Get Mystery Box with random crypto!

ተፈጥሮን ከጅምር አነፃፅሮ ካንቺ መሳይሽን ሲያጣ ከውኖ አስቀመጠው ሰማይን ያንቺ እጣ ገጣሚውም አለ | የኛ ግጥም ና ታሪክ

ተፈጥሮን ከጅምር አነፃፅሮ ካንቺ
መሳይሽን ሲያጣ
ከውኖ አስቀመጠው ሰማይን ያንቺ እጣ
ገጣሚውም አለ በሰማይ ሲመስል
ከፀሃይ ጨረቃም ትበልጫለሽ ብሎ ምንም አንቺን ቢስል
ሰማዩም ይቅርብኝ ወደኔ ላቅርብሽ ምድሬ ናት ብዬ
እደማልዳስስሽ እደማላገኝሽ እያወቀ ልቤ
ግና
ናፍቆትሽን ችዬ
እስከመቼ ልወድ እስከመች ላፍቅርሽ በምናቤ ስዬ
ግና
ለኔ የኔ ቆንጆ ለኔ ግራ ጎኔ
የማርቀኝ ከቶ ማጠፋ ከጎኔ
የነፍስ ያህል ዋጋ የሠጠዋት ከኔ
ከሩቅ ሆና ገና ሆድ የማታባባ
ማምሸቱን አይቼ ጥያት የማልገባ
የማትለዋወጥ ወራትን ጠብቃ
የማትቀያየር ሲላት የማጠቁር ሲላት የማትደምቅ
የራስን ሳይኖሩ ለሰው ሂወት መስጠት ያስተማረች ለኔ
ካምላክ የተገኘች አየር ናት ሄዋኔ

ርዕሴ እርሷ ነች

ገጣሚ ዳንኤል ሞላ @Ilvall