Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ግጥም ና ታሪክ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ourpoemsandhistorys — የኛ ግጥም ና ታሪክ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ourpoemsandhistorys — የኛ ግጥም ና ታሪክ
የሰርጥ አድራሻ: @ourpoemsandhistorys
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 107

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-14 16:36:54 ....................

አንዳንዴ ሀሳባችን ወደ የት እንደሚሄድ አናውቀውም ለሆዳችን ቀን በቀን ምግብ እንደምንመግበው ሁሉ አዕምሮአችንም ከቀን ወደ ቀን ስልጠናዎች እንዲሁም ፍሬ ነገሮች ያስፈልጉታል ስንቶቻችን ነን እዚህ ምድር ላይ ለሆነ አላማ እንደተፈጠርን የምናውቀው? ስንቶቻችን ነን ስለተፈጠርን ብቻ እየኖርን ያለነው? ስንቶቻችን ነን ህይወታችን ውስጥ የተሰጡንን ሴኮንዶች እየተጠቀምንባቸው ያለነው?


ከምንም አይነት ነገር በፊት እራሳችን ላይ መስራት ያስፈልገናል።

ልናማክርሽ እንፈልጋለን እንዲሁም እኔ ከአሁን ጀምሮ የእውነት የሚገባኝን ህይወት መኖር እንፈልጋለው ለምትሉ እህት ወንድሞቼ ከስር ባለው የቴሌግራም እንዲሁም ኢንስታ አካውንቴ inbox ልታናግሩኝ ትችላላቹ

Telegram...... @Nizan5
Instagram...... nizan9336

######growth######
######Life########
11 views13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 20:42:55 እንደ ዝሆን ድዳ አትሁን…

የዝሆን ግልገል ከልደቱ ጀምሮ በትንሽ ቦታ ውስጥ እንዲሆን ይሰለጥናል። አሰልጣኙ መሬት ላይ በተተከለ እንጨት ላይ የትንሹን ዝሆን እግር በገመድ ያስረዋል። ይህም የትንሹ ዝሆን የምቾት ቀጠና ነው። ትንሹ ዝሆን በመጀመሪያ አከባቢ ገመዱን ለመበጠስ ይሞክራል። ገመዱ ግን ጠንካራ በመሆኑ ትንሹ ዝሆን ገመዱን መበጠስ እንደማይቻል ይማራል። በገመዱ ርዝመት በተለካ አካባቢ ብቻ ተወስኖ መኖር ይማራል።

ዝሆኑ በቀላሉ ገመዱን ለመበጠስ የሚችልበት እድሜ ላይ ሲደርስም ለመበጠስ አይሞክርም። ምክንያቱም ገና በልጅነቱ ገመዱን መበጠስ እንደማይችል ተምፘልና። በዚህ መንገድ ትልቁ ዝሆን በጣም በቀጭን ገመድ መታሰር ይችላል።

ምናልባት ይህ አንተን ይገልፅህ ይሆናል። ልክ ዝሆኑን ባሰረው እይነት ቀጭን ገመድ አሁንም በምቾት ቀጠናህ ውስጥ ታስረህ ይሆናል። እነዚህ ያሰሩህ ቀጫጭን ገመዶች ደግሞ በልጅነትህ የተቀበልካቸው እንቅፋት የሆኑ እምነቶችና ምስሎች ናቸው። ይህ የሚገልፅህ ከሆነ መልካም ዜና አለ። ይኸውም የምቾት ቀጠናህን መለወጥ ትችላለህ። እንዴት ለዚህ ሶስት የተለያዩ መንገዶች አሉ፤

የምትፈልገውን እንዲገኘህ፤ እንደ ስራህና ነገሮች በፈለግከው መነገድ እያሄዱልህ እንደ ሆኑ ማረጋገጫና አውንታዊ የራስ ጋር ንግግር መጠቀም ትችላለህ።
የምትፈልገውን ስታገኝ፤ ስትሰራና ስትሆን ያለ አዲስ አስገዳጅ ኃይል ውስጣዊ ምስል መፍጠር ትችላለህ።
በቀላሉ ባህርይህን መቀየር።

እነዚህ አቀራረቦች ከአሮጌው የምቾት ቀጠናህ ያወጡሀል።
10 views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-07 22:16:28 አጠር ያለ አስተማሪ መልዕክት

