2022-08-26 22:30:32
ዛሬ ሱልጧን አልብ አርስላን ልእለሀያሉን የሮም የባይዛንታይን ኢምፓየርን ያንበረከከባት ቀን ነች !!!
አዎ የማንዚኪርት ( መላዝከርድ ) ጦርነት - የከፈኑ ጦርነት !!
የባይዛንታይኑ ግሪካዊው ንጉስ ሮማኖስ 300,000 ጦሩን አሰልፎ መላው ሙስሊም አለምን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ ነው ። ያኔ ገና እስልምናን ከተቀበሉ ብዙም ያልቆዩት ቱርኮች ሙስሊሙን አለም የመጠበቅ ግደታን ተሸክመዋል ። በርግጥ ለጦረኞቹ ቱርኮች ጦርነት ምናቸውም አልነበረም ። " ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው " ሊሉስ የሚገባቸው ቱርኮች ።
ያኔ የምስራቅ ሮም የባይዛንታይን ኢምፓየር በመቶ ሺህ የሚቆጠር ጦሩን ሲያንቀሳቅስ የሰልጁቆቹ ሱልጧን አልብ አርስላን ጦርነቱን ለማስቆም የተቻለውን አደረገ ። ጦርነቱ ገፍቶ ከመጣ በመሳሪያም በሰው ሀይልም አነስተኛ ስለሆኑ የጦር መሳሪያ እርዳታ ኦንኳ ቢያደርጉ ብሎ ለሙስሊሞቹ የአባሲያ ኸሊፋ መልእክት ቢልክም የተሰጠው ምላሽ ግን " ልንሰጥህ የምንችለው ምንም አይነት መሳሪያ የለንም " የሚል የስንፍና መልስ ነበር ።
ስለዚህ ሱልጧን አልብአርሰላን ጦርነቱን እንዲያቆምና እንዲስማማ ለንጉስ ሮማኖስ መልእክት ቢልክም የንጉሱ መልስ ግን " መላው የኢስላሙ አለምን በቁጥጥራችን ስር አድርገን መካና መድናን በእጃችን ካስገባንና እናንተንም ወደመጣችሁበት ካባረርናችሁ በሗላ እንስማማለን " የሚል የምፀት መልስ ላከለት ። መዋጋት ግድ ሆነ !
የሱልጧን አልብ አርስላን ተስፋ አንድ ብቻ ሆነ - አሸናፊው ጌታ አላህ !
እናም ወታደሮቹን ሰበሰበና እንደዚህ አላቸው " ወላሂ ሀገራችን ከገቡ ሴቶቻችንን መጫዎቻ ያደረጓቸዋል ፣ ልጆቻችንን ባርያ ያደርጓቸዋል ፤ መሳጂዶቻችንን የአስካሪ መጠጥ መፈንጪያ ያደርጓቸዋል ከመዋጋት ውጭ አማራጭ የለንም " አላቸው ።
በዚህ ጊዜ ሸይኹ አቡናስር አልሀነፊ ተነሱና " ወላሂ እናን ለአላህ ዲን ነው የምትዋጉት እናንተ የምትጋደሉት አላህ ከዲኖች ሁሉ የበላይ አድርጎ ለላከው የአላህ ድን ነው አልብአርስላን ሆይ አላህ የሙስሊሞችን ድል በአንተ እጅ ሊያደርገው እመኛለሁ " አሉት ።
አልብአርስላን ነጭ ከፈኑን ይዞ ወጣ ለወታደሮቹም " እኔ ዛሬ አዛዣችሁ አይደለሁም መዋጋትና ሸሂድነትን የፈለገ ከኔ ጋር አብሮኝ ይዋጋ መሄድ የፈለገ ይሂድ የሚከለክለው የለም " በማለት ተናገራቸው ። ሁሉም ወታደሮቹ አብረን ሸሂድ እንሆናለን ! በማለት በከፍተኛ ለቅሶና ወኔ ቃላቸውን አስተጋቡ ። ሁሉም ተላቀሱ !! ሁሉን ሸሂድነትን ናፈቁ ። እናም ሁሉም ነጭ ከፈናቸውን ያዚና ወደ ወይ ድል ወይ ሸሂድነትን ናፍቀው ወደ መላዝከርድ ተመሙ ። 300,000 የሮም ወታደሮች በ አስር ሺዎች ከሚቆጠሩ የቱርክ ሙስሊሞ ጦር ጋር ተላተሙ ።
በመጨረሻም ሰልጂቆች አሸነፉ ። አላህም አልብአርስላንን አሸናፊ አደረገና ሙስሊሙን አለም ከውድመት ጠበቀው ። አልብአርስላን የባይዛንታይኑን ንጉስ ማረከው ። ቱርኮችም የአሁኗ ቱርክ ምድር ላይ ሰፈሩ ። ባይዛንታይን ከዚያ በሗላ አላገገመም ።
ያ የአለምን ታሪክ የቀየረው ጦርነት የተካሔደው ልክ በዛሬዋ እለት በ 1071 እ.ኤ.አ ነበር ።
Seid Mohammed Alhabeshiy
ቴሌግራም
t.me/Seidsocial
2.3K views19:30