2022-07-04 16:54:48
በዚህ በክረምት ወራት እንዴት መጠበቅ አለብን?
በክረምት ወራት ጤናችንን ለመጠበቅና የበሽታ መከላከል አቅማችንን ለማሳደግ ማድረግ ከሚገቡን ነገሮች
1. ቫይታሚን ሲ አብዝተን መመገብ፦ የዝናብ ወራት ለባክቴሪያዎችና ቫይረሶች መራባት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።ይህም ጉንፋንን ጨምሮ ሌሎች ህመሞች ስለሚበዙ የበሽታ መከላከል አቅማችንን ለማሳደግ የቫይታሚን ሲ አወሳሰድዎን ይጨምሩ
2. ንፁህ ዉሃ መጠጣት፦ ብዙዎቻችን በዝናብ ወቅት በዙ ዉሃ ላንጠጣ እንችላለን። ሰዉነታችን ደግም ጤነኛ ሆኖ ለመቀጠል ዉሃ በበቂ መጠን ማግኘት አለበት። ሰለሆነም የሚጠጡት ዉሃ ንፁህ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
3. እንቅልፍ በበቂ መጠን መተኛት፦ በቀን ከ 7-8 ሰዓታት እቅልፍ መተኛት የሰዉነት የበሽታ መከላከል አቅምን ያጎለብታል። ይህም በክራምት ወራት በብዛት ሊከሰቱ የሚችሉ እንደ ጉንፋን ያሉ ህመሞችን ለመቀነስ ይረዳል።
4. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፦ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ክብዳት ለመቀነስና የሰዉነትን አቋም ለማስተካከል ብቻ ሳይሆን የሚረዳዉ የበሽታ መከላከል አቅማችንንም ለማጎልበት ይረዳል።
5. የእጅ ንፅህናን መጠበቅ፦ እንደሚታወቀዉ በዝናብ ወራት ጎጂ የሆኑ ጀርሞች ቁጥር እየሰፋ ይሄዳል። ስለዚህ የእጅ ንፅህናን በጥሩ ሁኔታ መጠበቅ በእጅዎ ቆዳ ላይ ሊኖሩ የሚችሉትን ተዋሲያኖችን በሙሉ ማለት ይቻላል ይገድላል።ስለሆነም ከመመገብዎ በፊት እጅዎን መታጠብ ወይንም በሳኒታይዘር ማፅዳት ያስፈልጋል።
6. ከአለርጂኖች ይጠበቁ፦ በክረምት ወራት አለርጂኖች በከፍተኛ መጠን ይጨምራሉ። ሰለሆነም ለመጥፎ ሽታ ሰዉነትዎ የሚኖረዉ ምላሽ ያልተገባ ከሆነ ከቤት ሲወጡ የአፍ መሸፈኛ( ማስክ) ያድርጉ።
7. ከታመሙ ሰዎች ያለዎትን ርቀት መጠበቅ፦ ጉንፋንና ሌሎች ተላላፊ ህመሞች በክረምት ወራት ስለሚጨምሩና ብዙ ሰዎች በጉንፋን ስለሚጠቁ ከታመሙ ሰዎች ያለዎትን ርቀት ይጠብቁ።
8. የወባ መራቢያ ቦታዎችን ማጥፋት፦ በዝናብ ወቅት ከሚከሰተው አስከፊ ችግር አንዱ የወባ ትንኞች መራባት ነው። ይህም ያቆሩ የዉሃ ጉድጓዶች፣ በቤት ዉስጥ ክፍት የዉሃ ማጠራቀሚያ እንዳይኖር ማድራግ። ትንኞች የሚራቡት በረጋ ውሃ ውስጥ ነው፤ ስለዚህ መሰል ውሃን የሚያቆሩ ምንጮችን ማስወገድ በጣም ይረዳል.
9. የሚቻል ከሆነ ልብስዎ ከታጠበ በኃላ ቢተኮሱ፦ በክረምት ወራት ሞልድ( ሻጋታ) በብዛት ይከሰታል። በክረምት ወራት ፀሃይ አንደልብ ስለሌ ልብስ ቢተኮስ ይመረጣል።
ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!
650 viewsAddis Kasiye, edited 13:54