Get Mystery Box with random crypto!

ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ rovibookben — ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ rovibookben — ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @rovibookben
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 29.59K
የሰርጥ መግለጫ

Join @Rovibook
😎
<|>
/\
👢👢
መካሪ ከተገኘ ህይወት ቀላል ነው!!
ለማንኛውም ማስታወቂያ ነክ ጉዳዮች @RASNAMRUD ያናግሩን

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-05-13 11:00:57
23.5K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-15 10:25:43 ከመጻሕፍት ዓለም በ pinned « ️ ምርትና አገልግሎታችሁን እንዲሁም አዲስ የከፈታችሁትን ቻናል ወይም ግሩፕ ማስተዋወቅ ለምትፈልጉ ማስታወቂያ ቻናላችን ላይ በታላቅ ቅናሽ እንሰራለን 0938753747 በሰአት ለ1 ሰአት 30 ብር ለ2 ሰአት 50 ብር ለ4 ሰአት 80 ብር ለሙሉ ቀን 150ብር (ለ12ሰአት) * 500 view 25 birr 1k view 50 birr 2k view…»
07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-14 21:39:53 እንደምን አመሻችሁ የመፅሐፍት ዓለም ቤተሰቦች
ለትረካ ስራ በአካል ተወዳዳሪዎች የነበራችሁ ስለመጣችሁ ሁላችሁንም ከልብ እናመሰግናለን አሁን ውጤቶችሁን የምንገለገልበት ስዓት ነው ከዛ በፊት 2ነገሮችን ልበል
1ኛ በሆንላይን(@heny10)ላይ ከአሜን ባሻገር ገፅ 33 እያነባችሁ የላካችሁልኝ ልጆች ውጤት ገና ነው ስለዚህም ይሄ ውጤት እናንተን አያካትትም
2ኛ በአካል ስቱዲዮ መጥታችሁ ድምፃችሁን ወስደን የዛሬው ውጤት ላይ ያላለፋችሁ ግን መተረክ እምትፈልጉ ልጆች ደስ እያለን እንቀበላቸዋለን (ክፍያ ለጊዜው ባይኖረውም የምንቀጥራቸው ልጆች በሌሉበት ሠዓት እናንተ በክፍያ ግን ትሰራላችሁ )
ስለዚህም ከዚ በታች ያላችሁ ልጆች ለቀጣዩ ለመጨረሻ ዙር አልፋችኋል
1ኛ ቤተሌሄም ይመር
2ኛ ሀይለሚካሄል ዳንሄል
3 ዮናስ አይናለም
4ኛ ታደለ ሽመልስ
5ኛ እየሩሳሌም ሰለሞን
6ኛ ምስክር አበራ
7ኛ ሳሙኤል ጌታቸዉ
8ኛ ሱራፌል ሙልዬ
9ኛ ትዕግሥት አበበ
10 ብሩክ ጫላ
እናመሰግናለን ሁላችንም ስለዚህ ከላይ ስማችሁ የጠቀስኩት ቀጣይ ፈተና ይኖራል ስለሁሉም ከልብ እናመሰግናለን ።
ለማንኛውም ጥያቄ
+251938753747
@heny10
42.3K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-11 17:45:23 እንደምን አላችሁ
ለትረካ የተወዳደራችሁ ውጤት ስላዘገየን ትልቅ ይቅርታ እየጠየቅን አሀድ ማታ የምናሰማውቅ መሆኑን እንገልፃለን ።
31.2K views14:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-12-05 20:57:09 ሠላም የመፀሀፍት ዓለም ቤተሰቦች ከዚህ በፊት ያወጣነውን የመፅሐፍ ትረካ የስራ ማስታወቂያ ብዙ ሰዎች አመልክታችዋል እናም ለፈተና ያለፋችሁ ነገ ስለሆነ ጠዋት ከ4ሠዓት እስከ 5ሠዓት ድረስ 6ኪሎ መነን ትህምርት አካባቢ መጥታችሁ ፈተናውን መውሰድ ትችላላችሁ ቦታው ላይ ስትደርሱ በዚ ስልክ መደወል ትችላላችሁ +251938753747 ያልተመዘገባችሁ እና በትረካ መስራት እምተፈልጉ ዛሬ የመጨረሻ መመዝገቢያ ነው።

