Get Mystery Box with random crypto!

ታሪካችንን እንወቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tarikacheninenwoke — ታሪካችንን እንወቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tarikacheninenwoke — ታሪካችንን እንወቅ
የሰርጥ አድራሻ: @tarikacheninenwoke
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 453
የሰርጥ መግለጫ

ይህ Channel ቀደምት የኢትዮጲያዊያንን ታሪክ የሚዘክር ታሪክ የሚያስተምር እና የተለያዩ በኢትዩጲያዊያን የተፃፉ የስነ-ፁሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ነው ። በድጋሚ ኢትዮጵያን እንወቅ !

አስታየት ጥቆማ ካላችሁ @Kalowohaset ያናግሩኝ

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-07 11:35:26 መልአኩም እንዲህ አላቸው
"እነሆ ለህዝብህ ሁሉ የሚሆን
ታላቅ ደስታ የምስራች እነግራችኋለው
#አትፍሩ!
ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነው ተወልዶላችኋልና።"

እንኳን ለጌታችን ለመዳኒታችን
ለ እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል
በሰላም አደረሳችው

መልካም በዓል!

@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
353 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-27 19:06:16 Watch "ኢትዮጲያዊ ! Like /Share" on YouTube






share
Subscribe
በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ !
470 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, edited  16:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-24 16:07:49 Watch "November 24, 2021" on YouTube


426 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-06-03 18:25:54
#ህፃኑ ሲጠይቅ

«ስሚኝ እናት አለም !»
«እሺ ምንድነው የኔ አለም ?»
«ያቺ ነገር ምንድናት ?»
«የት አለች?የት ነው ያየሃት?»
ሕፃኑም ዘረጋ እና እጆቹን ወደ ሰማይ !
ጨረቃዋን አሳያት ስታበራ አናታቸው ላይ !
«እሷማ ጨረቃ ናት !»
ብላ መለሰች እናት ።
«ጨረቃ ማለት ምንድነው ?»
«ይሄ ልጅ ምንድነው የሚለው ?»
«እናት አለም ጨረቃን አንቺም አታውቂያት ?»
« እንግዲህ አታስቸግረኝ ጨረቃ ጨረቃ ናት ።»
«ጨረቃስ እሺ ትሁን ታዲያ ተዚያ ላይ ማን ሰቀላት?»
«እግዚሐር ነው የፍጠራት ።»
« እግዚአብሄር ማለት ምንድነው ?»
«ይህ ልጅ ምንድነው የሚለው ?»
እግዚሐር ማለት ሰሪ ነው አንተን እኔን የሰራ ፤
ጨረቃንም የፈጠራት በለሊት እንድታበራ !»
«እኔን የሰራ እግዚሐር ነው ?»
«አዎን የሰራህ እግዚሐር ነው !»
«ታዲ አንቺ ምንድኔ ነሽ እናት አለም !»
«እንዴት አድርገሽ ወለድሺኝ ?»
«ውልድ ! አድርጌ ነዋ በቃ እንግዲህ አታድርቀኝ !»
«ምንድነው እናት አለሜ ስጠይቅሽ ምትቆጪኝ !»
«እሺ የኔ አለም ጠይቀኝ ! »
«እንዴት አድርገሽ ነው የወለድሽኝ ?»
«አንተ ልጅ ዝም በል ብያለሁ !
እራስህ አድገህ ድረስበት ፤
አሁን እኔ ስራ ልስራበት !»


አቤ ጉበኛ
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
1.1K viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-17 05:59:25
@tarikacheninenwoke
753 viewsᴛʜᴇᴏᴛᴏᴋᴏs, edited  02:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-02 10:03:59 የመቃብር ደጃፎች ተሰባበሩ
የመከራ ዘመን አበቃ
የእዳ ደብዳቤም ተቀደደ
ሰይጣን ከምድር በታች ታሰረ
የገነት በር ተከፈተ
አዳም ወደ ርስቱ ተመለሰ
ጌታችን በክብር ተነስቷል
ክርስቶስ ተንስዐ ሙታን
በአብይ ሃይለስልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አጋዝኦ ለአዳም
ሰላም እምዜሰ
ኮነ
ፍስሃ ወሰላም

እንኳን ለትንሳኤ በአል
በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
948 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 07:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-21 15:52:28 => አድዋ እና ሰበቡ
በሲራክ ወንድሙ
... ክፍል ፩
....... ይህ ፅሁፍ ኅብረ ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በቴዎድሮስ በየነ በ2008 ዓ.ም ከታተመው የታሪክ መፅሀፍ ውስጥ የአድዋ ድል ከሚለው ምዕራፍ ላይ ለአንባቢ እንዲበጅ (እንዲገባ) በሌላ ቅንፍ በትንሹ እውቀቷን ለማስጨበጥ በሌላ ሌላ ቅንፍ ለመላው አፍሪካ የነፃነት በዓል ምክኒያት በማድረግ ከ ፌስቡክ ሆይሆይታ ና ሆያሆዬ ባሻገር ጦርነቱ ላይ በምናብ በመገኘት ለመዘካከር ነውና ሳትሰለቹ አንብቧት።

መጀመሪያ ላይ ስለአድዋ ጦርነት መንስኤ ሲነሳ የውጫሌው ውል አንቀፅ አስራ ሰባት እንደሆነ በሰፊው ሲነሳ እንሰማለን
ውሉ ችግሩ ምንድነው? መቼ ተፈራረሙ? ውጫሌ የት ነው?

