Get Mystery Box with random crypto!

እድሜዎ ከ50 ዓመት በላይ ነዉን? ወይም ዕድሜያቸዉ ከ50 አመት በላይ የሆነ የቤተሰብ አባል አለዎ | St. Urael Internal Medicine Clinic

እድሜዎ ከ50 ዓመት በላይ ነዉን? ወይም ዕድሜያቸዉ ከ50 አመት በላይ የሆነ የቤተሰብ አባል አለዎ?

እንግዲያዉስ እድሜ በመግፋቱ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮች ስላሉ መደበኛ የጤና ክትትል ማድረግን እንዳይረሱ።
ከ10 አረጋውያን ከዘጠኝ በላይ የሚሆኑት አንዳንድ ሥር የሰደዱ በሽታዎች ያለባቸው ሲሆን ከ 10 ውስጥ ስምንት የሚሆኑት ከአንድ በላይ የሆነ ስር የሰደደ ህመም ሊኖራቸዉ ይችላል።
ጤናማ ህይወት አንዲኖርዎ የሚከተሉትን ይተግብሩ
1. የደም ግፊት ክትትል
እድሜዎ በገፋ ቁጥር የደም ቧንቧዎች ስለሚጠነክሩና የመተጣጠፍ እድላቸዉ ስለሚቀንስ የደም ግፊት የመከሰት እድሉ ይጨምራል።
2. ስኳር
እድሜ በጨመረ ቁጥር በስኳር ህመም የመያዝ እድልዎ ይጨምራል። የስኳር ህመም ደግሞ ለኩላሊት፣ ለልብ፣ለአይነስዉርነትና ለሌሎች የጤና ችግሮች የመጋለት እድልን ይጨምራል።ስለሆነም የደም የስኳር መጠንዎን በየግዜዉ ይመርመሩ።
3. የልብ ህመም
እድሜያችን ሲጨምር በደም ቅዳ የደም ቧንቧዎች ዉስጥ የስብ መርጋት ይፈጠራል። ይህም ለልብ ችግሮች የመጋለት እድል ስለሚጨምር የልብ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።
4. የሰዉነት ዉፍረት
የሰዉነት ዉፍረት መጨመር ለልብ፣ለስትሮክ፣ ለስኳር፣ለካንሰር፣ ለደም ግፊት መጨመር፣ለመገጣተሚያ ህመምና ለሌሎች ህመሞች የመጋለትን እድል ይጨምራል።
5. የመገጣጠሚያዎች ህመም( ኦስቲዮአርትራይቲስ)
የእድሜ መጨመር የመገጣጠሚያዎች መላሸቅ እንዲከሰት ያደርጋል።

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!