Get Mystery Box with random crypto!

Seid Social

የቴሌግራም ቻናል አርማ seidsocial — Seid Social S
የቴሌግራም ቻናል አርማ seidsocial — Seid Social
የሰርጥ አድራሻ: @seidsocial
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.83K
የሰርጥ መግለጫ

አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-07 18:22:15
ሰውየው በሞቻችን አሹፏል ። " ሰው ቢሞትም ዛፍ መትከላችንን እንቀጥላለን ምክንያቱም አስክሬኑ ጥላ እንዲያገኝ " በማለት ለገዳዮች አረንጓደ መብራት አብርቶላቸዋል ። እንደዚህ አይነት ብልግና የተናገረ መሪ አይችቼም ሰምቼም አላውቅም !

ከዚህ በሗላ ምን እንጠብቃለን ?! ከዚህስ በላይ ምን ይመጣብናል ?!
በቀን ሺዎች እያለቁ እርሱ በሟቾች ከተሳለቀ ታዲያ የግድያው ባለቤት እርሱስ አለመሆኑን እንደት እርግጠኛ እንሆናለን !?
2.0K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 13:14:00
እርሱ የተረት አባት አውርቶ የሚያስቅ ነገሮ - የሚያዝናናቸው
እነርሱ ህፃናት ከማጨብጨብ በቀር ሚና
- የሌላቸው

ከፊሉ አስገዳይ ሀገርን ለማፍረስ ቀን ሌት የሚሰራ
ነፍጠኛን ቀበርኩት ሰበርኩት እያለ ህፃናትን ገድሎ - ፎክሮ ሚያቅራራ

በእንድህ አይነት መንግስት ሀገር ከተመራች
የሰው ቄራ ሆና ፈራረሰች እንጅ ምኑን በለገፀገች

Seid Mohammed Alhabeshiy
2.0K views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 11:19:23
ጠቅላይ ሚኒስትሩኮ ፓርላማ መሰብሰብ ሌላ ዝብዘባ መስጠት አይጠበቅበትም
የ ዶክተር ሀንጋሳ አህመድን ጥያቄ ብቻ ከመለሰ የእውነት እርሱ ብቻ በቂ ነው ። ሀንጋሳ የመላ ኢትዮጵያንን ጥያቄ አንዷን እንኳ ሳያስቀር አቅርቦለታል ። ለሀንጋሳ ትክክለኛውን መልስ በቃልም በተግባርም መመለስ ቢችል በቃ የኢትዮጵያ ችግር ተፈታ !

የችግራችን ሰንኮፎች የተቸነከሩት ዶክተር ሀንጋሳ ካነሳቸው ጥያቄዎች ጋር ነው ! ሌላው እዳው ገብስ ነው ።
ከአንድም የፓርላማ አባል የዶክተር ሀንጋሳን ያክል መስቀለኛ ጥያቄ እንደማይነሳ እርግጠኛ ነኝ !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy
2.0K views08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:33:23
ትላንት በወለጋ ከተገደሉት ከ 350 በላይ ሙስሊሞች ውስጥ 171 የሚሆኑት የተገደሉት በመስጅድ ውስጥ ነው ።
ግና ይህ ሁሉ ግፍ በምድሩ ላይ ሲሰራ የኦሮሚያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ዝንብ የሞተ ያክል እንኳ አልቆጫቸውም !
የኦሮሚያ ክልል ሙስሊም ወንድሞቻችን ዛሬም ከኦነግ ጎን ቆመው ስለኦነግ ይታገላሉ !

ስለ ጎንደርና ሞጣ ሲታገሉ የኮራንባቸው ኡስታዞች ድምፃቸውን አጥፍተዋል ከጥቂቶቹ በስተቀር !

እስልምና የሚያስተሳስረን ትልቁ ገመድ መስሎን ነበረ ። ለካስ የወንድማማችነት ዘመኑም አልፏል መሰል ። ለካ ዲን የሚያስተሳስርበት ያ ወርቃማ ወቅት ላይመለስ ኮብልሏል መሰለኝ !