....ውጫሌ በወሎ ወረኢሉ ውስጥ የምትገኝ መንደር ስትሆን ይህን ውል የኢጣልያ መንግስት እና የኢትዮጵያ መንግስት በሚያዚያ 25 ቀን 1881 ዓ.ም በውሉ አስተርጓሚ በግራዝማች ዮሴፍ ንጉሴ የተከናወነ ውል ነው።
ውሉ ጠቅላላ 20 አንቀፅ ሲኖረው ለጦርነቱ መነሻ የሆነው አንቀፅ 17 ነው።

እስኪ አንቀፁን በሁለቱም ትርጉም እንመልከተውና ለጥቀን ሌላውን እንቀጥል:-
#በአማረኛ_የተፃፈው
"የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ከአውሮፓ ነገስታት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሁሉ የኢጣሊያ መንግስት አጋዥነት መላላክ ይቻላቸዋል።"

.... ይላል።
#በኢጣሊያኛ_የተፃፈው_ደግሞ
"የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ አገር መንግስታት ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት አማካኝነት ማድረግ ይገባቸዋል።"
...የሚል ነበር።

ጣሊያኖች ይህን ውል ከተዋዋሉ በኃላ ለ12 የአውሮፓ መንግስታትና ለዩናይትድስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ጭምር October 11 ቀን 1889 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ #ኢትዮጵያ_በኢጣሊያ_ስር_ነች እያሉ አሳወቁ።
በትምህርት ቤት መማሪያ ደብተሮችም ላይ ሁሉ ኢትዮጵያ በኢጣሊያ ጥገኝነት ስር ናት የሚል ታተመ።

ይህ ለአድዋ ጦርነት መነሳት ምክኒያት ና ዋነኛ መንስኤ የሆነው ጉዳይ ሊታወቅ የቻለው አለቃ አፅመ ጊዮርጊስ የተባሉ ቋንቋ አዋቂ አፄ ምሊኒክ በሰጧቸው ትዕዛዝ መሰረት የውሉን ሰነድ በመመርመር የውሉ 17ኛው አንቀፅ የያዘውን ትርጉም መዛባት በመግለፅ ጉዳዩ ኢትዮጵያ የምትጎዳበት ስለመሆኑ ጭምር በማስረዳት በሰጡት ቃል ነው።

............. ይህን ያህል ስለ17ኛው ውል መሳሳት አቅጣጫ ከያዝንና ካየን የትርጉሙ መጭበርበር እንዴት ከአለቃ አፅመ ጊዮርጊስ ለአፄ ምሊኒክ እንደደረሰ እንቃኝ።
አለቃ አፅመ ጊዮርጊስ ባልታተመ (ይህ የወንድማችን ቅፅ አንድ እስከወጣበት ጊዜ ድረስ) መፅሀፋቸው እንደገለፁት ለአፄ ለምሊኒክ እንዲህ ሲሉ በደብዳቤ አመለከቱ :-
<< የተፃፈው ውል ኢጣሊያ አገር የሚሄደው ማለፊያ ነው።
ብቻ 17ኛውን ክፍል ይመልከቱት።ዛሬ በሚዛን ብትመዘን የብር ተመን አትሆንም ካንድ ዓመት በኃላ ግን ከሺህ ቶን ፈረሱላ እርሳስ ይልቅ ትከብዳለች። >>

... ይህ ደብዳቤ እንደ ደረሳቸው ምኒሊክ አንቶኔን አስጠርተው እንደገና ጠየቁት።
አሁንም ግልፅ ባልሆነ አነጋገር አጭበረበራቸው። እንዲህም አለ << ታዲያ ይህ ምን ክፋት አለበት (17ኛው ክፍል) እኛ የርስዎ አሽከርዎ ፖስተኛ መሆናችን ነው እንጂ።>>... | አለቃ አፅመ ጊዮርጊስ የኦሮሞ ህዝብ ታሪክ (ያልታተመ)|

....... የውሉ ዋና ፀሀፊ ፒዬትሮ አንቶኔሊ ከአፄ ምሊኒክ ከእቴጌ ጣይቱና ከመኳንንቱ ፊት ቀርቦ ይህን የውጫሌ ውል እምቢ ካሉ ጦርነት መነሳቱን እንዲያውቁት ያስፈልጋል ብሎ ሲደነፋ እቴጌ ጣይቱ ደግሞ እጥፍ ጊዜ ቱግ ብለው ተቆጡና፤
" የዛሬ ሳምንት አድርገው። በዚህ የሚደነግጥልህ የለም ሂድ የፎከርክበትን አድርግ። እኛም የመጣውን እናነሰዋለን። እግሩን ለጠጠር ደረቱን ለጦር ሰጥቶ አገሩን የማያድን ሰው በዚህ የሌለ አይምሰልህ።
የገዛ ደሙን ገብሮ ለገዛ አገሩ መሞት ጌጥ ነው እንጂ ሞት አይባልም። አሁንም ሂድ አይምሽብህ የፎከርክበትን በፈቀደህ ጊዜ አድርገው። እኛም እዚህ እንቆይሃለን።.....
እኛ ለራሳችን እንበቃለን የሀገራችንንም ክብር እንጠብቃለን። አንፈራችሁም! በፈቀድነው ጊዜ ከመሬታችን ከሀገራችን ተራራ እንደ ድንጋይ እንፈነቅላችኃለን።" አሉት።

