Get Mystery Box with random crypto!

Seid Social

የቴሌግራም ቻናል አርማ seidsocial — Seid Social S
የቴሌግራም ቻናል አርማ seidsocial — Seid Social
የሰርጥ አድራሻ: @seidsocial
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.83K
የሰርጥ መግለጫ

አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-22 20:38:50 ፍልጤሞች ምን ያክል ፐርሰንት የሚሆነውን ግዛታቸውን ይቆጣጠራሉ ?

ይህ ብዙዎች የሚጠይቁት ጥያቄ ነው ። መልሱ ደግሞ እጅግ የሚያሳዝን !

በአሁኑ ሰአት ፍልጤሞች የሚቆጣጠሩት የፍልስጤም ግዛት 15 % አይሞላም ። ከ 85 % በላይ የሚሆነው የፍልስጤም ግዛት በእስራኤል እጅ ገብቷል ።

ፍልስጤሞች 15 % ግዛታቸውን ብቻ ይቆጣጠራሉ ይባል እንጅ በዚያቹ ግዛታቸውም ፍፁም ሉአላዊነት የላቸውም ። ፍልሰጤም የቀረቻቼው ብጣሽ ግዛትም በእስራኤል አጥር ውስጥ የምትገኝና የእስራኤል ወታደሮች እንደፈለጉ የማፈነጩባት ግዛት ነች ።

የእስራኤል ወታደሮች ያልተቆጣጠሯት የፍልስጤም ግዛት ጋዛ ብቻ ነች ። እርሷም ብትሆን በእስራኤል እና በግብፅ የታጠረች በመሆኗ ካለ ሁለቱ ሀገራት ፈቃድ መውጣትም መግባትም አይቻልም ።

በማህሙድ አባስ የሚመሬው የፍልስጤም ግዛት ከተራ ፖሊሶች የዘለለ ትጥቅና ታጣቂ እንዲኖረው አይፈቀድለትም ። እስራኤል ማህሙድ አባስን ልታስረው ብትፈልግ አንድም የሚያስቆማት ሀይል የለም ። የፈለጉትን አካል በፈለጉት ጊዜ የማድረግ ብቃቱም መብቱም አላቸው ።

ስለ ሀገር ሉአላዊነት የሚለፍፉት ምእራባውያን ስለፍልስጤም ትንፍሽ አይሉም ። የዩክሬን ሉአላዊነት ተደፈረ ብለው የማእቀብ ጋጋታ የሚያወርዱት እነ አሜሪካ ስለ ፍልስጥኤም መወረር ደንታቸው አይደለም ። ማን ሆነና ፍልስጤምን የሚያስወርራት ? ማን ሆነና እስራኤልን እስራኤል ያደረጋት ?

ሙስሊሞች ሶስተኛውን ቅዱስ ቦታቸውን በርግጥ አጥተዋል ። ቁድስ ለሙስሊሞች የማሸነፍና የመሰነፍ ፤ የከፍታና የዝቃታ ምልክት ነች !
መስጅድ አልአቅሷን እስራኤል በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ከመስጅድነት ወደ አይሁድ ቤተ እምነትነት ለመቀየር ዝግጅቷን እንደጨረሰች ተረጋግጧል ። እናም እንደ ስፔይኑ ካቴዴራል መስጅድ አልአቅሷን " መስጅድ ነበር " የምንልበት ጊዜ እንዳይመጣ ያስፈራል ።

ግን ከዚያ በፊት አላህ ዳግማዊ ሰላሁዲን አልአዩቢን ይልክ ይሆን ? ወይንስ ዳግማዊ ኻሊዲና አቡ ኡበይዳን ?!

