Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ግጥም ና ታሪክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ourpoemsandhistorys — የኛ ግጥም ና ታሪክ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ourpoemsandhistorys — የኛ ግጥም ና ታሪክ
የሰርጥ አድራሻ: @ourpoemsandhistorys
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 107

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-06-16 21:46:45
85 views18:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 19:45:22 #በዝናብ ቅጠሪኝ

አማልዱኝ ባልልም አስታራቂ ልኬ
ባልማፀንሽም ፊትሽ ተንበርክኬ
ዕንባዬ እንዳይታይ ካንቺ ተደብቄ
አነባለሁ ዛሬም ዝናቡን ጠብቄ

ልቤ በስቃይ ጣር ብሶቱን ሲያሰማ
ሀዘኔ ተሰምቶሽ ልብሽ እንዳይደማ
ቀኑ ጨላልሞልኝ ክረምቱ እስኪገባ
መጥተሽ አትጠይቂኝ ሆድሽም አይባባ

ዝናብ የኔን ብሶት ሀዘኔን ባያጥበው
ሳለቅስ እንዳታዪ ዕንባዬን ይጋርደው
በጉንጬ 'ሚፈሰው ዝናብ እንዲመስልሽ
ሁሌ ክረምት ይሁን ጉዳቴ አይታይሽ

ውዴ፦
ጥፋቴ ሲገባኝ ዛሬ ተመልሼ
ነይልኝ አልልም እፊትሽ አልቅሼ
አዲሱ ኑሮሽን ልረብሽ በ'ንባዬ
በበጋ አልጣራም 'ናፍቀሽኛል' ብዬ

ሳለቅስ እንዳታዪኝ
ሁሌ በያመቱ በክረምት ነዪልኝ
የናፈ'ኩሽ እንደሁ
ጉርምርምታው ሲብስ በክረምት ጠይቂኝ
አንቺን ያገኘሁ 'ለት
ከንፈሬ ተላቆ ስስቅ እንድታዪኝ
ቀን የጨለመ 'ለት
ዶፍ እየወረደ ዝናብ ውስጥ ጠብቂኝ።
-------------------------
አንዱዓለም ኪዳኔ
"በዝናብ ቅጠሪኝ"
የግጥም መድብል

https://t.me/ourpoemsandhistorys
95 views16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-31 18:28:41
96 views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 19:04:23 እወድሻለሁ ልልሽ ቀጠሮ ነበረኝ
ግን ጊዜውን አላምነው አሁን በላት አለኝ
አሁን ወድሻለሁ
ወድሻለሁ ብዬ ልነግርሽ ብመጣ በክንፍ በፈረስ
ለነፍስሽ ይወደኛል በይው ከጎንሽ እስክደርስ
አሁን ወድሻለሁ ቶሎ ቶሎ ስሚኝ
ህይወት ሆኗል መድሎ
ሞልቷል ያልኩት ጎድሎ
ህያው ያልኩት ሞቷል
የገነነው ወድቆ
የገዘፈው ደቆ
ሀሳብ ንፋስ ሆነ
ጊዜ ይሉት ዑደት ሰው እያተነነ
እኔ ጊዜ የለኝ
የሚሞት ስጋና ህያው ፍቅር አለኝ
ቶሎቶሎ ስሚኝ
ቶሎቶሎ ሳሚኝ
በቀጣዩ ግጥም ማፍቀሬን ልንገርሽ ያልኩትን ትቻለሁ
እሱ ጋር ሳትደርሺ ድንገት ትን ቢላት እያልኩ እፈራለሁ
ጊዜን እያሰላው
ለምን እሸሻለው
ትላንትም አይደለም
ነገንም አይደለም
ዛሬንም አይደለም
አሁን እወድዳለሁ
አሁን ናፍቀሽኛል
አሁን አሰኘሽኝ
አሁን ባገባሁሽ
አሁን አሁን አሁን
አሁን እንፋቀር
ቀጣዩን ማን ያውቃል ከወልደ እግዜር በቀር