እርሱም ከአዳራሹ ሊወጣ ከሞከረ በኃላ እንደገና መለስ ብሎ
"የምንገጥመውኮ ጦርነት ነው፤ ወንዶቹስ በሆነላቸው እንኳን ሴቲቱ" አላቸው።
"የእኔ ሴትነትና ያንተ ወንድነት የሚለካው እዚያው ጦር ሜዳ ነውና እንዳትቀር።"ብለው መለሱለት።
እንግዲህ የአጭቤው(አጭበርባሪው)አንቶኔሊ አንቶዬ(ስምህን ቄስ ይጥራው አንተ ሰላቢ ለነገሩ.... )
በንቀት እና በወኔ ሙላት የተመላለሱትን ቃለ ምልልስ አይተናል።

የጣይቱን ፉከራ በጦርነቱ ውስጥ በሰራችው ገድል የምናውቀው ነው መቼስ።
ያው ዘመን እየመጣ ዘመን በሄደ ቁጥር እነእቴጌን መሰል ሴቶችን ማጣት የሀገር ህመም ነው። መቼስ ዘንድሮ እንደሆነ ፎክረውና ብልሃት ምሰው ከሚያሸንፉ ይልቅ ቁራጭ ጨርቅ በላያቸው ላይ ለጥፈው ወንዱን እያፈዘዙ አንዴ ከቆመ ዛፍና መኪና ጋር እያጋጩ አንዴ ቦይ ውስጥ እየከተቱ ሆኗል ብልሃቱ። (ቱ ደሞኮ እኛኑ ነው )
እኔስ ስንቴ ነው አንገቴን እስኪያመኝ እየሾፍኩ ቆሎ በትኜ ጣቢያ ያደርኩት " መገን" አለ ወሎ።

የአንቶኔሊን ንቀት ታክል በዘመኔ ላይ መማረር ቢኖርብኝም ይሁን ይመቻቸው ብያለሁ።
የዚህችን ክፍል መዝጊያ ከመፅሀፉ ውስጥ ባገኘዋት ፈገግ በምታስብል ገጠመኝ ልዝጋና በቀጣዩ ቀን በሌላ ክፍል ልመለስ....

...... አንቶኔሊ ከስብሰባው ሲወጣ ምኒልክ ለጋሲዮን ድረስ የሚሄድበት በቅሎ ስጡት ብለው ተሰጠው። አንቶኔሊ በቅሎ ለሰጠው አሽከር አንድ መቶ ብር ሰጠ።
አሽከሩም የተሰጠውን ብር ይዞ አዳራሽ ገብቶ ለምኒልክ ነገረ።
ራስ መኮንን ነበሩና " ጉርሻ ከሆነ ይበዛል። ጃንሆይ ለሰጡት በቅሎ ከሆነም ያንሳልና ይመለስ!" አሉ። ምኒልክም ስቀው ለአሽከሩ "ጉርሻ ነውና ውሰደው" አሉት።

........... ዛሬ የአድዋን ድል መዳረሻ ቀናት አስመልክቼ በቅንጭብ ያቀረብኩት ክፍል ይህን ይመስላል በቀጣይ አንዳንድ የጦርነቱን ነጥቦች እናያለን ሀሳብ አስታየታችሁን ፃፉልኝ።
የተሳሳትኩትም ካለ አርሙኝ ያጠፋሁትም ካለ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

ለዚህ ፅሁፌ በዋነኝነት ኃብረ ኢትዮጵያ በሚል ርዕስ በ2008 ዓ.ም በቴዎድሮስ በየነ የታተመውን ቅፅ አንድን ተጠቅሜያለሁ።
ቸር ቆይታ!!!
- ለማድብን እጅጉ ( ቃሲም )
- ለበፍቃዱ አረጋ
#እና
- ለቃለአብ ሲሳይ (ናታኒም)
ምስጋናዬ ይድረስልኝ
#ሲራክ ወንድሙ @siraaq
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
1.1K viewsC-ራክ, 12:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-18 08:57:23
እንኳን ለጌታችን እና ለ መድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በአል በሰላም አደረሳችሁ !

#ያ_ጋ_ሩ
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
937 viewsᴛʜᴇᴏᴛᴏᴋᴏs, 05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-07 00:09:26 "ፍሥሐ ለኩሉ ዓለም ተወልደ ለነ ክርስቶስ"
(ቅዱስ ያሬድ)
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
1.9K viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 21:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