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
t.me/Seidsocial
2.3K views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 22:06:26 የወሎ ኦሮሞዎችን ከሌላው የወሎ ማህበረሰብ የሚለያቸው ብቸኛ ነገር ቢኖር ኦሮሞኛ መናገራቸው ብቻ ነው ። ከዚያ ውጭ በወሎ ኦሮሞና በተቀረው ወሎ መካከል አንዳችም የባህልም የእምነትም የዘርም የእሴትም ልዩነት የለም ።

ካለወሎ ኦሮሞ ወሎ ጎደሎ ነው ። ካለነርሱ ሙሉእ አይደለንም ። በተለይ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ልክ እንደተቀረው ወሎ ሁሉ የወሎ ኦሮሞ ከሚሴ አካባቢ የኢልምና መንፈሳዊ ማእከላችን ( Spiritual center ) ነው ። እነ ደዌና ጨፋ ሮቢቴ የመሳሰሉ የኢልም መንደሮች ባይኖሩን ኖሮ እኛ በብዙ ጎደሎ ነበርን ።

በዚህች ከሁሉም የርስበርስ ጦርነት አሮንቃ ውስጥ በተዘፈቀችና ከመንግስት ይልቅ የጎበዝ አለቆችና ሽፍቶች ጠንካራ በሆኑባት አገር ውስጥ በርግጥ ወሎየ መሆን የሞት ፍርድ ከሆነ ሰነባበተ ። አንድኛው ብሔርተኛ " ኦነግ " በሚል የዳቦ ስም በወሎ ላይ ጥቃት ሲፈፅም ኦነግ ደግሞ ኦነግ የተባለውን ወሎየ " ነፍጠኛ አማራ " በማለት በጅምላ ይጨፈጭፋል ። የድብልቅ ማንነት ባለቤት የሆነው ስብጥሩ ወልየም ከየትኛውም መሆን አቅቶት በሁለት ሰይፍ ይታረዳል ። ይህ አሳዛኙ ሁኔታ ነው ።

ገለልተኛ በሆነ መልኩ ህግን ማስከበር ያቃተውና በዘርልጓም የተተበተቡ ፅንፈኞች በሚመሩ የብልፅግና መንግስት ዘንድ ሰውነት ከዛፍ ከረከሰ ከችግኝ ካነሰ ስለቆየ የህግ ያለህ ብለን ብንጮህም መንግስታችን የሚሰማው በዛፍ ላይ ያለችን የአእዋፍ ድምፅ እንጅ የንፁሀንን የሰቆቃ ድምፅ አይደለምና ስቃያችን ተራዝሞ ቀጥሏል ።

ወለጋ ላይ በኦነግ ከተጨፈጨፊት ወሎየዎች የወሎ ኦሮሞዎችም እንደሚገኙበት እየታወቀ የወለጋ ወገኖቻችን ደም ሳይደርቅ ጦርነቱን ወደ ወሎ ምድር ማምጣት የሀገሪቱን እጣፈንታ በእንቅርት ላይ ጆር ደግፍ የሚያደርገው ነውና ይህ መንግስት ይህንን እንዲያስቆም አሁንም ደግመን ደጋግመን እንጠይቃለን !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
t.me/Seidsocial
1.4K views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 20:13:01 ከ 27 አመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ነበር በቦስኒያ ሙስሊሞች ላይ እጅግ አስከፊው የዘር ማጥፋት በሰርቢያ ጦር የተፈፀመው ።

ሙስሊሞችን ጨፍልቆ ኦርቶዶክሳዊት ታላቋን ሰርቢያን ለመመስረት ታግሎ ያታገለው ስሎቦዳን ሚሎሶቪች በቦስኒያዎች ጂሃድና በነ ኢራን እና ቱርክ አይተኬ እገዛ ሲከሽፍበት የበቀል እርምጃውን በስሬብሬኒካ ከተማ ላይ ደገሰ ። ለዚህ አላማውም ፅንፈኛውን የሰርቢ ጦር መሪ ራትኮ ሚላዲችን አስታጥቆ ወደ ከተማዋ ላከ ።

ስሬብሬኒካ ያኔ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ እጅ የነበረች ቢሆን ጨፍጫፊውን የሰርቢያ ጦር ግን ማስቆም አልተቻለም ወይንም የማስቆም ፍላጎቱ አልነበረም ። እናም በራትኮ ሚላዲች የሚመራው ጦር የሙስሊሞች ከተማ ወደሆነቺው የስሬብሬኒካ ከተማ ገባ ።