አርፋጅ አንቀበልም !!!
32.9K views17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-11-28 21:45:12
32.8K views18:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-10-30 07:52:43 ሰማሺኝ አለሜ ?
መሄድ እሚሉት ቃል ፥ ከሀገር የሰፋ
የትርጉም ኩታንኩት ፥ ጉንጭን እሚያለፋ
መሄድ ሲሉ ሰምተሽ !
እንደ ያሬድ ዜማ ፥ እንደ እግዜር ያለ እረፍት
እንደ ቀን ቅዳሴ ፥ እንደ ሌ'ት ማህሌት
የ 6 ቀን እድሜ ፥ በ 60 አመት ሀሳብ
ያ'ንድ ቅፅበት ቀመር ፥ እንደ ህያው ጥበብ
ያነፅነውን ፍቅር !
ባ'ንድ የስልክ ጩኸት ፥ ባ'ልፈልግህም ቃል
ፍቅርሽን ገፈሺኝ ፥ እኔነቴ ወልቋል
የመውደድ ግርማዬ ፥ በሀፍረት ተራቁቷል ።

ሰማሺኝ አለሜ ?
መሄድ የሚሉት ቃል ፥ የማጣት ታላቁ
የክፋቱ ክፋት ፥ ከኔ አንቺን ማራቁ
ባ'ንቺ 1 መሄድ ውስጥ ፥ ሺ ጥሎኝ የሄደ
ክንድሽ ያረፈበት ፥ ጎኔ እየነደደ
አቅሜ እንዳለልነበርሽ
ዛሬ አቅም ቢከዳኝ አካሌ እየራደ
መሄድሽን ረግማለሁ !
ደግሞ እጠይቃለሁ ?
በቅተኸኛል ያልሺን ፥ በባዶ ሀሳቤ
በተጎሳቆለው ፥ በድኩም ምናቤ
ቢመላለስብኝ
ልክ እንደ እግዚኦታ ፥ እንደ ቤተስኪያን ደውል፥ አንገቴን ደፋለሁ
አፍጦ ከሚያየኝ አቧራ መሬት ላይ ፥ መልስ እጠብቃለሁ

ሰማሺኝ አለሜ
ባ'ንቺ መሳቅ ቀኔ በርቶ ፥ በሀዘንሽ ሲጠፋብኝ
እውር ልቤ ባንቺነትሽ ፥ እንደሚያይ ሰው ሲዘልብኝ
ተዚያ ተቤተስኪን ፥
ከመላዕክት መቅደስ ፦ ከእግዜሩ ደጃፍ
እነኛን ጥዑም ቀን ፥
በመዋደድ ቅኔ ፥ አብረን ስናሳልፍ
እጅሽ እጄን ይዞ ፥ የተባባልነው ቃል
የልጆቻችን ስም ፥ ማን ትባል ማን ይባል
እንዳልነተረኩሽ ፥ እንዳልጨቀጨቅሺኝ
ዛሬ ግን የለሽም ፥
ብቻዬን ከ እግዜር ጋ ፥ ሄደሻል ጥለሺኝ !

ሰማሺኝ አለሜ ?
መሄዱንስ ሂጂ ፥ ብርሀን ይነጠፍልሽ
ይቃናልሽ መንገድ ፥ ክንፈ መላዕክት ይጠብቅሽ
ደግሜ ልሻለሁ ፥ ይቅናልሽ መንገዱ
ሊያገኝሽ ይጋደል ፥ ይሙትልሽ ወንዱ
ሌሊቱ እንዲረዝም ፥ እያልኩኝ ባልነጋ
እኔ ግን አለሁኝ ፥ ተኝቼ እየቃዠሁ በትዝታሽ አልጋ
ሰርክ እየደነገጥኩ ፥ ሰርክ እየባነንኩኝ
የመሄድሽን ህልም ፥
ልትመጣ ነው በሚል ፥ እየተረጎምኩኝ

እኔ ግን አለሁኝ
በትዝታሽ አልጋ ፥ ላልነቃ ተኝቼ
መሄድሽን ላልወቅስ ፥
ስላ'ንቺ ልሸነፍ ፥ ምዬ ተገዝቼ
35.3K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-10-29 22:09:28 AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" እውነተኛ ግርዶሽ

