቃራኒው ከኒካህ በፊት የሚደረግ የሀራም ግኑኝነት ግን ወንጀል ሲሆን ሪዝቅንም ያጠባል።

አላህ ሆይ! በነገራቶች ሁሉ ሀላሉን ወፍቀን ከሀራም ጠብቀን። አሚን

:::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
690 viewsedited  18:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:45:52 ክፍል አራት

ሁሉም እህት ወንድሞቻችን ሊያነቡት የሚገባ በጣም ወሳኝና አንገብጋቢ ርዕስ! ተከተሉን

የመተጫጨት አደቦቹና ገደቦቹ
 

ከክፍል ሶስት የቀጠለ

ስለዚህ በስልክ መደዋወል ከሆነ ለሃጃ መሆን አለበት ማለት ስለኒካሁ ጉዳይ፣ ወደፊት ስለሚሆነው ነገር በጣም አስፈላጊ ማውራት ያለባቸው ነገር ከሆነ ተደዋውለው በሃጃቸው ልክ አውርተው ይጨርሳሉ ከዛ ውጭ ድምፅ መለሳለስ፣መሳሳቅ፣ መቀላለድ፣ ምንድን ነው ምትወጂው/ምትወደው፣ ስላለፈው ህይወታችሁ ማውራት፣ ናፍቅሽኝ ናፈከኝና ሌሎችንም ትርፍ ወሬ ማውራት አይቻልም! በሸሪዓው የከለከለው ነው። መቀራረብ መዋደድ መፋቀር ከኒካህ በኋላ ነው ከዛ በፊት ፍቅር የለም የሸይጦን ወጥመድ ቢሆን እንጂ።! ፍቅርም ከተባለ የሃራም ፍቅር ነው ሚሆነው። የሃራም ፍቅር ደግሞ ገደል ውስጥ ነው የሚከተን። ከሸይጧን መረብ ውስጥ ነው የሚከቱን፣ ወደ ጀሃነም እሳት የሚያቃርብ እንጂ ወደ ትዳር መቃረቢያ አይደለም።!
በተለይ ትዳር በሱና መጀመር አለበት ገና ሲጀመር በሃራም መሆን የለበትም በሱና የሚጀመር ከሆነ ትዳሩ በረካ ይኖረዋል።
 ኒካህ እስካላሰረልሽ ድረስ የፈለገ ብትወጂውና ቢፈልግሽ አጅ ነቢይሽ ነው። አደራችንን ጥንቃቄ እናድርግ ካለፉት እህት ወንድሞቻችን ትምህርት እንውሰድ ይሄ መንገድ በጣም መጥፎና የብዙ እህቶቻችን ህይወት ምስቅልቅሉን አውጦታል! አላህ ይጠብቀን። ቁጥብነት ለራስ ነው። አይ አልሰማም የምን ከሆነ ወላሂ አላህ አያያዙ ብርቱ ነው በተለያዩ መንገዶች ይፈትነናል ተጋብተንም ሰላም ያለው ህይወት አይኖረንም ምክንያቱም መሰረታችን በሃራም የተጨማለቀ ስለሆነ ታዲያ እንደዚህ ከሆነ ለምን እንቀርበዋለን ይሄን መንገድ። አስቡት እስኪ ሃላል የሆነ ትዳር ይዛችሁ መዋደድ መተዛዘን የሌለበት ጭቅጭቅና ንትርክ የበዛበት ህይወት ትፈልጋላችሁ ይሄን ማንም አይፈልግም ስለዚህ በዚህ መንገድ ያልገባን ሰዎች ከዚህ በኋላም እንዳንገባ ጥንቃቄ እናድርግ በዚህ ህይወትም ውስጥ ያለን ሰዎች በአስቸኳይ ወደ ሃላል እንቀይረው ካልሆነ እስካሁን ላሳለፍነው ወንጀል ትክክለኛ ተውበት አድርገን ወደ አላህ እንመለስ ከምንገዱ እንራቅ።
በሃራም ነገር ላይም እያለን አላህን መገናኘት እንፍራ!