ከዚያ በሗላ የቦስኒያ ሙስሊሞችን ወንዶችና ወንድ ህፃናትን ለብቻ ሴቶችና ሴት ህፃናትን ለብቻ ለያየና ወደ አዘጋጀላቸው ቦታ ወሰዳቸው ። ለብቻ የተወሰዱት ወንዶችና ወንድ ህፃናት በሙሉ እንዲገደሉ ተደረጉ ። በጥይት ጨፍጭፈው የተረፋቸውን በሰይፍ ከዚያም በሰይፍ አልበቃቸው ሲል በቡልዶዘር ከነህይወታቸው ጨፈለቋቸው ። እንደዚያ እየገደሉ ቀድሞ ያዘጋጁት የጅምላ መቃብር ውስጥ በአንድ ላይ ይወረውሯቸው ጀመር ። እነዚህ ፅንፈኛ የሰርቢያ ብሔርተኞች ከቡልዶዘርና ከጥይት የተረፏቸውን ሙስሊሞች ከነህይወታቸው በዶዘር በቆፈሩት መቃብር ውስጥ እየከተቱ አፈር ያለብሱባቸው ነበር ።

የስሬብሬናካ ዘር ማጥፋት ( Genocide ) ግፍ በዚህ አያበቃም ። ከወንዶቹ ነጥለው የወሰዷቸውን ሙስሊም ሴቶች ሁሉም ወታደሮች ህፃናትን ሳይቀር መድፈር ያዙ ።
አንድ የአይን እማኝ ሄግ ለሚገኘው የአለም አቀፉ ፍርድ ቤት ያየውን ጭካኔ ሲናገር እንደዚህ ይላል
" አንድት የወራት እድሜ ያለው ህፃን ያላት ሙስሊም ሴት ቀረበች ከዚያም ደፈሯት በዚህ ጊዜ ህፃኑ ማልበስ ያዘ የሰርቢያ ወታደሮች ይህች የተደፈረች እናት ልጇን ከማልቀስ አስቁሚ አሏት ግና ህፃኑ ማልቀሱን ቀጠለ ። በዚህ ጊዜ አንዱ ወታደር ተቀብሎ አንገቱን ቀን*ጥሶ ጣለው ።
ከዚህ የከፋም አይቻለሁ አንዲቱ ሙስሊም ህፃን ዘጠኝ አመቷ ነው ከዚህች ህፃን ጋር ወንድሟ አብሮ ነበረ ። ወታደሮቹ ያ ወንድሟ እህቱን እንዲደፍር አስገደዱት እርሱ ግን እንቢ አለ እርሱም ህፃን ስለነበር አልደፈራትም ። በዚህ ጊዜ ወታደሮቹ ያንን ልጅ አንገቱን ቆር*ጠው ጣሉት እርሷንም ደፈሯት ። "

ሌላኛው የአይን እማኝ ደግሞ
" የዘጠኝ አመት ልጇ ልትደፈርባት ያለች እናት " እባካችሁ እርሷ ገና 9 አመቷ ነው እርሷን እንኳ ተውልኝ " እያለች ትማፀናቸው ነበር ግና እነርሱ ሊሰሟት አልፈቀዱም ህፃኗን ልጅ ደፈሯት ደሟ በህፃን እግሮቿ ላይ እየፈሰሰ ከመሬት ተዘርራ አየሗት " በማለት ያን ሰቅጣጭ የሙስሊሞች ጭፍጨፋ ተናግሯል ።

የሰርቢያ ብሔርተኞች ያን ሁሉ ሰቅጣጭ የዘር ማጥፋት በመሀል አውሮፓ በቦስኒያ ሙስሊሞች ላይ ሲፈፅሙ በቦታው ያለውና በኔዘርላንድ የሚመራው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ቅንጣት ታክል እንኳ ሊከላከልላቸው አልቻለም ነበር ። ከዚያም አልፎ የሰላም አስከባሪው ጦር መሪ ያንን ሰቅጣጭ ትእይንት በቀጥታ ይመለከቱ ነበር ።

