Get Mystery Box with random crypto!

SadatKemal Abu Meryem

የቴሌግራም ቻናል አርማ sadatkemalabumeryem — SadatKemal Abu Meryem S
የቴሌግራም ቻናል አርማ sadatkemalabumeryem — SadatKemal Abu Meryem
የሰርጥ አድራሻ: @sadatkemalabumeryem
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 119.45K

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-09-11 06:16:25
የውሸት ጥግ "ይበልጣል ከኢዶች ሁላ መውሊዶ ያረሱለላህ"?
17.7K views03:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-11 06:15:05
ሰይጣን መውሊድ ፋና ቲቪ።
በድምፅ ማስረጃ የተደገፈ።
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/2644
17.0K views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-11 06:15:05 ሰይጣን መውሊድ ፋና ቲቪ።
በድምፅ ማስረጃ የተደገፈ።
16.2K views03:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-10 19:51:51 "ኑሩን ከኑሩ ኸለቀው ጀሊሉ"
~
ይሄ ንግግር ሱፊዮች አካባቢ ተደጋግሞ የሚሰማ ነው። ምን ማለታቸው ነው?
* "ኑሩን" ሲሉ ነብዩን ﷺ ማለታቸው ነው።
* "ጀሊሉ" ሲሉ አላህ ማለታቸው ነው።
* "ከኑሩ" ሲሉ ከአላህ ኑር ማለታቸው ነው።
* ኸለቀው = ፈጠረው

ጥቅል መልእክቱ:-
አላህ ነብዩን ﷺ ከራሱ ኑር (ብርሃን) ነው የፈጠራቸው እያሉ ነው።
አንዳንዶቹ ይህንን መነሻ በማድረግ በግልፅ ነብዩ ﷺ የአላህ ክፍል (ጁዝእ/ part) ናቸው ብለዋል። ይሄ መሰረተ-የለሽ እምነት ነው። ለዚህም በተለያዩ ነጥቦች ምላሽ መስጠት ይቻላል።

1- ነብዩ ﷺ ከኑር (ከብርሃን) ነው የተፈጠሩት የሚሉ አካላት መሰረተ ቢስ ወሬ እንጂ አንድም የቁርኣንም ይሁን የሐዲሥ መረጃ ማቅረብ አይችሉም።

2- በአፈጣጠር በኩል ነብዩ ﷺ እንደሌላው የአደም ዘር ሰው ናቸው። እዚህ ላይ ጥርጣሬ ሊገባን አይገባም። አላህ እንዲህ ሲል ሰው አዋጅ እንዲናገሩ አዟቸዋል፦
{قُلۡ إِنَّمَاۤ أَنَا۠ بَشَرࣱ مِّثۡلُكُمۡ}
"እኔ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ' በላቸው።" [ከህፍ፡ 110]

3- ወላጆቻቸው እና ዘር ማንዘራቸውም የሚታወቁ ናቸው። እሳቸውን ጨምሮ ሁሉም እንደ ሌላው የሰው ዘር የአደም ዘር ናቸው። አደም ከጭቃ መፈጠራቸው ግልፅ ነው።

4- ነብዩ ﷺ ሞተዋል። ስለዚህ "ከአላህ ኑር ነው የተፈጠሩት፣ የሱ ክፍል (ጁዝእ/ part) ናቸው'' የሚል ሰው የአላህ ክፍል ሙቷል እያለ ነው። ይሄ ሰቅጣጭ ድምዳሜ ነው። ለነገሩ እነዚህ ሰዎች የነብዩን ﷺ መሞትም ሊከራከሩ ይችላሉ። የሱፊያ እምነት በብዙ ነጥቦች ከ0ቅል ጋር የተኳረፈ እምነት ነው። እንኳን ነብዩን ﷺ ፤ በየመንደሩ ያሉ ሸይኾች ሲሞቱ "አልሞቱም፤ ሌላ አገር ወጥተዋል" እያሉ የሚያምኑ ብዙ ናቸው። ለማንኛውም ነብዩ ﷺ መዲና ሞተው ሶሐቦች አጥበው፣ ከፍነው፣ ሶላተል ጀናዛ ከሰገዱባቸው በኋላ ዓኢሻ ቤት ውስጥ ተቀብረዋቸል። አላህም ሟችነታቸውን እንዲህ ሲል አስረግጦ ተናግሯል:-
{إِنَّكَ مَیِّتࣱ وَإِنَّهُم مَّیِّتُونَ}
"አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው።" [ዙመር: 30]