በርግጥ ትላንትም አስክሬን ስንቆጥር ከረምን አሁንም እየቆጠርን ነው ። ነገስ ከዚህ የባሰ ጭፍጨፋ እየተዘጋጀ አይደለም ወይ ?

ምን ብለን እንጩህ ! ምን ብለን እናልቅስ !
2.1K views19:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 20:00:55
የኦነግ እውየተኛው መሪ ጃል ሽመልስ አብዲሳ አድስ አበባ ላይ በተንጣለለ ቤተመንግሥት እየተንፈላሰሱ በኦነግ ሸኔ ላይ እርምጃ እየወሰድን ነው ማለት ከስላቅ ውጭ ምንም ሊሆን አይችልም !

ጃል ሽመልስ አብዲሳ ለፍርድ ይቅረቡልን !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy
2.2K views17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 09:30:31
ገደሉት

ኦነግ ባለፈው ደራ ሊገባ ሲታገል ካገታቸው አራት ሰዎች መካከል አንዱ ከስር በፎቶው ላይ የምትመለከቱት ማሙሽ የተባለው ወጣት ነበር ። እናም ይህንን ወጣት ካገቱት የመልቀቂያ 500,000 ብር ካመጣችሁ እንለቀዋለን በማለት ቤተሰብ ተበድሮ ለምኖ 500,000 ብር ለኦነግ አስገባ ። ግና አው*ሬዎች አው*ሬ እንጅ ሌላ አልነበሩም !
500,000 ብሩን ከቤተሰቡ ከተቀበሉ በሗላ ማሙሽን ገደሉት ።

ማንም ቢሆን ከኦነግ በላይ አ*መኔ ሊሆን አይችልም !
2.4K views06:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 22:34:54 ሰሜን አፍሪካዊቷ ታላቅ ሀገር አልጄሪያ ነፃነቷን ከፈረንሳይ ለመቀዳጄት 1.5 ሚሊዮን ሰማእቶችን ገብራለች ! ለዚያም አልጀራ የ 1.5 ሚሊዮን ሰማእታት ሀገር ትባላለች !

አፍሪካዊቷ ታላቅ ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ፈፅሞ ነፃነቷን ላለማስነካት ሚሊዮን ውድ ልጆቿን ገብራለች ! በደምና በአጥንት ተቦክታ የተማገረቺው ሀገራችን የአለም የነፃነት ቀንድል ትባላለች !

ይህንን ታሪካችንን ሊያወይቡ ፤ እልፍ አእላፍ ጀግኖች ተሰውተው እዚህ ያደረሷትን ሀገር ሊያፈርሱ የሚደክሙ ሁሉ እነርሱ ይፈ*ርሳሉ እንጅ ኢትዮጵያ እንደሆነ አትፈርስም ! ለዚህ ታሪክ ምስክር ነው ። በትውልድ መካከል የበቀሉ አረ*ሞች ይነቀላሉ እንጅ ለአረሞቹ ሲባል አዝመራው አይነቀልም !

የአልጀሪያን ታሪክ ዝም ብየ አላነሳሁትም ። በነፃነት ታሪክ ተጋድሎዋ ከእኛ ጋር የሚያመሳስላት ነገርም ስላላት እንጅ ። አልጀሪያዊያን ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ነፃነቷን ያጎናፀፏት ሀገር ብትሆንም ቅሉ ልክ እንደኛ ሀገር ሁሉ የጠላቷ ተልእኮ አስፈፃሚ ባንዳ*ዎች የሞላባት ሀገርም ነበረች ።

በርካታ ሚሊዮኖች ለነፃነታቸው ተፋልመው ሚሊዮኖች ሸሂድ ( ሰማእታት ) ሲሆኑ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ባን*ዳዎች ደግሞ ከቅኝ ገዥዋ ፈረንሳይ ጎን ተሰልፈው ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ይወጉ ነበረ ። ባን*ዳ እንደዚህ ነው ! ለፍፁም አራ*ዊትነቱና ጥቅመኝነቱ ውድ ሀገሩን ውድ ህዝቡን ውድ እምነቱን ይሸጣል ። የሀገራችን ባን*ዳዎችም ልክ እንደዚያው ናቸው ።