(ገጣሚ:- ኤልያስ ሽታሁን
ተቀንጭቦ የተወሰደ ግጥም ነው )

@besye_getm
100 views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-23 21:51:04
89 views18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 20:55:52 ተፈጥሮን ከጅምር አነፃፅሮ ካንቺ
መሳይሽን ሲያጣ
ከውኖ አስቀመጠው ሰማይን ያንቺ እጣ
ገጣሚውም አለ በሰማይ ሲመስል
ከፀሃይ ጨረቃም ትበልጫለሽ ብሎ ምንም አንቺን ቢስል
ሰማዩም ይቅርብኝ ወደኔ ላቅርብሽ ምድሬ ናት ብዬ
እደማልዳስስሽ እደማላገኝሽ እያወቀ ልቤ
ግና
ናፍቆትሽን ችዬ
እስከመቼ ልወድ እስከመች ላፍቅርሽ በምናቤ ስዬ
ግና
ለኔ የኔ ቆንጆ ለኔ ግራ ጎኔ
የማርቀኝ ከቶ ማጠፋ ከጎኔ
የነፍስ ያህል ዋጋ የሠጠዋት ከኔ
ከሩቅ ሆና ገና ሆድ የማታባባ
ማምሸቱን አይቼ ጥያት የማልገባ
የማትለዋወጥ ወራትን ጠብቃ
የማትቀያየር ሲላት የማጠቁር ሲላት የማትደምቅ
የራስን ሳይኖሩ ለሰው ሂወት መስጠት ያስተማረች ለኔ
ካምላክ የተገኘች አየር ናት ሄዋኔ

ርዕሴ እርሷ ነች

ገጣሚ ዳንኤል ሞላ @Ilvall
89 views17:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 19:51:49 የኛ ግጥም ና ታሪክ pinned «የመንፈስ -አፍቃሪ ----------------------------------------------- ከዲማው ጊዮርጊስ ስፈልግሽ ኖሬ ቢጫ እንደለበሽ ሰማሁኝ በወሬ ቡታንታዬን ትቼ የገበሬ ልብሴን ዘር መዝራት ተስኖኝ ከድቼው ፈረሴን በምስል አይቼሽ ከማር እስከ ጧፍ ከገዳሙ ስፍራ ዋንጫ ሲሰለፍ ማሬ ማሬ እያልኩኝ ስልሽ ከርሜ …»
16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 19:51:34 የመንፈስ -አፍቃሪ
-----------------------------------------------

ከዲማው ጊዮርጊስ ስፈልግሽ ኖሬ
ቢጫ እንደለበሽ ሰማሁኝ በወሬ
ቡታንታዬን ትቼ የገበሬ ልብሴን
ዘር መዝራት ተስኖኝ ከድቼው ፈረሴን
በምስል አይቼሽ ከማር እስከ ጧፍ
ከገዳሙ ስፍራ ዋንጫ ሲሰለፍ
ማሬ ማሬ እያልኩኝ ስልሽ ከርሜ
ከቴዲ አፍሮ ዘፈን አየሁሽ ደግሜ
ጧፉን በላዬ ላይ ወርውሬ ከልብሴ
ልቤ ፍቅር ይዞት ከገዳም መነኩሴ
ንቤ ገዳም ገብታ ብርሀን ተጎናፅፋ
ቤቷ ልመልሳት ቀሚሷን ስሰፋ
ዋሻዋን ቀይራ ሲኖዳ ዩሀንስ
ፈውሴ እንዳይሆን ፍቅሯ መንናብኝ ሳልደርስ
አቅጣጫ ቀይሬ ከወሎ መንደር
ሸዋ ከ ሩፋኤል ስፈልግ እሷን
ለካ የሰው ሆና የገዳም ድንግል
ፊቷ ጥለት መስሎ የብር መስቀል
ለበስኩት ቀሚሷን ቀለሙን ቀይሬ
የማልኩበትን ልብስ ቢጫውን አጥቁሬ
ብራናዬ እንዳላልኩ ሰይሜሽ በኩራት
ማር ጧፋ ሆነ ገባ ከመቅደሱ ስርዐት
ሰከላ እያልኩኝ ዲማውን እርቄ
ራሴው ለ ራሴው የመሰናበቻ ምርቃት መርቄ
የፀበል ዳር ሆና ለፈውስ ያልታደለች
ዋርካ ሸፍኖብኝ በምኞቴ የቀረች
ሰብልዬ እያልኩኝ ተስፋ ባጣ ጥሪ
ሆኜ ቀርቻለሁ የመንፈስ አፍቃሪ