"ሲሞት እንገላገለዋለን" ሲሉ ለነበሩ ጠላቶችም ''እርማችሁን አውጡ እሱ አይሞትም" አይደለም ያላቸው። ይሄውና ምላሹ፦
{وَمَا جَعَلۡنَا لِبَشَرࣲ مِّن قَبۡلِكَ ٱلۡخُلۡدَۖ أَفَإِی۟ن مِّتَّ فَهُمُ ٱلۡخَـٰلِدُونَ (34) كُلُّ نَفۡسࣲ ذَاۤىِٕقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ}
"(ሙሐመድ ሆይ!) ካንተ በፊት ለማንም ሰው ዘለዓለም መኖርን አላደረግንም። ታዲያ ብትሞት እነሱ ዘውታሪዎች ናቸውን? ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት።" [አንቢያእ፡ 34-35]

ማምታቻ:-
-
ነብዩ ﷺ ከኑር (ከብርሃን) ነው የተፈጠሩት የሚሉ አካላት አንድ እንዲህ የሚል የሚያቀርቡት "ሐዲሥ" አላቸው፦
أولُ ما خلق اللهُ نورُ نبيِّكَ يا جابرُ
"መጀመሪያ አላህ የፈጠረው የነብይህን ኑር (ብርሃን) ነው፣ ጃቢር ሆይ!"
በየትኛውም የሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ የማይገኝ መሰረተ ቢስ ወሬ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
18.7K views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-10 19:34:55
የአህባሾች ቲቪና መውሊድ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/2634
17.3K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-10 19:34:55 የአህባሾች ቲቪና መውሊድ
17.2K views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-09 11:27:07 ማስታወቂያ
~
የፊታችን እሁድ በሑዘይፋ መስጂድ የሴቶች ፕሮግራም እንዳለ ስለተነገረን ሳምንታዊ ደርስ አይኖርም።
21.1K views08:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-07 09:42:29
130 ሐዲሶች ክፍል 17
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/5755
የኪታቡ pdf ከሚከተለው ሊንክ ያገኙታል
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/5509
17.2K viewsedited  06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-07 09:41:10 የኪታቡ pdf ከሚከተለው ሊንክ ያገኙታል
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/5509
16.3K viewsedited  06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-07 08:34:30 ሰኞ እና መውሊድ?

መውሊድ አክባሪዎች “ነብዩ ﷺ ሰኞን የተወለዱበት ቀን ስለሆነ ፆመዋል፡፡ ይህም መውሊድን (ልደታቸውን) ለማክበር ማስረጃ ነው፡፡” ይላሉ፡፡
በአላህ ፍቃድ እና እገዛ ማስረጃ ብለው ያቀረቡት፣ ማስረጃ መሆን እንደማይችል በሰፊው እንየው፡፡
ነብዩ (ﷺ) ሰኞን ቀን እንደሚፆሙ በትክክለኛ ሀዲሶች ተረጋግጧል፡፡ የሚከተሉትን ሀዲሶች እንይ

የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ሰኞን ለምን እንደሚፆሙ ተጠየቁ፣ እሳቸውም “በዛ ቀን ተወለድኩ፣ እናም መለኮታዊ ራእይም በዛው ቀን መጣልኝ” ሰሂህ ሙስሊም 1162
በሌላ ዘገባ የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ አሉ “ስራዎች ሰኞ እና ሀሙስ (ወደ አላህ) ይወጣሉ፡፡ ስራዬ ፆመኛ ሆኜ እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ” ቲርሚዚ 747

