2022-08-25 17:44:22
"ሶምሶማ ጦርነት"
ኤልያስ ሽታኹን
~ ~ ~ ~ ~
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ከነጮች ጋር እየተማረ ቁጭ ብለው እየተጨዋወቱ ሳለ "በልጅነቴ ጫማ አላውቅም ነበር" ሲላቸው ነጮቹ ደነገጡ::
"ረጅሙን የትምህርት ዘመኔን በባዶ እግር ነው ያሳለፍኩት" አለ ::
ምን ቢሉት ጥሩ ነው "ለምን አትፅፈውም? ይሄ እኮ የሚደንቅ ነው ለብዙ ሰው::"
ለነርሱ የደነቃቸው ክስተት ለጌታቸው ኃይሌ ሀገር ግን የተለመደ ህይወት ነበር::
ለብዙ የሚደንቀው ነገር ለኛ ኑሮ መሆኑ ስላቅ ነው:: በዓመት ሦስቴ የምናከብረው ብቸኛ ብዓል ነው ውጊያ::
ለምንሰማው ከደከመን እዳው ላይ ላሉት ዳፋው ዳይ ለወደቁት ምንኛ ስቃይ ይሆን?
ዛሬም ተስፋ አለን እንባባል ይሆናል:: ግን ዋሾ ነን:: እንደሀገር ሁለት ስሜት አለቀቀንም
ያልወጣልን ብሶት እና
የማንወጣው እልህ::
እንደህዝብ ቁጡ እና ሆደ ባሻ ሆነናል::
ታክሲ ውስጥ ብሶት
ኪዎስክ ውስጥ ጠርሙስ መስበር ቱግ ባይ::
ሳንነካ ሁሉም የሚያጠቃን የሚመስለን
ሁሉም የሚንቀን የሚመስለን
ሳንጠየቅ ገና የይሆናል መልስ የምናዘጋጅ ደንባሮች ሆነናል::
እንደህዝብ ተቀያይመናል::
እንደግለሰብ ተጠላልተናል::
በየሶሻል ሚዲያው ላይ ያሉት ነገሮች ድምፃቸው ቤተስኪያን ደጅ ከሚጮህ የመዝሙር ሞንታርቦ በላይ ይሰማል:: (ለሁለት ደቂቃ Tiktokህን ስክሮል አርገህ ሞክረው::) ሁሉም እየጮኸ ነው::
-ዳንሱ በጩኸት
-ስብከቱ በጩኸት
-ሞቲቬሽኑ በጩኸት
-ምክሩ በጩኸት
እልህ+ብሶት = ( )
እንደሀገር ልጅነቴ በሀገሬ ቅያሜ ካለኝ ቆየሁ:: ተኳርፍናል::
በየቦታው ሄጄ ያየሁት ህዝብ የራሱ ብሶት የራሱን እልህ ሳይ ያስፈራል እላለሁ::
"....አስርጪብኝ የምነት ቀንጃ
ለስጋቴ አጣማጅ አቻ
ለጭንቀቴ መቀንቻ ....."
እንዳለ ጸጋዬ
እኛስ
አይደክምም ወይ እያስታመሙ መግደል?
አይደክምም ወይ እየገረፉ ማባበል?
አይደክምም ወይ እየሳቁ ምስጋት?
አይደክምም ወይ እያረፉ መዋጋት?
አይደክምም ወይ?
አይደክምም?
አይደክምም?
10 views14:44