አንድ ሰው ነበር በባህር ብቻውን በመርከብ እየተጓዘ እያለ
በመዓበል ተመታና መርከቡ ተሰባብሮ በባህሩውሰጥ ሰመጠች ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ  ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል ,,,,,,,,ምግብ ዓሳ እያጠመደ እየተመገበ ብዙ ቆየ

አንድ ቀን ዓሳ ሊያጠምድ ወደ ባህሩ እየሄደ በመሀል እዛች ባህር ላይ ጭስ ይሸተዋል ዞር ብሎ ሲመለከት
ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው ,,,,,,,እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዋን ሊያድናት አልቻለም ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል አለቀሰ ፈጣሪውን ወቀሰ

እንዴት እዚህ ባህር ላይ ለብቻዬ ጥለከኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለኸኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራዋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለክ ብሎ አለቀሰ አማረረ,,,,,,,, ከደቂቃዎች በኋላ አንድ ድምፅ ሰማ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ ተደሰተ ,,,,,, የመርከቡ ሰዎችም መጥተው ጭነው ወሰዱት
ከዚያም ለመርከብ ሰዎች ጠየቃቸው !
እንዴት አገኛችሁኝ እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት መጣችሁ ?

አላቸው ,,,,, መርከበኞቹም እኛም በዛኛው በኩል ዞረን እየሄድን ነበር ከዚያ በኩል ጭስ አየንና እዚህ ሰው ይኖራል ብለን መጣን አንተ አገኘን አሉት። አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃይ ልታወጣኝ ፈልገህ ነው ትንሿ ጎጆዬን ያፈረስከው  ወደ ትልቁ ቤቴ ልትወሰደኝ ነው አለ

አንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣ ሲበላሽብን ፈጣሪንም ሰውንም ስናማርር እንኖራለን ግን ካጣነው ነገር ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን በችግራችን ጊዜ መጠጋት
ያለብንን አንድዬን እንረሳለን ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪውን እንኮንነዋለን ።ያጣነውን የሰጠን እግዚአብሔርን አእምሯችን ከሚያስበው በላይ ሊሰጠን እንደሚችል ማመን አለብን እግዚአብሔርን እንደ ቅዱሳን በእምነት መፅናትን ያድለን አሜን

@eotcy
@eorcy
@eotcy
7 views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 20:16:55 የወደደ ፍቅሩን
ሸረሪትም ድሩን
እንደማያስነካ
እንዲዚያ ነኝ በቃ::

ወዶገባ ሆኖ ምርኮኛ ትካዜው
እንዲሳካ ብሎ
እውነቱን ሸጦ ነው አፍቃሪ ለጊዜው።

“እሺ” ቢል ቢዋረድ ቢናቅም ቢዘበት
"ምንም አያመጣም" ብለሽ አትሳቂበት::

ለወናፍ ዐፍ ሁሉ ቢሆን መዘበቻው
የመጣበት ቀን ግን
በፍቅሩ ልክ ነው የአፍቃሪ ጥላቻው።
16 views., 17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 09:09:10 https://vm.tiktok.com/ZMFNawTaP/
9 viewsማህሌት። , 06:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 08:40:20 ለዚህ ነው "ህይወትን" የማላምናት?

ለዚህ ነው "መኖር" "የሰው ስም ብቻ ነው" የምለው::

ለዚህ ነው "አለሁ" ማለት ነውር የሚመስለኝ::

ለዚህ ነው "ሳለን እንከባበር" እና " ሞትን እንቅደመው" የምለው::

እሳት ነው "ሞት" ያገኘውን ይበላል::

ጨለማ ነው "ሞት" ወደ-አለመተያየት ያስገባል::

"ሳይጨልምብን እንተያይ"

ኤልያስ ሽታኹን
11 viewsማህሌት። , 05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 13:48:24 https://vm.tiktok.com/ZMFNNFe6R/
14 viewsማህሌት። , 10:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 03:15:23 #እማሆይን ፍለጋ#