በዚያች ቅፅበት የሰርቢያ ኦርቶዶክሳዊ ብሔርተኞች ከ 8,000 በላይ ቦስኒያውያንን በጅምላ ሲጨፈጭፉ ከ 25,000 በላይ ሴቶችና ህፃናትን በሰቅጣጭ ሁኔታ ደፈሩ ። ይህ ከሆሎከስት ማለትም ናዚ አይሁዳዊያንን ከጨፈጨፈበት ክስተት በሗላ በአውሮፓ የተከሰተ ትልቁ የዘር ማጥፋት ሆኖ ተመዝግቧል ።

ሗላ ላይ ጭፍጨፋው ካበቃ በሗላ አለምአቀፉ ፍርድቤት በሰርቢያው ጦር መሪ ራትኮ ሚላዲች ላይ የ 700 አመት ( ሰባት መቶ አመት ) እስራት ሲበይን በሌሎችም ላይ ከመቶ አመታት እስከ 50 አመት ድረስ ከፍተኛ እስርን ፈርዶባቸዋል ።

እነ ራትኮ ሚላዲችና ስሎቦዳን ሚሎሶቪች የቦስኒያ ሙስሊሞችን ከምድረገፅ ለማጥፋት የቻሉትን ሁሉ ቢያደርጉም ቦስኒያ ሔርዝጎቬኒያ ግን ዛሬም የሙስሊሞች ሀገር ሆና ቀጥላለች ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
t.me/Seidsocial
1.6K views17:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 18:48:04 ሩሲያ ምስራቅ ዩክሬይንን ከመቆጣጠር ወደ ሙሉ ዩክሬይንን ወደ መጠቅለል ዘመቻ ተሻጋግራለች ።
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ለሁሉም ዩክሬናዊያን የሩሲያ ዜግነት እንዲሰጥ አዘዋል ። ይህም ሁለቱ አንድ ዘርና ማንነት ያላቸውን ህዝቦች በአንድ ሀገርነት ለማጠቃለል ያለመ ነው ።

አሁን ሩሲያ ምስራቅና ደቡብ ዩክሬይንን በቁጥጥሯ ስር አድርጋ ጦራ ወደ መሀል እየገሰገሰ ነው ። ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን " ጦርነቱን ገና አልጀመርንም " ማለታቸው ደግሞ በዩክሬይን መንግስትና በምእራባውያን ላይ ታላቅ ድንጋጤን የፈጠረ ሆኗል ። የሩሲያ ጦር ለሌላ ትልቅ ተልእኮ ለሌላ ሰፊ ዘመቻ በተጠንቀቅ ላይ ይገኛልም ተብሏል ።

ከ 1.4 ሚሊዮን በላይ ጦር ሰራዊት ያላትና በጦር ሰራዊት ግዝፈት ከቻይና በመቀጠል ከአለም ሁለተኛ ደረጃን የምትይዘው ሩሲያ እስካሁን በዩክሬይን ያሰማራቺው ከ 100,000 የማይበልጥ ጦሯን ነው ። እናም ሩሲያ ከዚህ በበለጠ ወደ ዩክሬይን ለመዝመት ዝግጅቷን እየጨረሰች ነው ።

ሩሲያ እስካሁን ድረስ በዩክሬን ላይ ጦርነት አላወጀችም ። ሩሲያ ዘመቻዋን " ልዩ ወታደራዊ ዘመቻ " በማለት ነው የምትጠራው ። እናም በዩክሬን ላይ ሙሉ ጦርነት የምታውጅ ከሆነ ሙሉ ሀይሏን ወደ መጠቀም እና አውዳሚ ሚሳኤሎቿን ወደማዝነብ ትሸጋገራለች ።

የሩሲያው ክንደ ብርቱ መሪ የቭላዲሚር ፑቲን የዛቻ ቃል ግን ከዩክሬይንም የቸሻገረ መላው ምእራባውያንን የሚያስፈራራ አይነት መግለጫ ነው ።
ፑቲን እንደዚህ አለ " ምእራባዊያን ሩሲያን ለማንበርከክ ይፈልጋሉ ። እንደዚያ ከሆነ መልካም ነው ከጦር ሜዳው እንገናኝና ይሞክሩን " ሲል ሩሲያ ምእራባውያንን ለመግጠም ብቻ ሳይሆን ለማንበርከክም ዝግጁ መሆኗን ገልጿል ።