ከነዚህ ሁለት ሀዲሶች የምንማራቸው ትምህርቶች እንደሚከተለው ይቀርባሉ
1.) የአላህ መልክተኛ (ﷺ) ሰኞን የፆሙት ለሶስት ምክንያቶች ነው
a. የተወለዱበት ቀን ስለሆነ፣
b. ቁርኣን ለእሳቸው የወረደበት ቀን ነው፣
c. ስራዎችም ወደ አላህ የሚወጡበት ቀን ስለሆነ እና እሳቸው ስራቸው ፆመኛ ሆነው እንዲወጣላቸው ስለፈለጉ፡፡
የአላህ መልክተኛ (ﷺ) የፆሙት ከላይ በተጠቀሱት ሶስት ምክንያቶች እንጂ ሰኞን ስለተወለዱበት ብቻ አልነበረም፡፡

2.) ከዚህ ሀዲስ ሰሃባዎች አመት ጠብቀው በረቢአል አወል የነብዩን (ﷺ) ልደት ማክበርን አልተረዱም፡፡ ሰሃባዎች ደግሞ ለኢስላም በጣም ቅርብ፣ ኢስላምን ጠንቅቀው አዋቂዎች እና ኢስላምን ከማንም በላይ የተረዱ ከመሆናቸውም ጋር “መውሊድ” የሚባል በአል አያከብሩም ነበር፡፡

3.) ታቢኢን በመባል የሚታወቁት የሰሃባ ተማሪዎች ከዚህ ሀዲስ መውሊድ የሚባል በአል አለ ብለው አልተረዱም፡፡

4.) አራቱ ታላላቅ የፊቂህ ኢማሞች አቡ ሀኒፋ፣ ኢማሙ ማሊክ፣ ኢማሙ ሻፊኢ እና ኢማሙ አህመድ ይህን ሀዲስ እያወቁ፣ ሀዲሱን መውሊድ (የነብዩን ልደት) ማክበር ይቻላል ለሚል ማስረጃ አልተጠቀሙትም ፡፡

5.) በዚህ ሀዲስ የተገደበው አምልኮ ፆም ነው፡፡ ስለዚህ ፁሙ፡፡ ከዚህም አትለፉ፡፡ ዲኑ ገር ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) የሰሩትን እንስራ ያልሰሩትን አንስራ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ይገርማሉ ሀዲስን ትርጉሙን ያዛባሉ፣ ይጠመዝዙታል ለምን ሲባል ቢድኣን ለማንገስ፡፡ እኛ ከሰሃባዎች በላይ አላህን አዋቂ፣ ፈሪም፣ አላህ ዘንድ እውነተኞችም አይደለንም፡፡ እኛ ከሰሃባዎች በላይ ነብዩ (ﷺ) አንወድም፣ አናከብርም፣ መስዋትም አልሆንም፡፡ ስለዚህ አደብ አድርገን እንቀመጥ፡፡
እንዲህ አይነት ጥፋቶችን ስናጋልጥ እናንተ በእድሜ ከጠገቡት ታላላቅ ኡለማዎች፣ ሙፍቲዎች፣ ዶክተሮች፣ ኡስታዞች ትበልጣላችሁን? ሲሉ ይጠይቃሉ
መልሱም ቀላል ነው
እነዚህ እናንተ ኡለማ ብላችሁ የምትከተሏቸው ሶዎች ከሰሃባዎች አላህን በመፍራት፣ አላህ እና መልክተኛውን በመውደድ፣ በእውቀት ይበልጣሉን?
አይበልጡም
ስለዚህ ሙፍቲም፣ ዶክተርም፣ ኡስታዝም፣ ሙነሺድም፣ ድቤ መቼም አርፈው ይቀመጡ፣ ዲን አይበጥብጡ፡፡
ኡማውን አይከፋፍሉ፡፡ ሺርክ እና ቢድኣን አያንግሱ፡፡
አላህ ከሺርክ፣ ከቢድኣ፣ ከዘረኝነት የፀዳ እውነተኛ አንድነት ይስጠን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
20.7K views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