ኢትዮጵያ ታላቅ የጀግና መስዋእቶች ሀገር ብትሆንም በዚያው ልክ በርካታ ባን*ዳዎች የሚርመሰመሱባት ሀገርም ናት ። ከሻእቢያ እስከ ህወሀት ከዚያም እስከ ኦነግ የሀገራችን የአንድነት እንቅፋቶች የሉአላዊነት ፀሮች ሆነው ኖረዋል እየኖሩም ነው ።

እነዚያ የአልጀሪያ ባን*ዳዎች ፈረንሳይ ከሀገሪቱ ተሸንፋ ተንበርክካ ስትወጣ ፀሀያቸው ጨለመባቸው ። አብዛኞቹ በአልጀሪያ ጀግኖች እስከወዲያኛው ሲሰናበቱ የተቀሩት ደግሞ ከወራሪው ሀይል ጋር በመፈርጠጥ ወደ ፈረንሳይ ተሰደዱ ። እዚያ ግን ፈረንሳይ ባለውለታየ ናችሁ አላለቻቼውም ። እንደውም ተዋርደው ተንቀው ፈረንሳዮች ተፀይፈዋቸው መኖር እጣፈንታቸው ሆነ ። ባን*ዳነት ትርፉ ይህ ነው ። ውርደትና ርክሰት !!

የሀገራችን ባን*ዳዎችም ተጠራርገው ይወ*ገ*ዳሉ !! የንፁሀን የግፍ እንባ የትም አያደርሳቸውም !

ኢትዮጵያ ግን ታሸንፋለች !!!!!

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
t.me/Seidsocial
2.3K views19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 09:47:32
ጊዜው ከ 5 ወር በፊት ነው አንድ ሾፌር ከደራ ወደ አድስ አበባ እየተጓዘ በረሃው ላይ ሲደርስ የኦነግ ተዋጊዎችን ይመለከታል ። ትንሽ ከፍ እንዳለ ደግሞ የኦሮሚያ ልዩ ሀይልን ያገኛል ። ከዚያም እርሱ በሞኝ ልቦናው የጠቆመ መስሎት የኦነግ ሀይል በረሀው ላይ እንዳለ ይነገራቸዋል ።

በዚህ ጊዜ የልዩ ሀይሉ መሪ የነበረው ሰው ወደ ኦነግ ቡድን መሪ ደውሎ " ስለምን ታስጠቁሩናላችሁ ? ለምን አብረን እየሰራን መሆኑን በሚያጋልጥ መልኩ ትንቀሳቀሳላችሁ ? ብንተሳሰብ አይሻልም ወይ ? " ብሎ ይጮህበታል ። በዚህ ጊዜ የኦነጉ መሪ ለልዩ ሀይሉ መሪ ማን ይህን መረጃ እንደሰጠው ሲጠይቀው የሾፌሩን ማንነት ይነግረዋል ። ከዚያ ሾፌሩን ኦነግ መንገድ ላይ አስቁሞ ገደለው ። በዚህ መልኩ ነው አብረው እየሰሩ የሚቀጥሉት ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው እንደገለፀው ሁለት ወንድማማች ሆኖ አንዱ ለኦነግ አንዱ ለልዩሀይል የሚዋጋ አለ ። ታድያ በዚህ ሁኔታ ሁለቱ አካላት ተጨካክነው ይዋጋሉ ማለት ዘበት ነው ።
ከባለስልጣናት እስከ ተራ የፀጥታ ሀይላት በኦነግ አስተሳሰብ ተጠምቀው አብረው እየሰሩ ሳለ ንፁሀን ወገኖቻችን ደህንነታቸው ይጠበቃል ማለት ስላቅ ነው !

አብይ አህመድ ወይ ኢትዮጵያን ይመርጣል
ወይ ከኦነግ ጋር ይሰለፋል !

ኢትዮጵያን ከመረጠ ደግሞ ኦነጋዊ ገንጣይ አስተሳሰብ ያላቸውን ባለስልጣኖቹን መንጥሮ ኢትዮጵያን ከእርስበርስ ጦርነት ይታደግ !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
t.me/Seidsocial
2.4K views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