Get Mystery Box with random crypto!

ታሪካችንን እንወቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tarikacheninenwoke — ታሪካችንን እንወቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ tarikacheninenwoke — ታሪካችንን እንወቅ
የሰርጥ አድራሻ: @tarikacheninenwoke
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 453
የሰርጥ መግለጫ

ይህ Channel ቀደምት የኢትዮጲያዊያንን ታሪክ የሚዘክር ታሪክ የሚያስተምር እና የተለያዩ በኢትዩጲያዊያን የተፃፉ የስነ-ፁሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ነው ። በድጋሚ ኢትዮጵያን እንወቅ !

አስታየት ጥቆማ ካላችሁ @Kalowohaset ያናግሩኝ

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2020-12-14 20:13:28 ስንጠብቀው የነበረው ዘጋቢ ፊልም እንሆ.....
በስተመጨረሻም ከብዙ ጊዚያት በኋላ አየር ላይ ውሏል።

ስለ ነገር ያልገባችሁ ካላችሁ ከላይ reply ያረኩትን መልዕክት አንብቡት....

#ጥንታዊነት_የዘመኑ_ፋሽን_ነው!

#T_H_E_O_T_O_K_O_S


@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
1.1K viewsᴛʜᴇᴏᴛᴏᴋᴏs, 17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-21 17:42:51
« ስለ ኢትዮጵያ ሳስብ አልደነግጥም መቼም አልደነግጥም የቆምኩበትን የአባቶቼን መሠረት አውቀዋለሁ። ኢትዮጵያ ባንተ አልተጀመረችም ባንተም አትፈርስም!!! »


ፕሮፌሰር ሀይሌ ገሪማ ከ2 ዓመት በፊት የተናገሩት ዘመን ተሻጋሪ ንግግር!

THEOTOKOS

@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
1.1K viewsᴛʜᴇᴏᴛᴏᴋᴏs, 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-08 22:58:14 #በእንግሊዝኛ #የተቀየሩ #የግዕዝ #ስያሜዎች፦

ተ.ቁ በእንግሊዝኛ በግዕዝ
=== ======= ========
1. ቴሌስኮፖ መቅረበ ኮከብ
2. ኮፓውንድ ውህድ
3. ግራቪቲ ስብህተ-ምድር
4. አይዶሎጂ ርዕዮተ-ዓለም
5. ኢቫፖሬሽን ተን
6. ሜርኩሪ አጣርድ
7. ቬነስ ዙሕራ
8. ማርስ መሪሕ
9. ጁፒተር መሽተሪ
10. ስተርን ዙሐል
11. ኮንስታሌሽን ህብራተ ከዋክብት
12. ጋላክሲ ክምቸተ ከዋክብት
13. ስቴላር ሲስተም ስርዓተ-ኮከብ
14. ሶላር ሲስተም ስርዓተ-ፀሐይ
15. ሳይረስ ደማቋ ኮኮብ
16. ኮሌጅ መካነ ትምህርት
17. ዩኒቨርስቲ መካነ አምሮ
18. ሌክቸር ትምህርተ ጉባኤ
19. ሌክተቸረር መምህረ ጉባኤ
20. ዲን ሊቀ ጉባኤ
24. ቢሮ መስሪያ ቤት
25. ባንክ ቤተ ንዋይ
26. ሲቪል ሰርቪስ ሰላማዊ አገልግሎት
27. ኮምፒተር መቀመሪያ
29. ድግሪ ማዕረግ
30. ሚኒስተር ምሉክ
31. ማስ ሚዲያ ምህዋረ ዜና
32. ፎቶ ግራፍ ብራናዊ ስዕል
33. ራዲዮ ንፈሰ ድምፅ
34. ፖሊስ የህግ ዘበኛ
35. ኢንተርኔት የህዋ አውታር
36. ሎሬት አምበል፥ተሸላሚ የቅኔ
37. ዶክተር ሊቀ ሙህር
38. ኢምባሲ የእንደራሲ ፅ/ቤት
39. ዲፕሎማት መንግስት መልክተኞች
40. ኢኮኖሚክስ ስነ ብዕል
41. ሀዋላ ምህዋረ ንዋይ
41. ሳሎን እንግዳ መቀበያ
42. ቱሪዝም ስነ ህዋፄ
43. ስካን ምክታብ
44. ፕሬዝዳንት ሊቀ ሀገር/ ሙሴ
45. ቴሌኮሚኒኬሽን ምህዋረ ቃል
49 . ቪዛ የይለፍ ፍቃድ
50. ፓስፖርት የኬላ ማለፊያ

