Get Mystery Box with random crypto!

#ህፃኑ ሲጠይቅ «ስሚኝ እናት አለም !» «እሺ ምንድነው የኔ አለም ?» «ያቺ ነገር ምንድናት | ታሪካችንን እንወቅ

#ህፃኑ ሲጠይቅ

«ስሚኝ እናት አለም !»
«እሺ ምንድነው የኔ አለም ?»
«ያቺ ነገር ምንድናት ?»
«የት አለች?የት ነው ያየሃት?»
ሕፃኑም ዘረጋ እና እጆቹን ወደ ሰማይ !
ጨረቃዋን አሳያት ስታበራ አናታቸው ላይ !
«እሷማ ጨረቃ ናት !»
ብላ መለሰች እናት ።
«ጨረቃ ማለት ምንድነው ?»
«ይሄ ልጅ ምንድነው የሚለው ?»
«እናት አለም ጨረቃን አንቺም አታውቂያት ?»
« እንግዲህ አታስቸግረኝ ጨረቃ ጨረቃ ናት ።»
«ጨረቃስ እሺ ትሁን ታዲያ ተዚያ ላይ ማን ሰቀላት?»
«እግዚሐር ነው የፍጠራት ።»
« እግዚአብሄር ማለት ምንድነው ?»
«ይህ ልጅ ምንድነው የሚለው ?»
እግዚሐር ማለት ሰሪ ነው አንተን እኔን የሰራ ፤
ጨረቃንም የፈጠራት በለሊት እንድታበራ !»
«እኔን የሰራ እግዚሐር ነው ?»
«አዎን የሰራህ እግዚሐር ነው !»
«ታዲ አንቺ ምንድኔ ነሽ እናት አለም !»
«እንዴት አድርገሽ ወለድሺኝ ?»
«ውልድ ! አድርጌ ነዋ በቃ እንግዲህ አታድርቀኝ !»
«ምንድነው እናት አለሜ ስጠይቅሽ ምትቆጪኝ !»
«እሺ የኔ አለም ጠይቀኝ ! »
«እንዴት አድርገሽ ነው የወለድሽኝ ?»
«አንተ ልጅ ዝም በል ብያለሁ !
እራስህ አድገህ ድረስበት ፤
አሁን እኔ ስራ ልስራበት !»


አቤ ጉበኛ
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke
@tarikacheninenwoke