Get Mystery Box with random crypto!

ድንገተኛ የጉበት መድከም ድንገተኛ የጉበት መድከም ማለት ጉበት በቀናት ወይም ሳምንታት ዉስጥ ለሰ | St. Urael Internal Medicine Clinic

ድንገተኛ የጉበት መድከም

ድንገተኛ የጉበት መድከም ማለት ጉበት በቀናት ወይም ሳምንታት ዉስጥ ለሰዉነታችን የሚሰጠዉን አገልግሎት በሚያጣበት ወቀት የሚከሰት ነዉ። ይህ ችግር በብዛት በጉባት ቫይረስ ኢንፌክሽን ወይም በመድሃኒቶች አማካኝነት ይከሰታል። ድንገተኛ የጉበት መድከም ከፍተኛ የደም መፍሰስ እና በአንጎል ውስጥ ግፊት መጨመርን ጨምሮ ከባድ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል።

የህመም ምልክቶች
· የአይን ነጩ ክፍልና የቆዳ ቢጫ መሆን
· በቀኝ የላይኛዉ የሆድዎ ክፍል ህመም መሰማት
· የሆድ ማበጥ(ዉሃ መያዝ)
· ማቅላሽለሽ
· ማስታወክ
· በአጠቃላይ የጤንነት ስሜት ያለመሰማት(የህመም ስሜት መኖር)
· ግራ መጋባት ወይም መቀባዠር ስሜቶች
· አንቅልፍ ማጣት
· የእጅ ማንቀጥቀጥ ስሜት ናቸዉ።

ድንገተኛ የጉበት መድከም የሚከሰተው የጉበት ሴሎች በከፍተኛ ሁኔታ ሲጎዱና መሥራት ሲያቅታቸው ነው። ከተለመዱት መንስኤዎች ዉስጥ

· ፓራሲታሞል( አሴታሚኖፌን) ከመጠን በላይ መዉሰድ፦ በጣም ብዙ አሲታሚኖፌን (Tylenolና , ሌሎችም) መውሰድ በጣም የተለመደው የጉበት መድከም መንስኤ ነው።

· ባህላዊ መድሃኒቶች፦
· ቶክሲኖች
· በጉበት ዉስጥ ያሉ የደም መልስ የደምቧዎች ህመም
· ካንሰር ህመም
· የደም ግፊት መቀነስ( ሾክ)

ለበለጠ ንባብ የ Facebook ገጻችንን ከታች ባለው Link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
https://www.facebook.com/sturaelclinic/
እናመሰግናለን!!!