" ማንም ያልታጠቃቸው አውዳሚ መሳሪያዎች አሉን ፤ ማንም የማይፎካከረው ሀያል ጦርም አለን ጠላቶቻችን እኛን ለመግጠም ከማሰባቸው በፊት ደጋግመው እንዲያስቡ የሚያደርጋቸው ነው ፤ የትኛውም ሀያል ነኝ ባይ ሀገር ከሩሲያ ጋር የሚያፎካክረው አቅም የለውም ይህ ብዥታ እንዳይፈጥርባቸው ይጠንቀቁ " በማለት ሩሲያ ከፊቷ የቆመን የትኛውን ሀይል ከማውደም እንደማትመለስ ፕሬዚዳንት ፑቲን አረጋግጧል ።

እናም የሩሲያ ጦር የዩክሬይን ዘመቻውን ወደ ጦርነት ሊያሳድግ ፓርላማው ዛሬ ይሰበሰባል ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
t.me/Seidsocial
1.9K views15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:24:37
በሸዋ የሚኖሩ የወሎ አማራዎች ሌላ ዙር ጭፍጨፋ እየተዘጋጀላቸው ይሆን ?

በምእራብ ሸዋ ዞን የሚኖሩ ወሎየዎች ትጥቃቸው እየተቀማ ወደ እስርቤትም እየተጋዙ እንደሆነ ከቦታ የደረሰኝ መረጃ ያመለከታል ። ይሆ እየሆነ የወሎ ማህበረሰብ በስፋት በሚኖርበት ምእራብ ሸዋ ዞን ባኮ ቲቤ ወረዳ ነው ።

የፀጥታ ሀይሎች የአማራ ተወላጆችን ብቻ እየመረጡ ትጥቃቸውን እየቀሙ ይገኛሉ ። በተለይ ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት ህጋዊነት ባላቸውና የአካባቢውን ፀጥታ በሚያስጠብቁ ሚሊሻዎች ላይ ማተኮሩ በአካባቢው ማህበረሰብ ላይ ትልቅ ስጋትን ደቅኗል ። ትጥቅ የማስፈታቱ ሂደት የኦሮሞ ሚሊሻዎችን የማያካትት መሆኑና በድብደባና ወከባ የታጀበ መሆኑ ሲታሰብ ስጋቱን ከፍ ያደርገዋል ።

በወለጋ የተጨፈጨፉት ወገኖቻችን ቀድሞ ኦነግ ጦርነት ሳይከፍትባቸው በፊት መሳሪያቸው በመንግሥት ፀጥታ ሀይሎች ተቀምቶ ትጥቅ አልባ እንዲሆኑ ተደርገው ነበር ። እናም ባዶ እጃቸውን ሆነው ያገኛቸው ሸኔ ህፃናትን ጭምር ሳያስቀር የሰራውን ሰራ ።

የባኮ ወሎ ማህበረሰብ ጠንካራ ማህበራዊ መሰረት ያለው ሲሆን ከዚህ ቀደም ሊፈፀሙበት የታሰቡ የኦነግ ጥቃቶችን በራሱ ሲመክት የኖረ ነው ። አሁን አካባቢው በኮማንድ ፖስት ስር ነው ቢባልም ኦነግ እንደፈለገ በሚፈነጭበት አካባቢ ማህበረሰቡን ትጥቃ አልባ ማድረግ አሁንም ለጅምላ ጭፍጨፋው ማመቻቼት ነው ።

በዚህ በኩል ተሰሚነት ያላችሁ አካላት ዳግም ጭፍጨፋው ከመከሰቱ በፊት የግፉአን ድምፅ እንድትሆኑ እጠይቃለሁ !