እናም በመልካም ንግግር ሃያዕ በተሞላበት ጥንቃቄ በተሞላበት ከፊትና የራቀ ንግግር ካልሆነ በስተቀር የሴት ልጅ ድምፇ ይፈትናል ምክንያቱም አላህ(ሱብሃነ ወተዓላ)"መልካም የሆነን ንግግር ተናገሩ ነገር ግን ለወንድ ልጅ ድምፃችሁን አታለስልሱ" ብሏልና
አዎ የሴት ልጅ ድምፅ በጣም ከባድ ነው ወንድ ልጅን በጣም ይፈትናል በተለይ ማለስለስ ማለዘብ የተለያዩ ቃላቶችን እየከሸነች የምትናገረው ከሆነ ይሄ ለወንድ ልጅ በጣም ፊትና ነው። ይሄን ነገር ሴቶች ልታውቁ ይገባል። ከዚህ ወንጀልም ልትርቁ ይገባል። ስለዚህ ባጭሩ ከትዳር በፊት እነዚህ መንገዶችን ልናደርጋቸው አይገባም ማለት ነው። ለዚህም ነው በሃጅ ላይ ያለች ሴት "ለበይክ አላሁመ ለበይክ" የሚለውን ቀስ ብላ ለራሷ በሚሰማት መልኩ እንድትል የተደረገችው። እንደ ወንዱ አትጮህም። ልክ አንደዚሁን አንድ ወንድ ልጅ በሶላቱ ውስጥ ቢሳሳት ወንድ ልጅ "ሱብሃናላህ" ብሎ ማስታወስ ተፈቅዶለታል ሴት ልጅ ግን አልተፈቀደላትም በእጇ ትንሽ እንድታጨበጭብ ነው የተፈቀደላት። ይሄ ሁሉ የተደረገበት ምክንያት የሴት ልጅ ድምፅ ስለሚፈትን ነው አዛን እንዳትልም ጩሃ ቁርዓንም እንዳትቀራ አልተፈቀደላትም። ስለዚህ ሴት ልጅ ወንድ ጋር ለሃጃ ስታወራ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ማለት ነው።

  ግን ከዚህ ሁሉ በላጩ በወልዮቿ ቢያልቅ ነው በአባቷ ወይም በውንድሟ በቤተሰቦቿ በኩል ቢያልቅ የተሻለ ነው ማለት ከተጫጩ ካያት ካየችው በኋላ እሱ ወደሷ ባይሄድ(ባይደውል)በቃ ሚፈልገውን ነገር ሁሉ ቤተሰቦቿን መጠየቅ ቢችል በጣም የተሻ ነው። ይሄ መሆኑ የተመረጠበት የተለያዩ  ወደሸይጦን ከሚወስዱ መንገድ ወደ ዚና ከመሄድ ለመጠንቀቅና ለመራቅ ነው።  ከዛ ኒካህ ካሰሩ በኋላ እንደፈለጉ መሆን ተፈቅዶላቸዋል። 

                ባረከላሁ ፊኩም
       (አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)

    ክፍል አምስት ይቀጥላል

ለአላህ ብለን በውስጥ መስመር በግሩፖችንም ቻናል ያለንም በቻናላችን ሼር እናድርገው።
በተለይ በውስጥ መስመር በምንችለው ሼር እናድርገው።

የሁላችንም ሃላፊት ነው ሃላፊነት የሚሰማን ሰው እንሁን! ለዲናችን ይችን ትንሽ ነገር እናድርግ!


በዚህ ህይወት ተጨማሪ ምክር ካስፈለጋችሁ እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁና በሃራም ምንገድ ላይ ሆናችሁ ለመውጣት እገዛ ካስፈለጋችሁ በውስጥ መስመር አማክሩኝ ሚስጥራችሁ ሁሌም የተጠበቀ ነው።
@jezakellah @jezakellah

          ለአላህ ብለን!
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
  ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር

ያለፉትንና የቀሩትን አስተማሪ መልዕክቶች ቻናላችንን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን። አልሃምዱሊላህ የብዙዎች የመመለስ ሰበብ ሆኗል።
በዝሙት አንዘምን ๓  የቴሌግራም ቻናል
   Join us on tg channel
     
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
   Onther channel
         በዝሙት አንዘምን ๓  
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
755 views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:52:52
☞::::ከአላህ የራቀ ልብ:::::☜

በህይወቱ ውስጥ እርካታን በፍፁም አያገኝም ።

☞ህይወት አላህን በእውነት ከልቡ
ለወደደው ናት ።

:::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
556 viewsedited  19:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 22:46:02 ﷽ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يصلون عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آَمنوا صَلُّوا عليه وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል;- አላህ ዘንድ ከቀኖች ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው። ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን፦"ሰሂህ"ብለውታል።
[አል ሲልሲለቱ ሰሂሃ: ቁጥር 1502] ,

የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ በጁምዓ ለሊትና በጁምዓ ቀን ላይ በኔ ላይ ሰላዋት ማውረድ አብዙ፣ በኔ ላይ አንድ ሰላዋት ያወረደ አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰላዋት ያወርድበታል።  ኢማሙ አልባኒ ሀዲሱን፦"ሀሰን"ብለውታል። 《አል ሲልሲለቱ ሰሂሃ: ቁጥር 1407》 , ከሱናዎችም መካከል ከልብስዎ ውቡን በመልበስና በጥሩ መዓዛ አውዶ መውጣት ናቸው።
والله اعلم وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وأصحابه وسلم

:::::ቴሌግራማችን::::::::::::

#ሼር    #ሼር

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
631 viewsedited  19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:58:44
☞:::::::እህቴ::::::::☜

የምታነቢውን መፀሃፍ ምረጭ የምታደምጭውን ሚዲያ ለይተሽ እወቂ።

ጆሮሽ እዛም እዚህም የሰማ እንደሆነ ልብሽ እዛም እዚህም የናፈቀ እንደሆነ ያጠሙሻል ገደል ይከቱሻል ።

የፊትና ዘመን ነውና።

:::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
1.9K viewsedited  07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:56:11 ክፍል ሶስት

ሁሉም እህት ወንድሞቻችን ሊያነቡት የሚገባ በጣም ወሳኝና አንገብጋቢ ርዕስ! ተከተሉን

የመተጫጨት አደቦቹና ገደቦቹ
 

ከክፍል ሁለት የቀጠለ

እናም ለብቻ መገናኘት አይቻልም አባት መኖር አለበት ወይም እናት ወይም ወንድም መኖር አለበት ወይ አጎት ወይም አክስት ባጭሩ ሁለታቸው ለመገለለ የሆነ የልጅቷ ቤተሰቦች መኖር አለባቸው።
  ከዛ ውጭ ግን ፈተናው ከባድ ነው አላህ(ሱብሃነ ወተዓላም)"ላ ተቅረቡ" (አትቅረቡ) ብሎ ልክ ከፍተኛ ቮልቴጅ እንዳለው የኤሌክትሪክ ሃይል አስጠንቅቆናል ሃሳባችን ትዳር ስለሆነ ብቻ እንደዚህ ልቅ የሆነ ግኑኝነት ልናደርግ አይገባም። አላህን እንፍራ በሃራም ያነካካነው ነገር መጨረሻው አያምርም ብንጋባም እንኳ።

"ሁለታቸው ለብቻ ከተቀመጡ ሸትጧን ሶስተኛው ነው"  ስለዚህ ጥንቃቄ ያስፈልጋል ትዳር ማለት ከአላህ ፀጋዎች ትልቁ ፀጋ ነው ስለዚህ በትዳር ስም አላህን ልናምፅበት አይገባም። አላህ(ሱብሃነ ወተዓላ) ባስቀመጠበት አደብ ብቻ ነው ሊሆን የሚገባው።

አጀማመሩም በሱና ሊሆን ይገባል በሱና የተጀመረ እስከመጨረሻው ያምራልና ስለዚህ ጥንቃቄ እናድርግ። ብዙዎቻችን እዚህ ላይ እየተሸወድን ነው ምክንያቱም ትዳሩ ሊሆንም ላይሆንም ወንጀል ይዘን መሄድ የለብንም ስለዚህ ለብቻ መገለል ሚባል ነገር ሊኖር አየገባም።
  ሃራም ነገር ላይ ሁነን በራስ መተማመን አይሰማን ወላሂ አላህ አያያዙ ብርቱ ነው በዚህ መንገድ አላህን ያውቁታል (ቀርተዋል)የተባሉ ልጆች ራሱ ተፈትነውበት ወድቀዋል።  አላህ ይጠብቀን!
ስሜታችን ስላለን ሳይሆን አላህ ባዘዘን መንገድ እንሂድ!
የሁሉም ነገር ቁልፉ በአላህ እጅ ነውና አጋብቶን እንኳ ሰላም የሌለው ትዳር አድርጎ ይፈትነናል። ስለዚህ ቆም ብለን እናስብ በገዛ እጃችን ዱንያችንንም አኼራችንንም አናበላሸው።