THEOTOKOS

@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
2.5K viewsᴛʜᴇᴏᴛᴏᴋᴏs, 19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-06 14:14:19
883 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-06 14:14:19
796 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-06 14:14:19
741 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-06 14:14:19
691 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-06 14:14:19
670 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-06 14:14:19 በኢትዮጵያ፣ ዛሬም ውቅር አብያተ ክርስቲያን ከወጥ አለት ተፈልፍለው እየታነፁ ነው – ቢቢሲ
ላሊበላን የመሰሉ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያውያን እየተደገሙ ነው፤
በሰ/ወሎ ዋድላ ወረዳ፣ አራት ውቅር መቅደሶች ከወጥ አለት ተፈልፍለው ታነፁ፤
ሐናፂው፣ ዘመናዊ መሣሪያ አይጠቀሙም፤የምሕንድስና ትምህርትም የላቸውም፤
“ጥበቡ የፈጣሪ ነው፤እኔ የእርሱ መሣሪያ ነኝ፤”/ሐናፂው አባ ገ/መስቀል ተሰማ/
“ከ800 ዓመት በፊት የሠሩትን ታሪክ በራሳቸው እጅ ደግመውታል፤” /ቢቢሲ/
†††
ከአንድ ወጥ አለት ተፈልፍለው የተሠሩት የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን፣ በኢትዮጵያም ኾነ በዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ዘንድ በታሪካዊነታቸው ጎልተው ይታወቃሉ፡፡ አብያተ ክርስቲያኑ፣ በጠቢባን እጆች የተሠሩት ወይም የተፈለፈሉት፣ በ12ኛው ክፍለ ዘመን ነው፡፡ ይኹንና የእኒያ ጠቢባን እጆች ሥራቸውን ቀጥለውበታል፤ ዛሬም፣ ዐዲስ አብያተ ክርስቲያን በሀገራችን ጠቢባን እጅ እየተፈለፈሉ ናቸው፡፡
አባ ገብረ መስቀል ተሰማ ይባላሉ፤ ዐዲስ ሕንፃ አብያተ ክርስቲያን ከወጥ አለት በመፈልፈል ጥበብ የተካኑ ናቸው፡፡ አብያተ ክርስቲያኑን ፈልፍለው ለመጨረስ አራት ዓመት ፈጅቶባቸውል፡፡ ሥነ ሕንፃውም፣ እርሳቸው ምን ያህል በጥበብ የተሞሉ መኾናቸውን ያሳያል፡፡
“ኢትዮጵያውያን በዚያ ጥንት ዘመን ዘመናዊ መሣሪያ ሳይታጠቁ እንዴት ላሊበላን ያህል ቤተ መቅደስ ከአለት ወቅረው ቤተ ክርስቲያን ይሠራሉ?” የሚል ጥያቄ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ሲነሣ ቆይቷል፤ ጥያቄውን ይዘው፣ “የጥበቡ ባለቤት ሌላ ነው፤ ከሀገሪቱም ውጭ ነው፤” ወደ ማለት ያመሩ አሉ፤ “የሚሠሩም ከኾነ እስኪ ይድገሙት፤” ያሉም አልጠፉም፡፡
ዓለም አቀፍ ሚዲያ የኾነው ቢቢሲ፣ “በዩኔስኮ የተመዘገቡ የቅርስ ሥፍራዎችና የብዙኃን ጎብኚዎች መዳረሻ የኾኑት ኢትዮጵያውያን፣ ከ800 ዓመት በፊት የሠሩትን ታሪክ በራሳቸው እጅ ደግመውታል፤” የሚል ሐሳብ ያለውን ዘገባ አውጥቷል፡
“ዳግማዊ ላሊበላ” የሚል ስያሜ የተሰጣቸው አብያተ ክርስቲያኑ፣ በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ ከጋሸና ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ ለላሊበላ ከተማ ቀረብ ባለ ሥፍራ ነው እየታነፁ ያሉት፡፡ ቢቢሲ ታዲያ፣ “በጥልቀትም ኾነ በጥበብ መገለጫ የሌላቸው ላሊበላን የመሰሉ ውቅር አብያተ ክርስቲያን በኢትዮጵያውያን እየተደገሙ ነው፤” የሚል መረጃ ይፋ አድርጓል፡፡
“ጥበቡ የፈጣሪ ነው፤ እኔ የእርሱ መሣሪያ ነኝ፤” የሚሉት አባ ገብረ መስቀል ተሰማ፣ ቤተ መቅደሱን በመሥራት ላይ ናቸው፡፡ “ፈቃዱ ከእግዚአብሔር ነው፤ ሃይማኖታዊና አገራዊ ፋይዳ አለው፤ እንደ ሃይማኖታዊነቱ፣ ጥንቱንም የቅዱስ ላሊበላ ቦታ ነው፤ በግራኝ አሕመድ ወረራ ጊዜ ላዩ ጠፍቶ ስለነበር እርሱን ለመመለስ ነው፤” በማለት ያስረዳሉ፡፡
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ወደ ኢትዮጵያ ከሚመጡ ጎብኚዎች 90 በመቶዎቹ ፍላጎታቸው ላሊበላን መጎብኘት ነው፡፡ በአቅራቢው ሌላ ከአለት የተወቀረና የተፈለፈለ ጥበብ መፈጠሩ፣ ሌላ ዕድል ሌላ ገቢ ይዞ እንደሚመጣ፣ ተጨማሪ በርካታ ቱሪስቶችንም እንደሚስብ ይጠበቃል፡፡
አባ ገብረ መስቀል እስከ አኹን፣ አራት ፍልፍል አብያተ መቅደስን ከወጥ አለት አንፀው ጨርሰዋል፤ ሌሎችንም በማነፅ ላይ ናቸው፡፡ በሥራቸው ግን፣ ዘመናዊ መሣሪያን አይጠቀሙም፤ የምሕንድስና ትምህርትም አያውቁም፤ ግን ሠርተውታል፡፡ እኔ ለማመን እስኪከብደኝ ድረስ ነዉ የገረመኝ ግን እውነት ነው እስኪ እናንተም አይታችሁ ተገረሙ ፡፡
737 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-10-29 08:06:39 ለመላው የእስልምና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን፤
ለነብዩ መሐመድ ልደት (መውሊድ) እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል!

@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
811 viewsናታኒም የ እንቅዮጳዝዮን ልጅ, 05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