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
t.me/Seidsocial
2.2K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 23:01:47
Yaa Walloo battee- ያ ኢልመ ይመሬ!!
★★★★★// //★★★★★

Maal čilimiinakkanaa
maal čilimiinakkan

ይህ አህመድ ይመሬ-ኬሻ የለበሰ
ተእናቱ እቅፍ ወርዶ በአውሬ የተፈሰሰ

ተግርጌዋ ውሎ- በሳር የተጌጠ
ህቃታ አልቦ ሙጫ-በሞት የተናጠ
በወሎየ ጭዳ… በአስከሬን ያጠጠ
በእጀ ጠባቡ ኪስ-በአሹቅ የአበጠ

በግራ እጁ ቂጣ- በቀኝ እጁ እናቱን- ቀሚሷን ያነቀ
ቂጣ እየገመጠ… በአሹቅ እያበቀ
ከምድጃ ጋጡ… ከጋጡ ምድጃ አብሮ እየተንፏቀቀ

እየሳቀ ነበር --እየተጫወተ--እንደዚህ ሳይተኛ
ተስፋ ሳይነጠቅ፣ ትንፋሽ ሳይቀማ-ሳይባል ነፍጠኛ

ሳይቃት መትረጌስ--ሳይደፋ በፊት
ክንብል ሳይል ቀድሞ- ለቁርሾ ሳይቋት

አኮሌ አንጠልጥሎ-የላም ጭራ ይዞ
የላም ልጅ ወተቱ- እስኪታለብ ፈዞ

ለቂጣው መጉመጃ - ለአሹቁ ማዳፊያ
ወዲህ ከእንቦሳው ወዲያ ከእናት ጉያ
እየታሸ ነበር- ቂጣ እየገመጠ
እየሳቀ ነበር --እንቦሳ እየሳመ

ኪም ኪም ኪም …ተስፋን እያበጀ
ቂጣ በወተት ገምጦ…እድሜን እየባጀ

Yaa didii galgalaa
Yaa didii galgalaa

ሙጫን የሚቀዱ
ተፈጥሮን የካዱ

ተጨቆንን በሚል ጭቆና ያረገዙ
እርጉዝ የሚቀዱ—ሙጫ የሚመግዙ

ሙጫ ቢያ አህመድን
ያን ኢልመ ይመሬን
በጥይት በሳሱት፣ በምሳር ፈለጡት
ህቃታውን ቀሙት
ከነናቱ ደፉት
እንቦሳውን ቀሙት

ወተቱን ሳይጠጣ አሹቅ እንደቃመ
በወለጋ ምድር-በሰው መሳይ ፍጡር ሰውነት ታመመ

የቶሌ ቆሪጦች --የወለጋ አጋንንት
ክፉኛ ደንግጠው—የከፋውን አዩት

Jal Maroo farad qilleensaa qilleensee
dufeetii qalnuqixxeessee
waraanni gaaraa duultee
allaattin Shannee quufte

____________
ዐብዱልጀሊል ሸኽ ዐሊ ካሳ
2.0K views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 21:31:25
አንድ ቀን ነብያችን ሶ.ዐ.ወ የሱብሂ ሶላትን በመስጅድ እያሰገዱ እያለ ህፃን ልጅ ሲያለቅስ ይሰማሉ ። ህፃኑ የሚያለቅሰው እናቱን ፈልጎ ነበር ። እናቱ ደግሞ ከነብያችን ሶ.ዐ.ወ ጋር እየሰገደች ነው ። እናም አዛኙ ነብይ የህፃኑን ለቅሶ እንደሰሙ ከቁርአን አያዎች በጣም አጭሯን በመቅራት የፈጅር ሶላትን ጨረሷት ። ልብ በሉ ከነብያችን ሶላቶች ረጂሙ የሲብሂ ሶላት ነው ።

ከዚያም ሰዎች ነብያችንን ሶ.ዐ.ወ ስለምን ሶላቱን በዚህ ያክል ፍጥነት ጨረስክ ? ብለው ጠየቋቸው ። ነብያችንም " ህፃኑ ልጅ እናቱን ፈልጎ ሲያለቅስ ስሰማ አሳዝኖኝ ነው " በማለት መለሱላቸው ።

ነብያችንን ሶ.ዐ.ወ ፍጥረታት ሁሉ ያሳዝኗቸዋል ። ለህፃናት ያላቸው እዝነት ደግሞ ከሁሉ ይልቃል ። ህፃናት ሲያለቅሱ አይተው በፍፁም አያልፉም ። ሲበደሉ በፍፁም አይወዱም ። አባት የሌለው ህፃን ሲያለቅስ ቢያዩት " እኔ አባትህ ብሆን ደስ አይልህም ?" በማለት አባት ሁነውት እንጅ አያልፉትም ። እንኳን ለሰውና ለአውሬ የሚያዝኑት አዛኝ ነብይ !

