Get Mystery Box with random crypto!

St. Urael Internal Medicine Clinic

የቴሌግራም ቻናል አርማ sturaelclinic — St. Urael Internal Medicine Clinic S
የቴሌግራም ቻናል አርማ sturaelclinic — St. Urael Internal Medicine Clinic
የሰርጥ አድራሻ: @sturaelclinic
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.08K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቅዱስ ኡራኤል የዉስጥ ደዌ ስፔሺያሊቲ ክሊኒክ ቻናል ነዉ።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ፣ከ ቦሌ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደዉ መንገድ ላይ ሩዋንዳ ኤምባሲ አጠገብ እንገኛለን።
ስልክ፡- 9424 ወይም
በ 0940464646 / 0940565656

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-05-25 15:02:37 አራት (4) ከምግብ ዉጪ የደም ስኳር መጠንዎን ሊጨምሩ/ሊያዛቡ የሚችሉ ነገሮች
1. ጭንቀት
2. የእንቅልፍ እጦት
3. የወር አበባ ዑደት
4. የፈሳሽ እጥረት


በየቀኑ ለጤናዎ ጠቃሚ የሆኑ ተከታታይ የጤና መረጃዎችን ለማግኘት የFacebook ገፃችንን Like እና Follow ማድረጎን እንዳዘነጉ።

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!
894 viewsAddis Kasiye, edited  12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 08:54:07
የእግር ሽታ

የእግር ሽታ ያስቸግሮታል? አንግዲያዉስ የሚከተሉትን ይተግብሩ!
ሁሌም እግሮችዎና የእግሮችዎ ጣቶች ዉስጥ ንፁህና ደረቅ ይሁኑ።

መተግባር የሚገባዎ
እግርዎን ቢያንስ በቀን አንዴ መታጠብ ( ከተቻለ ፀረ- ባክቲሪያ የሆኑ ሳሙናዎችን ይጠቀሙ)
እግርዎ ላይ ደረቅ ቆዳዎች ካሉ ያስወግዱ እንዲሁም የእግር ጥፍርዎን ያሳጥሩ፥ በንፅህናዉንም ይጠብቁ
የእግር ላብ መቀነሻ ፓዉደሮችን አሊያም መድሃኒቶችን ይጠቀሙ
የረጠበ ጫማ ካለዎ መልሰዉ ከማድረግዎ በፊት መድረቁን ያረጋግጡ
አየር በቀላሉ ሊያዘዋዉሩ የሚችሉ ጫማዎችን ይጫሙ፤ እንዲሁም ከተፈጥሮ ነገሮች እንደ ከጥጥ ወይም ቆዳ የተሰሩ መጫሚያዎችን ይምረጡ።

ማድረግ የለለብዎ
በጣም ጠባብ ጫማዎችን አያድርጉ
እርጥበት ባለባቸዉ ቦታዎች ለምሳሌ በመዋኛ ና ጂም ቦታዎች ባሉ ሻወር ቤቶች አካባቢ በባዶ እግር አይጓዙ
የእግር ካልሲ በተከታታይ ከሁላት ቀናት በላይ አያድርጉ፤ ከተቻለም ጫማዎችንም በየሁለት ቀኑ ለመቀያየር ይሞክሩ።
የአግር ሽታ እንዲከሰት የሚያደርጉ መንስኤዎች
ለእግር ጠረን መከሰት ዋነኛ መንስኤዎች የእግር ላብና በእግርዎ ላይ ባክቴሪያ መከማቸት እንዲሁም እንደ አትሌቲክ- ፉት ያሉ የፈንገስ በሽታዎች ናቸው።

የእግርዎ የላብ መጠን ሊወስኑ የሚችሉ ነገሮች
ሞቃት የአየር ፀባይ
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
ቀኑን በሙሉ ቆሞ መዋል
የሰዉነትዎ ክብደት ከፍተኛ መሆን
የሆርሞን ለዉጦች፦ በጉርምስና፣ በማረጥና በእርግዝና ወቅት የሚከሰቱ
መድሃኒቶች፦ ልድብታ የሚሰጡ
ከመጠን ያለፈ የሰዉነት ላብ እንዲፈጠር የሚያደርጉ ችግሮች ናቸዉ።

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
1.2K viewsAddis Kasiye, edited  05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-07 20:33:28
የኩላሊት መድከም የህመም ምልክቶች