ገጣሚ: አበባው ሀይሉ
70 views16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 20:31:10 #ከፍቅር_በላይ
:
:
አፍቅሮኛል እያልሽ ያወጋሽው ወሬ፣
ስንት ጆሮ አልፎ ከኔም ደርሷል ዛሬ።
በኔ መውደድ ታስሮ መላወስ ከብዶታል፣
ያልሺውም ንግግር ከጆሮዬ ገብቷል።
ከራሴው ሳትሰሚ ሳታውቂው እርግጡን፣
የብብትሽን ጣልሽ ስታልሚ ቆጡን።
ሁሉን ሰምቻለው ማን ምንስ እንዳለኝ፣
አንቺ አፍ እንዳለሽ እኔም ጆሮ አለኝ።
:
:
ምንም ይሁን ምንም፣
ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም፣
እውነቱ ግን ይህ ነው እኔ አላፈቅርሽም፣
እኔስ አልወድሽም።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ከቤትሽ ፊት ለፊት ከዋርካው ጥላ ስር ሁሌ እቀመጣለው፣
ዕድል ያልቀናኝ ለት ያላየውሽ እንደው ጭንቄን አምጣለው፣
ያየውሽም ከሆን እንደ ረጋ ወተት በደስታ እናጣለው።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ያ የሰፈራችን ጠብደሉ ጎረምሳ በጨዋታ መሀል ሲሰድብሽ ስሰማ፣
በጣም ተናድጄ ፈንክቼው ሮጬያለው ጠብቄ ጨለማ።
ደግሞም የሆነ ጊዜ በመንገድ እያለፍሽ አንዱ ጓደኛችን የለከፈሽ ለታ፣
ደም ፋላቴ መቶ አዝንቤበታለው የቡጢ ጋጋታ።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ሳገኝሽ ስቄያለው ሳጣሽም ከፍቶኛል፣
አንቺን ብቻ እያየው በመንገድ ሳቀናም ስልክ እንጨት ገጭቶኛል፣
ትረፍ ሲለኝ ከላይ መኪናም ስቶኛል።
:
:
እርግጥ ነው አልክድም...
ጎኔና ፍራሼ የገጠሙ ጊዜም በህልሜ አይሻለው፣
ስምሽን ሲጠሩት የጠሩኝም መስሎኝ ስንቴ አቤት ብያለው፣
አዝነሽ ያየው ቀንም ደም እንባ አልቅሻለው።
:
:
ይህንም አልክድም...
ምንም ቢሆን ምንም፣
እኔ አንቺን አልወድም።
:
:
አፍቅሮኛል ብለሽ ስሜን ስላጠፋሽ አላዘንኩብሽም፣
እውነት እውነት ስሚኝ አላፈቀርኩሽም።
:
:
ይህ ፍቅር አይደለም፣
ይህ መውደድ አይደለም፣
ለጓደኞችሽም ዳግም ስታወጊ፣
ከዚህ የተሻለ ሌላ ቃል ፈልጊ።
አፍቅሮኛል ብለሽ ፍቅሬን አትግደዪ፣
ከፍቅር በላይ ነው ያፈቀረኝ በዪ፣
ከመውደድ በላይ ነው የወደደኝ በዪ።
71 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-06 18:03:22
ገጣሚ አስታወሰኝ ረጋሳ
98 viewsedited  15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