#ለልባም ሴት#

"...የሚነገሩ ንግርቶች፣ የሚጠቀሱ ጥቅሶች ፣የሚተረቱ ተረቶችም ልትሰሚ፣ልትዘከሪም ትችያለሽ። በመልክሽ፣በወዘናሽ ተለክቶ ስም ሊሰጥሽ ይችላል።
ቃላቶችሽን አክብሪያቸው ኑሪላቸው ለጥሩ አድማጭ አዊያቸው አልያም ዝምታን ምረጪ ለችግሮቿ መፍትሄ፣ለሀዘኗ ደስታን የምትፈጥር ከጥላቻ በላይ ፍቅርን ሰባኪ የሆነች ሴት ብልህ ነች።"
ይላሉ እማሆይ
"ወላጅ ቆንጥጦ ከሚያስተምረው
እድሜ ፈትኖ ሚያስተምረው ትምህርት እጅጉን የላቀ ነው።
የሰው ልጅ ምን ያህል ውድ እንደሆነ ዋጋውን የሚያውቀው አካባቢው ላይ እሱን አሳታፊ አሉባልታ ስለተቸረ ሳይሆን ማን እንደሆነ እራሱን ያወቀ ጊዜ ነው
አጥፍቶ እርሱ ስህተቱን እንዳልሆነ የተረዳ ወቅት ነው እራሱን ያወቀው ልጄ ከተጠበብሽ ምታውቀውን ስለሚመክሩሽ ስለምታከብሪያቸው ጆሮ ስጫቸው ጠቢብ ሴት ምክር ሳይሆን አዲስ ሀሳብን መቃረም ነው ሚበጃት።(ካላት ላይ ለመጨመር)
በስመአብ ስትዪ ማማተብን ከራስሽ እንደምትጀምሪው
መውደድን ከራስሽ ጀምሪ እራስ ወዳድ ሳይሆን እራስሽን የምትወጂ ሁኚ ያን ጊዜ ነው ሰው ሁሉ ጀርባውን ቢያዞር ቋሚ ምትሆኚው። ምታደርገውን ምታውቅ በራሷ ምትተማመን ልባም ከራሷ አልፋም ሰውን መካሪ እንደሆንሽ አውቃለው ሰዉ ጎድቶ በሸሸ ጊዜ በምድር ስብእና እና እውነት በሰማይ ፈጣሪ ብቻ መፅናኛ ሚሆነው ሁለቱን አጥብቀሽ ጨብጪ" ብለውኝ ዉሀ ተጎንጭተው ለቁርስ ለአቢ ከተሰራው የበሶ ጭብጦ ላይ ሁለቴ ቆነጠሩ
ወዲያው አቢ 'እማሆይ' እያለ ቁና ቁና ተንፍሶ ወደ ቤት ዘለቀ ለእማሆይ ተልኮ መመለሡ ነው።
አልቃሻ እማሆይ ከአምስት አመቱ ጀምሮ ያሳድጉት የነበረ የቀዬው ህዝብ 'እማሆይ አሁንም አድጎ ይሄ ልጅ መንሰቅሰቁን አልተወም እንደው ወንድ መሆኑንስ እንጃ' ሲሏት በስተርጅና ብስል የሆነችው እማሆይ "ሳሳድገው በሚያዝንበት፣በሚከፋበት ጊዜ አልቅሰው ይውጣልህ ብዬው ነው ይላሉ።"አቤት ጥበብ! አቤት መሠልጠን! ያለቀሰ ሁሉ ከማልቀሱ በፊት ላለማልቀስ እንደጠነከረ ሰው አላወቀ... አዎ ያልቅስ ሀዘኑ ከውስጡ ታምቆ ንፁህ ስብእናውን በበቀል እንዳይ ተካው እንባ አማላጅ ይሁን እንባ ሻሪ ይሁን።እንባ ድክመት አይደለም ሀዘንን መሻሪያ ዘዴ እንጂ።
በሉ እማሆይ እንዳይረፍድብኝ ልነሳ አየመጣው አዮታለሁ ብዬ እግራቸውን ስሜ አንዳች ነገር የቀረኝ ይመስል እፊታቸው ተገተርኩኝ አይኔን አይተው የገባቸው ይመስል "ደህና ሁኚ ቸር ይመልስሽ ብለው ሸኙኝ።" አሁንም ቅር እንደተሰኘ እያንገራገርኩ ከመኖሪያቸው ወጣሁ እማሆይ ጠቢብ ናቸው አንሰላስዬ ያሳነሱብኝ ምርቃት ቢበዛ ሀሴትን ፈጥሮ ያወጉኝን እንዳልዘነጋው መሆኑ ተገለፀልኝ.......

###እማሆይን እንፈልግ አልያም ልቦናችን ላይ እንገንባቸው...###

ደራሲ : ማህሌት ገድለ ሚካኤል (NiZ)
21 views00:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 22:16:43 https://vm.tiktok.com/ZMNoGbv11/
29 views19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 10:31:30 https://vm.tiktok.com/ZMNEyL6su/
33 views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