ሌላኛው  የመተጫጨት አደብ በሚገናኙበት ግዜ መጨባበጥ፣መተቃቀፍ፣ መሳሳም፣ በጭራሽ በጥብቅ የተከለከለ ነው የወንጀሉ ቅጣትም በጣም ከባድ ነው እባካችሁ ጥንቃቄ እናድርግ ምክንያቱም አጅ ነቢ ስለምንሆን ነው ኒካሁ እስካልታሰረ ድረስ አጅ ነቢ ነው ምንሆነው። ብዙ ግዜ ሃገራችን ላይ አይታችሁ ከሆነ እከሌ እሷን አጭቷታል ከተባለ ተጋብተዋል የተባለ ነው ሚመስለው ግን ማጨትና ኒካህ ማሰር በጣም የተለያዩ ነገር ናቸው። ምን አልባት ቢያወራት ችግር የለውም ያው በጋብቻው የተያያዘ ወሬ አንዳንድ በጣም ወሳኝ ወሬ ብቻ ሌላ ፊትና ሚቀሰቅስ ነገር ሳያወራ ያም በጣም በትንሹ ነው።
ስለዚህ በነዚህ ነገራቶች ላይ በጣም ጥንቃቄ እናድርግ በተለይ ሸይጧን በነዚህ ነገራቶች በጣም ይበረታል። ጨዋ የሆኑ ሴትና ወንዶችን አንዴ ይሄ ነገር ከተጀመረ ነገራቶች ሁሉ የተበላሹበት ሁኔታዎች ናቸው ያሉት ነገራቶችም እየዞሩ ነው ወደ ሃራም። ስለዚህ ከተያየን በኋላ ወንጀል ሳይገባ ቶሎ ወደ ኒካህ መግባት ነው ያለብን።
ካልሆነ ምን አልባት ነገራቶች ላይመቹ ይችላሉ የተራራቀ ቦታ ካሉና ቶሎ ለመጋባትም ነገሮች ካልተመቹ ግዜው እስከሚደርስ መራራቅ አለብን። በምንም አይነት መንገድ ግኑኘወነት ሊኖረን አይገባም!

በስልክም ቢሆን ስለ ትዳሩ ካልሆነ ብቻ ሌላ ወሬ ሊያወሩ አይፈቀድላቸውም። እሷም በሚያወራት ግዜ ድምፁዋን በማታለሳልስ ልትፈትነው አይገባም።

ካጨናት ሴት ጋር በስልክ መደዋወል ማለት ለመጋባት ተስማሙ እንጂ ኒካህ አሰሩ ማለት አይደለም። ኒካህ ሚባለው ንካህ ሲታሰር ነው ከዚህ ጋ ብዙ ሰዎች ይሸወዳሉ አጫት ማለት አገባት ማለት አይደለም! በጣም የሚገርመው አንዳንድ እህትና ወንድሞት ለመጋባት በመስማማታቸው ብቻ ሁኔታቸውን ስናይ የተጋቡ ነው ሚመስለው ባልና ሚስት እራሱ እንደዛ ግኑኝነት አይፈጥርም ይሄ የሸይጦን መንገድ ነው የሚገርመው እንዲህ ተቀራርበው የተጋቡ ሴቶች ከተጋቡ በኋላ ጀርባ ሲሰጣጡ ይታያል ምክንያቱም በሃራም ምንገድ ስለሆነ የመጡት አላህ ውዴታቸውን ያወጣባቸዋል አላህ ይጠብቀን ይሄ ትልው አደጋ ነው ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል። ተጫጫችሁ ማለት ታጋባችሁ ማለት አይደለም ነገ ሳትጋቡ ሊቀር ይችላል።
በጣም ብዙ ሃራም ነገር ይሰራል ካጫት በኋላ በየሰዓቱ ይደውላል የት ዋልሽ፣ የት ገባሽ፣ ምሳ በላሽ ፣ራት በላሽ፣ ተኛሽ፣ ተነሳሽ፣ ሰገድሽ፣ ቀራሽ እያለ በየሰዓቱ ይደውላል ይሄ ትክክል አይደለም አንዳንዶችም እየያዙ ይወጣሉ በቃ ቤተሰቦቿ እንኳ ወስዶ ቤቱ ቢያሳድራት ምንም አይመስላቸውም እንደፈለገ ይሆናል ሱብሃናላህ!! ይሄ ሃራም ነው ወላሂ አላህን እንፍራ።!!