ሐሰተኛ ኑር ያደክማል ፣ እውነተኛ ኑሮ ከራስ ጋር ሰላም ያደርጋል፡፡ እውነተኛ ኑሮ የምትኖረው እግዚአብሔር እንዳለና ስራህን እንደሚመዝን ስታምን ነው፡፡ ነፃነት ጨዋነት ከሌለው ተዘዋዋሪ ባርነት ነው፡፡ ስጋን ከሚገርፉ ገዢዎች ነጻ አውጥተን ነፍስን በሚገዙ አጋንት እጅ የወደቀን ትውልድ ካፈራን የምናሳዝን ነን፡፡
"ከእባብ ጉድጓድ አምልጦ ዘንዶ ጉድጓድ" እንዲሉ አበው፡፡

ዓላማ የሌለው ጉዞ መንከራተት ነው፡፡
በውስጥህ ያለው የሕሊና ሕግ ፣ በመፅሐፍ ያለው የእግዚአብሔር ሕግ በልብህና በተግባርህ *#እንድትገልጠው የተሰጡህ ናቸው፡፡
ስለእግዚአብሔር ለማወቅ በፈለግህ መጠን ወዳጅነትህ እየጨመረ ይመጣል፡፡

#አምላክ_ላይሆኑ_አምላክህን_ያሳጡህን_አትርሳቸው፡፡

ፍልስፍናዎች ፣ ርዕዮተ አለሞች ፣ የበላይ አለቆች ፣ የጦር መሳሪያዎች ፣ የሀብት ጅልቦች ፣ *#ዘረኘነት እነዚህ ሁሉ አምላክ ላይሆኑ ስንቱን አምላክ እንዳሳጡት እወቅ፡፡
#ሰው_ላይሆኑ_ሰው_ያሳጡህንም_አትርሳ፡፡
አለመርሳት ማለት ማለትም ለቀጣዩ ተጠንቀቅ ማለት ነው፡፡

ኅሊናህን ቸል ብለህ ሰዎችን ወዳጅ ለማድረግ አታስብ፡፡ የጠፋ ማህበረሰብ የሚወለደው ከአሉታዊ ነፃነት ውስጥ ነው፡፡
አሉታዊ ነፃነት ልቅነት ነው፡፡ አዎንታዊ ነጻነትን ግን የመናገር ፣ የመኖር ፣ አሳብን የመግለጥ ፣ የወደዱትን ማመን ፣ የእኩልነት እግዚአብሔር የሰጠውን የፆታና የዕድሜ መብብ የሚያከብር ነው፡፡

#የተፈፀሙ_ነገሮች_የተጀመሩ_ነገሮች_ናቸውና
ለመጀመር ተነሳ፡፡ የተጀመሩት ይፈፀማሉና ፍፄሜውን አትፍራ፡፡ ቅዱስ መልዓክ ላንተ ያስፈልግኃል ለደካማውም ሰው አንተ ታስፈልገዋለህ፡፡ ከቆመው መልዓክ የወደቀውን ሰው ሊፈልግ እግዚአብሔር ሰው ሆነ፡፡
የአምላክ እናትን ባሰብክ ጊዜ እግዚአብሔር ለሰው የሰጠውን የላቀ ክብር ትረዳለህ፡፡

የህሊናን ድምፅ ጠንቅቀህ የምትመሰርተው ወዳጅነት ራስን ማጥፋት ነው፡፡ በነፍስህ ዋስትና የሌለበት ሀብት በሬሳ አጠገብ እንደተቀመጠ ጥሩ መዓዛ ያለው ምግብ ነው፡፡ ተገፋን ብለው ወደ አንተ ሚመጡ ሰዎች ምን ሰርተው ወደአንተ እንደ መጡ አጥና፡፡ ጅብ የማያቁት አገር ሂዶ ቁርበት አንጥፋልኘ ይላል" ይባላል፡፡ ከሁሉ ፀያፍ ነገር ሃይማኖትለዋጭነት እንደሆነ እወቅ፡፡

እግዚአብሔር በድንጋይ ጽላት ላይ ቃሉን ቀርጾ የሰጠን የእግዚአብሔር ቃል ዘመን የማይሽረው መሆኑን ሊያስተምረን ነው፡፡ ስነምግባር ስታጣ የምታሳድበው እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን አሳዳጊዎችንህም ነው፡፡