ዛሬ ምንም ወንጀል የሌላቸው ህፃናት እናቶቻቼው እንደወለዷቸው ያሉ ህፃናት በማያውቁት ማንነታቸው ሲገደሉ ሲታ*ረዱ ቢመለከቱ ወላሂ ቢላሂ ያንን የህፃናት ገዳይ ቡድን ጦርነት ያውጁበታል እንጅ በፍፁም አይተውትም ነበር ።

አንድ ቀን አንድ አረብ እስልምናን ከመቀበሉ በፊት ስድስት ሴት ልጆቹን እንደገደለ በመፀፀት ሲነግራቸው ነብያችን ሶ.ዐ.ወ የሚያደርጉትን አጡ ቁጣቸው ንደታቸው ከቁጥጥር ውጭ የሚውስድ ያክል ነበር " ወላሂ እስልምናን መቀበልህ ያለፉትን ወንጀሎች የሚያብስ ባይሆን ኖሮ አንገትህ በቀነ*ጠስኩህ ነበር " በማለት እጅግ ብርቱ ቁጣን ተቆጡት !

ዛሬ ህፃናት የጨካኞች የገፍ በትር ቀማሽ መሆናቸውን ቢያውቁ ምን ይሰማቸው ይሆን

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy
1.8K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 20:59:00
ይቺ መርየም ሰይድ…በወለጋ ምድር
★★★ ★★★

ተጀርባዋ አውላ ---ውሀ መቅጃ ጎማ
ቤቶቿ ባቀኑት ----በወለጋ ውርማ

ቁርስ ቢጤ…… መስሪያ
በለሴ………… ማንኮሪያ
ለለቤ ይሆናት
አፏን ትሽርበት
---
እናቷን ልታግዝ–እኋ ልትቀዳ
ወደ ወንዝ ወርዳ
---
ይቺ ጭቃ ጫማው —ይቺ ንታቢ ልብሷ
ይች ወሎየ ሶብይ—ይቺ እድለ ቢሷ
----
ተወደፊቷ ተግንባሯ ፊትፊት………
እቶን የለበሱ አውሬነት የቋቱ
«ምንድነሽ? ቁሚ » አሏት
ምንነቷን አውቀው ሩኋን ሊፈቱ
------

ይቺ የወሎ ሶብይ ___አየ መሬሚቱ
አይ እድለ ቢሷ—የወል ሰው ቁጭቱ

" መሬም" ብላ መጣይ ወገቧን አዙራ
ልትታገዝ መስሏት …ትጥቋን እያላላች …ጎማውን ገፍትራ!

አፋን ኦሮሚፋ—እንቤካ ኢንቤካ
እያለ ተኮሰ— ጮቤ እየረገጠ…… በጥርሱ እያሽካካ

………

የኔ መሬም ሰይድ—የኔ እፉየ ገላ
ምኗን ለመትረጌስ …ምኗን ለብቀላ
በፊቷ ተደፍታ— ጨቅይታ በደሟ አባላ

ገዳይ ይሸልላል—ነፍጠኛ መግደሉን
ግዳይ መለሽለሹን—አማራ መጣሉን

በወለጋ ጫካ…… በውርማው መካከል
ሶብይ በደም ነክሮ…… በምስል ይቀርፃል

በገድሉ ፈንድቆ
በቂልነት ደምቆ

Qeero, Qeero, Qeero
Qeero badaraatuu

እያለ ሸለለ
እያለ ቀለለ

የሞረዳን ልጆች
የነኩምሳን አማች
የጆቴን አደራ በቁሙ የበላ
ይህ ደመ አውሬ አባያ — የቃየል አተላ

እንኳንስ ወገንን መግደል የተጋባን
በገዳዎቹ ህግ- ነውረኛ መሆኑን

Silaa arbi bineensa,
Duuri qabaaf malee.
Silaa walgayiin Dhidheesa,
Xuuri qabaaf malee.