              ባረከላሁ ፊኩም
       (አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)

    ክፍል አራት ይቀጥላል

ለአላህ ብለን በውስጥ መስመር በግሩፖችንም ቻናል ያለንም በቻናላችን ሼር እናድርገው
በተለይ በውስጥ መስመር በምንችለው ሼር እናድርገው።

የሁላችንም ሃላፊት ነው ሃላፊነት የሚሰማን ሰው እንሁን!

በዚህ ህይወት ተጨማሪ ምክር ካስፈለጋችሁ እንዲሁም ጥያቄ ካላችሁና በሃራም ምንገድ ላይ ሆናችሁ ለመውጣት እገዛ ካስፈለጋችሁ በውስጥ መስመር አማክሩኝ ሚስጥራችሁ ሁሌም የተጠበቀ ነው።
@jezakellah @jezakellah

          ለአላህ ብለን!
ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር
  ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር

ያለፉትንና የቀሩትን አስተማሪ መልዕክቶች ቻናላችንን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን አልሃምዱሊላህ የብዙዎች የመመለስ ሰበብ ሆኗል።
በዝሙት አንዘምን ๓  የቴሌግራም ቻናል
   Join us on tg channel
     
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
https://t.me/Tidar_Be_Islam
   Onther channel
         በዝሙት አንዘምን ๓  
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
1.9K views07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:37:30 ይቺ ምድር እድሜዋ ትንሽ ስቃይዋ ብዙ ነው።ስቃይና መከራ የሌለባት ደስታ ብቻ የሞላባት ለጀነትህ ሁሌም ልፋ!!

ለዝች ለርካሽ ሀገር ብለህ ውድ የሆነችዋን ጀነት አትጣት ልፋትህ ጭንቀትህ ሁሉ ውድ ለሆነችዋ ጀነት ይሁን!!

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ كَانَتْ لَهُمْ جَنَّاتُ الْفِرْدَوْسِ نُزُلًا

እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ የፊርደውስ ገነቶች ለእነሱ መስፈሪያ ናቸው፡፡

አላህ መልካም ስራ ሰርተዉ ጀበትን ከሚወፈቁት ያድርገን አሚን።

:::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
2.4K viewsedited  16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:33:36 አርተፊሻል ቆንጆ

በኩል አሳምራ ለስና ቅንድቧን
ክሬም ተቀብታ ሁለት ጉንጮቿን
በጋለ ካዊያ ተተኩሳ ፀጉሯን

አጭር ቀሚስ ለብሳ ገልጣ ሰውነቷን፣
ስትል ሰበር ሰካ አድርጋ ታኳዋን፣
በምድር ላይ ሳለች ከሷ ወዲያ ሴት
በዚህ አለም ቆንጆ የለለ መስላት፣

በጉራ ተገፍታ በትእቢት ተወጥራ፣
ልታይ ልታይ ብላ ስትል ኮራ ኮራ፣
ወዲያው ወረደና የዝናብ መአት፣
ለመሮጥ አትችል ልብሷ ሲወጥራት፣

ተበላሸ ተኩሱ ፀጉሯም በሰበሰ፣
የጉንጮቿ ክሬም በአይኗ ኩል ራሰ፣

ዝናብ አጠበና ሜካፑን ወሰደው፣
ፅጌሬዳ መስላ ከቤቷ ስትወጣ፣
ዝናቡ አስመሰላት ጭራሽ የሰው ጦጣ፣

ያ ያ ያ ሁሉ ቅባቅብ ሂጃቧን ያስጣላት፣
ለካስ አርተፊሻል ሰው ሰራሽ ቆንጆ ናት

:::::ቴሌግራማችን:::::::

╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝@Tidar_Be_Islam ❞
2.4K viewsedited  16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 12:46:59
❥::::::::ጥሩ ሚስት::::::❥

ይች አለም መጠቀሚያ ናት።ትልቁ መጠቀሚያና መደሰቻ ግን መልካም ሚስት ናት።
'❥ ጥሩ ሚስት ናት"
(የአላህ መልእክተኛ (ሰለሏሁ አለይሂ ወስለም) አላህ ጥሩ ሚስት ይወፍቀን። አሚን

::::::Telegram:::::

╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
╭┈─────── ೄྀ࿐ ˊˎ-
╰➤ ❝
@Tidar_Be_Islam
4.5K viewsedited  09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