#የመጨረሻው_ድህነት_እግዚአብሔርን_ማጣት ነው፡፡

#የመጨረሻ_ብልጥግናም_እግዚአብሔርን_ማግኘት_ነው፡፡

እንደገና የቀረ የለምና አትመካ ፣ እንደ መሸ የቀረ ሌሊት የለምና አትሸማቀቅ፡፡
የምትችለውን ማድረግ የማትችለውን ለማድረግ መንደርደሪያ ነው፡፡
እውነተኛ የሀብት ውድድር በማጠራቅ ሳይሆን በመስጠት ከሆነ ደስታ አለው፡፡

#በእግዚአብሔር_መንግስት_ምን_ያህል_አጠቀምክ_ሳይሆን_ምንያህል_ሰጠህ_ትባላለህ፡፡

የማይሰጥ ባለጠጋ ድሃ ነው፡፡
ደሃ ሁለት አይነት ነው፡፡
የገንዘብና የቸርነት ድሃ፡፡
ከቸርነት ድህነት የገንዘብ ድህነት ይሻላል፡፡

ከባድ እስር ቤት በራስ አመለካከት መታጠር ነው፡፡
የሚያቆስለው ሰንሰለትም የመሰስትም እጅ ነው
#የጨለማም_ወህኒም_ማፍቀር አለመቻል ነው፡፡
ዓለም ማለት በጎሬህ መጠን በሰፈርህ ልክ ከመሰለህ ዘረኛ ሆነኃል ማለት ነው፡፡
ዘረኘነት ከእግዚአብሔር ጋር ጦርነት መግጠም ነው፡፡ ምክንያቱም ስለ ዘሩ የምትጠላው ያ ሰው ከዚያ ዘር ለመውለድ ያቀረበው አሳብ የለምና፡፡

#እውነተኛ_እውርነት_ፀሀይን_ሳይሆን_የፀሀይን_ጌታ_ማየት_አለመቻል_ነው፡፡"

መልካም ምሽት
@jahABP ነኘ

መልካምነት ደግነት በተግባር እንግለፃቸው

ከትላንትናው መፅሐፍ ላይ ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደቀነጨብኩት

*# ምልክት ያለባቸውን እኔ እንደጨመርኩት ልብ ይሏል

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
25.1K views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-10-29 00:00:14 AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" የፍቅር ትንታኔ

እንኳን ምድራዊ ሀብትና እውቀት ይቅርና ሰማያዊ ጸጋዎች ያለፍቅር ከባድ ናቸው፡፡
ፍቅርን ስትይዝ ሁሉንም ጸጋ ያዝክ ማለት ነው፡፡
የሃይማኖት ፍቅርና ጉልላት ፍቅር ነው፡፡
ፍቅር ካለህ እግዚአብሔር ባንተ ልብ አለ፡፡
አንተም በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ አለህ፡፡

ፍቅር ድል አለው፡፡ ስለፀጋ ስጦታዎች ብዙ ጭቅጭቅ አለ ስለሚበልጠው ጸጋ ስለፍቅር ግን ስብከት ጠፍቷል፡፡ ስለፈውስ ብዙዎች ይለምናሉ ነፍስን ስለሚፈውሰው ፍቅር ግን አይፀልዩም፡፡
ማንኛውመ መንፈሳዊ ነገር በእውቀት በእምነት በፍቅር ካልተደረገፈ ሀጢያት ነው፡፡

ትንፋሽ ድንገት የሚቋረጥ ሲመስልህ ፣ የልብህ ምቾት የቀዘቀዙ መስሎ ሲሰማህ ፣ ተስፋህ ጭልጥ ሲልብህ የምትድነው በፍቅር ብቻ ነው፡፡
እንጨት በምስጥ ፣ እህል በነቀዝ ፣ ልብስ በብል ይበላል ፣ ሰውን ጥላቻ ይገዘግዘዋል፡፡
ሌሎች በኃይል እንዲሰሩ ሞተሩ ፍቅር ነው፡፡

ፍቅር ከሌለ ሰማዕትነት ሊኖር አይችልም፡፡
በየዕለቱ ሰማዕትነት ላይኖር ይችላል፡፡
በየዕለቱ መስዋዕትነት ግን አለ እርሱም ጥላቻን እንቢ ማለት ነው፡፡ በሁሉም ቦታ ፣ በሁሉም ደረጃ ፣ በሁሉም ፀጋ ውስጥ በሁሉም ዘመን ደግሞም ለዘለዓለም የሚፈለግ ፍቅር ብቻ ነው፡፡
በፍቅር የማይቃጠሉ ልቦች ወንድማቸውን ለመስቀል ይጨክናሉ፡፡

ቤተክርስቲያን የቆመችበቶ ምሶሶ ፍቅር ነው ፣ ያለፍቅር ትወድቃለች፡፡

ፍቅር ራሳችንን በሰው ውስጥ ሰዎችን በራሳችን ውስጥ የምናይበት መስታወት ነው፡፡
ፍቅር ያላቸው ሌሎችን የማስተካከል አቅም አላቸው፡፡
ፍቅር በቀላሎች ሰፈር ያላት ስያሜ ምስኪንነት ፍርሃት ነው፡፡
መንገዶችን ከመስራት ፍቅርን መገንባት ይቀድማል፡፡
የተሰሩት መንገዶች በጥላቻ ይዘጋሉ፡፡
ትልቁ ርዕዮተ አለም ፣ የማይከሽፍ መሳሪያ ፍቅር ብቻ ነው፡፡
ፍቅር ትልቁ ስጦታ ፣ ትልቁ መንገድ ፣ ትልቁ መሪ ነው፡፡

ዓይን ያለ ፍቅር ምን አገባኘ ይላል፡፡ ጆሮ ያለ ፍቅር ከሰማ ይፈርዳል፡፡ ምላስ ያለፍቅር ከወጣ ይሰብራል፡፡ እጅ ያለ ፍቅር ከተዘረጋ ይጥላል፡፡
እግር ያለ ፍቅር ከሔደ ድልድይ ያፈርሳል፡፡
ፍቅር የሌለው ሰማዕት ክርስቶስን አላወቀምና በከንቱ ይሞታል፡፡ ብዙ ነገሮች እንደጎደለን ብንናገርም በዋናነት የጎደለንፍቅር ነው፡፡

ፍቅርበመጨረሻው ዘመን ይቀዘቅዛል እንጂ አይጠፋም፡፡
ያለፍቅር የተሰበኩ ነፍሰ ገዳይ ይሆናሉ፡፡ ለማፍቀር የልብ ፈቃድና የእግዚአብሔር ፍቅር ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
ፍቅር በግልፅነት የምትከብር ናት ፍፁም የምትሆነውም ፍርሃትን ስታሸንፍ ነው፡፡

#ፍቅር_እራሷ_ጌጥ_ናትና_ጌጥ_አትፈልግም፡፡
#ፍቅር_ጽንፍ_የለሽ_ናትና_ዘረኘነት_አይስማማትም፡፡
#ተብራርቶ_ያላለቀ_ትንታኔ_ፍቅር_ብቻ_ነው፡፡
በፍቅር ያጌጡ በወርቅ ከተኝቆጠቆጡ ይበልጣሉ፡፡

ምኞት ዳርቻ ጥማትም እርካታ የሚያገኘው በፍቅር ብቻ ነው፡፡ ያለፍቅር የተዘረጉ ምፅዋቶች ከዱላ አይተናነሱም፡፡
#ኅሊናውን_አጉድለን_ሆዱን_የሞላንለት_ከሰጠነው_የሰረቅነው_ይበዛል፡፡

ፍቅር ሁሉም የሚሰጠው ምፅዋት ነው፡፡
ፍቅርን የማይሰጥ ድሃ የማይቀበል ሀብታምም የለም፡፡ ጎዶሎዎቾ መልካም የሚሆኑት በፍቅር ብቻ ነው፡፡
ሩጫህን የጀመርከው ያለ ጭብጨባ ብቻህን መሮጥ የጀመርህ ቀን ነው፡፡

#የታየህን_እይ_እንጂ_የሚያዩህን_አትይ_ትወድቃለህና፡፡"

የሆነ መፅሐፍ ሳነብ አገኘሁትና ላካፍላቹ ብዬ አሰብኩኘና እንዲህ ለንባብ እንዲመች አድርጌ ቀነጨብኩት፡፡

መፅሐፉን ርዕስ የፈለገ በውስጥ መስመር ያናግረኘ፡፡

በፍቅር እንኑር እላለሁ

@jahABP ነኘ መልካም አዳር ተመኘሁ


@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
21.8K views21:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