Xuuri አልባ ነውረኛ- ሙጫ ገሎ ቢያዩት
የወለጋ ጫካ የቶሌ አውሬዎች …… በአውሬነቱ ናቁት
…………………………

ዐብዱልጀሊል ሸኽ አሊ ካሳ
2.1K views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 22:34:19
بأي ذنب قتل !
በሞን ወንጀላቸው ተገደሉ ?
እኮ በምን ወንጀላቸው ?
2.0K views19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:44:42 "በአንድት ጀንበር 170 ሰዎች ቀሳውስትና መነኮሳትን ጨምሮ በቤተክርስቲያን እንደተጠለሉ ተጨፈጨፉ የሚለውን አስቡ ። ከዚያም ከተጨፈጨፉት ውስጥ ከ 15 ቀን ህፃን እስከ እመጫትና ነፍሰጡር ሴት አሉበት" ብላችሁም አስቡት !
"ወይንም ደግሞ 1,600 ኦሮሞዎች በብሔር ማንነታቸው ተለይተው በአንድት ቀን ጀንበር ተጨፈጨፉ " የሚለውንም አስቡ !

እንደዚያ ቢሆን በእውነት ሀገር የምትቆም ይመስላችሗል ?
ያ ቢሆን አብይ አህመድ እንደዚህ እየተለፋደደ " ለሟቾች ጥላ የሚሆን ችግኝ እንተክላለን " የሚል ይመስላችሗል !?
ከላይ ከሁለቱ አንዱ ቢሆን ከሀገር ቤት እስከ ውጭ ይህቺ ሀገር አትናወጥም ነበር !?

ግና የሞቱት ወሎየዎች ናቸዋ ! ግና የተጨፈጨፉት ሙስሊሞች ናቸዋ ! ስለዚህ በሁለቱም መስፈርት ደማቸው ርካ*ሽ ነው !
ወሎየ ሞተ አልሞተ ማን ከቁብ ይቆጥረዋል ! ዱሮስ መሞት ለወሎየ መች ብርቅ ነው !

የሞተው የወሎ ሙስሊም በእስልምናው እንዳይቆሙለት በአብዛኛው የሀገሪቱን ሙስሊሞ የሚሸፍነው የኦሮሞ ሙስሊም ከእምነቱ ይልቅ የዘር ልጓሙ የሚጎትተው ዘረኛ ነው !!

የሞተው የወሎ አማራ የአማራ ህዝብ እና ፖለቲከኛ እንዳይቆምለት ለአማራ ፖለቲካ ለአማራ ማንነት ትልቁ ገመድ ኦርቶዶክስነት እንጅ ሌላ አይደለም ። ስለዚህ ኦርቶዶክስ ያልሆነ በተለይ ከጎጃም ወይም ከጎንደር ካልሆነ እርሱ ሁለተኛ አማራ ስለሆነ ምን ማካበድ ያስፈልጋል ?! ምንም !

በዚህ ሁሉ መሃል ግን ወሎ ያልቃል ! የዋሁ ከማንም ጋር ተላምዶ ተግባብቶ በፍቅር የሚኖረው ወሎየ ያልቃል !
ከውስጡ ጠንክ የሌለበት ማንንም በክፉ የማይመለከተው ወሎየ ይጨፈጨፋል ! ለምን !????

እና የሞተው አንድም ወሎየ ሁለትም ሙስሊም ስለሆነ የሀገሪቱ መሪ እንኳ ከችግኝ አሳንሶ በሞቱ ላይ ተሳለቀበት ?!!

እሺ ሁሉም ይሁን ሀያሉ አላህ ግን ፍርድህ አይቀርብም !
አንተ ተበቃዩ ጌታየ ሚስካን ባሮችህን ስለምን ለአው*ሬዎች ተውካቸው

ብልሀትም ሀይልም ከአላህ ውጭ የለም
2.0K views18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