Get Mystery Box with random crypto!

AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN ' እውነተ | ከመጻሕፍት ዓለም 🇪🇹

AB PHOTOGRAPHY & GRAPHIC DESIGN

" እውነተኛ ግርዶሽ

ሐሰተኛ ኑር ያደክማል ፣ እውነተኛ ኑሮ ከራስ ጋር ሰላም ያደርጋል፡፡ እውነተኛ ኑሮ የምትኖረው እግዚአብሔር እንዳለና ስራህን እንደሚመዝን ስታምን ነው፡፡ ነፃነት ጨዋነት ከሌለው ተዘዋዋሪ ባርነት ነው፡፡ ስጋን ከሚገርፉ ገዢዎች ነጻ አውጥተን ነፍስን በሚገዙ አጋንት እጅ የወደቀን ትውልድ ካፈራን የምናሳዝን ነን፡፡
"ከእባብ ጉድጓድ አምልጦ ዘንዶ ጉድጓድ" እንዲሉ አበው፡፡

ዓላማ የሌለው ጉዞ መንከራተት ነው፡፡
በውስጥህ ያለው የሕሊና ሕግ ፣ በመፅሐፍ ያለው የእግዚአብሔር ሕግ በልብህና በተግባርህ *#እንድትገልጠው የተሰጡህ ናቸው፡፡
ስለእግዚአብሔር ለማወቅ በፈለግህ መጠን ወዳጅነትህ እየጨመረ ይመጣል፡፡

#አምላክ_ላይሆኑ_አምላክህን_ያሳጡህን_አትርሳቸው፡፡

ፍልስፍናዎች ፣ ርዕዮተ አለሞች ፣ የበላይ አለቆች ፣ የጦር መሳሪያዎች ፣ የሀብት ጅልቦች ፣ *#ዘረኘነት እነዚህ ሁሉ አምላክ ላይሆኑ ስንቱን አምላክ እንዳሳጡት እወቅ፡፡
#ሰው_ላይሆኑ_ሰው_ያሳጡህንም_አትርሳ፡፡
አለመርሳት ማለት ማለትም ለቀጣዩ ተጠንቀቅ ማለት ነው፡፡

ኅሊናህን ቸል ብለህ ሰዎችን ወዳጅ ለማድረግ አታስብ፡፡ የጠፋ ማህበረሰብ የሚወለደው ከአሉታዊ ነፃነት ውስጥ ነው፡፡
አሉታዊ ነፃነት ልቅነት ነው፡፡ አዎንታዊ ነጻነትን ግን የመናገር ፣ የመኖር ፣ አሳብን የመግለጥ ፣ የወደዱትን ማመን ፣ የእኩልነት እግዚአብሔር የሰጠውን የፆታና የዕድሜ መብብ የሚያከብር ነው፡፡

#የተፈፀሙ_ነገሮች_የተጀመሩ_ነገሮች_ናቸውና
ለመጀመር ተነሳ፡፡ የተጀመሩት ይፈፀማሉና ፍፄሜውን አትፍራ፡፡ ቅዱስ መልዓክ ላንተ ያስፈልግኃል ለደካማውም ሰው አንተ ታስፈልገዋለህ፡፡ ከቆመው መልዓክ የወደቀውን ሰው ሊፈልግ እግዚአብሔር ሰው ሆነ፡፡
የአምላክ እናትን ባሰብክ ጊዜ እግዚአብሔር ለሰው የሰጠውን የላቀ ክብር ትረዳለህ፡፡

የህሊናን ድምፅ ጠንቅቀህ የምትመሰርተው ወዳጅነት ራስን ማጥፋት ነው፡፡ በነፍስህ ዋስትና የሌለበት ሀብት በሬሳ አጠገብ እንደተቀመጠ ጥሩ መዓዛ ያለው ምግብ ነው፡፡ ተገፋን ብለው ወደ አንተ ሚመጡ ሰዎች ምን ሰርተው ወደአንተ እንደ መጡ አጥና፡፡ ጅብ የማያቁት አገር ሂዶ ቁርበት አንጥፋልኘ ይላል" ይባላል፡፡ ከሁሉ ፀያፍ ነገር ሃይማኖትለዋጭነት እንደሆነ እወቅ፡፡

እግዚአብሔር በድንጋይ ጽላት ላይ ቃሉን ቀርጾ የሰጠን የእግዚአብሔር ቃል ዘመን የማይሽረው መሆኑን ሊያስተምረን ነው፡፡ ስነምግባር ስታጣ የምታሳድበው እግዚአብሔርን ብቻ ሳይሆን አሳዳጊዎችንህም ነው፡፡

#የመጨረሻው_ድህነት_እግዚአብሔርን_ማጣት ነው፡፡

#የመጨረሻ_ብልጥግናም_እግዚአብሔርን_ማግኘት_ነው፡፡

እንደገና የቀረ የለምና አትመካ ፣ እንደ መሸ የቀረ ሌሊት የለምና አትሸማቀቅ፡፡
የምትችለውን ማድረግ የማትችለውን ለማድረግ መንደርደሪያ ነው፡፡
እውነተኛ የሀብት ውድድር በማጠራቅ ሳይሆን በመስጠት ከሆነ ደስታ አለው፡፡

#በእግዚአብሔር_መንግስት_ምን_ያህል_አጠቀምክ_ሳይሆን_ምንያህል_ሰጠህ_ትባላለህ፡፡

የማይሰጥ ባለጠጋ ድሃ ነው፡፡
ደሃ ሁለት አይነት ነው፡፡
የገንዘብና የቸርነት ድሃ፡፡
ከቸርነት ድህነት የገንዘብ ድህነት ይሻላል፡፡

ከባድ እስር ቤት በራስ አመለካከት መታጠር ነው፡፡
የሚያቆስለው ሰንሰለትም የመሰስትም እጅ ነው
#የጨለማም_ወህኒም_ማፍቀር አለመቻል ነው፡፡
ዓለም ማለት በጎሬህ መጠን በሰፈርህ ልክ ከመሰለህ ዘረኛ ሆነኃል ማለት ነው፡፡
ዘረኘነት ከእግዚአብሔር ጋር ጦርነት መግጠም ነው፡፡ ምክንያቱም ስለ ዘሩ የምትጠላው ያ ሰው ከዚያ ዘር ለመውለድ ያቀረበው አሳብ የለምና፡፡

#እውነተኛ_እውርነት_ፀሀይን_ሳይሆን_የፀሀይን_ጌታ_ማየት_አለመቻል_ነው፡፡"

መልካም ምሽት
@jahABP ነኘ

መልካምነት ደግነት በተግባር እንግለፃቸው

ከትላንትናው መፅሐፍ ላይ ለንባብ እንዲመች አድርጌ እንደቀነጨብኩት

*# ምልክት ያለባቸውን እኔ እንደጨመርኩት ልብ ይሏል

@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD
@ABPGD @ABPGD @ABPGD