ክፍል ሁለት
ኩላሊትዎ ስራቸዉን በኣግባቡ የማይከዉኑ ከሆነ የሚከተሉት የህመም ምልክቶች ሊታዩ ይችላሉ። ከነዚህም ዉስጥ

የሽንት መጠን መቀነስ ምንም እንኳ አንድ አንድ ጊዜ ኖርማል ቢሆንም
የትንፋሽ ማጠር
የልብ ምት መዛባት
የደረት ላይ ህመም
ህመሙ አየከፋ ሲመጣ እንደሚጥለዉ ሰዉ ማንቀጥቀጥ
የሰዉነት ድካም( ከመጠን ያለፈ )
ማቅለሽለሽና ማስታወክ
ትኩረት ማጣትና መቀባዥር
የሰዉነት ላይ እብጠት
የጡንቻ መኮማትወር( ህመም)
የቆዳ ድርቀት ወይም ማሳከክ
የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም የምግብ ብረት ብረት ማለት

ለኩላሊት መድካም አጋላጭ ነገሮች ምንድን ናቸዉ?

የስኳር ህመም
የሁላሊት ህመም
የደም ግፊት
የልብ ህመም
የደም ቧንቧዎች መዘጋት
ሰር ለሰደደ የጤና ችግር ሆስፒታል መተኛት
የጉበት መድከም
የካንሰር ህመምና ህክምናቸዉ ናቸዉ።

የኩላሊት መድካም ሊያመጣቸው የሚችላቸዉ የጎንዮሽ ጉዳቶች

የሰዉነት እብጠት፦ ድንገተኛ የኩላሊት መድከም ሲኖር ሰዉነታችን ዉስጥ ፈሳሽ አንዲጠራቀም ያደርጋል( ለምሳሌ ሳንባችን ዉስጥ--ይህ የትንፋሽ ማጠር ስሜት እንዲከሰት ያደርጋል።)
የደረት ህመም፦ የልብ ሽፋን እንዲቆጣ ስለሚያደርግ የደረት ላይ ህመም ይከሰታል።
ይጡንቻ መድከም፦ የሰዉነታችን ፈሳሸና አሌክትሮላይት ምጣኔ መዛባት መፈጠር ለመሰል ችግር ይዳርገናል።

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
1.1K viewsAddis Kasiye, edited  17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-04 15:30:41
የኩላሊት መድከም

ክፍል አንድ
የኩላሊት መድከም ማለት አንዱ ወይም ሁለቱም ኩላሊትዎ የሚከዉኑትን አገለግሎት በራሳቸዉ መሥራት የማይችሉበት ደረጃ ወይም ሁኔታ ላይ ሲደርሱ የሚከሰት ችግር ነዉ።

የኩላሊት ስራ ምንድነዉ?

ኩላሊቶች ብዙ አገልግሎት ይሰጣሉ። በጣም አስፈላጊ ከሆኑት የኩላሊት ስራዎች ውስጥ አንዱና ዋነኛዉ ሰውነትዎ መርዛማ ነገሮችን ከሰዉነትዎ ለማስወገድ መርዳት ነው። ኩላሊት ደምን በማጣራት ቆሻሻ ነገሮችን በሽንት ዉስጥ እንዲወገድ ያደርጋሉ። ሰዎች ግራና ቀኝ በሽንጥዎ አካባቢ የሚገኙ ሁለት ኩላሊቶች አላቸዉ። ነገር ግን ቢያንስ አንዱ ኩላሊት በደንብና በትክክል እስከሰራ ድረስ ሰዎች በአንድ ኩላሊት በደንብ ሊኖሩ ይችላሉ።

ኩላሊት ስራዋን በደንብ የማትከዉን ከሆነ ከሰዉነታችን መወገድ የነበረባቸዉ ቆሻሻዎች በሰውነትዎ ዉስጥ ይጠራቀማል። ይህም ችግር ከፍ ያለ ከሆነ ልህይወትዎ አስጊ ሊሆን ይችላል።

ለኩላሊት መድከም መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉ ነገሮች ምንድናቸዉ?

በጣም ከተለመዱት የኩላሊት መድከም መንስኤዎች ዉስጥ የስኳር በሽታና የደም ግፊት ዋነኛዎቹ ናቸዉ።አንዳንዴ ምክንያቱ ባልተለየ ምክንያት ድንገተኛ የኩላሊት መድከም ሊከሰት ይችላል።

የኩላሊት በድንገት መድከም ( በሰዓተትና በቀናት ዉስጥ) ከተከሰተ ድንገተኛ የኩላሊት መድከም ችግር ተከሰት እንላልን። ይህ አይነቱ የኩላሊት መድከም ችግር ጊዜያዊ ሲሆን ለዚድንገተኛ ኩላሊት መድከም ችግር ሊዳርጉ ከሚችሉ ነገሮች ዉስጥ ጥቂቶቹ፦

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/

አድራሻችን፦ ቦሌ ሩዋንዳ ከሩዋንዳ ኤምባሲ ጎን።
897 viewsAddis Kasiye, edited  12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