Get Mystery Box with random crypto!

ርዕስ-እንደየ ሀዘኑ... አንዳንዴ እንባ ብቻ አይበቃም ቁስለት ለማሳበቅ መጮህ ብቻ አይበቃም ምሬ | የኛ ግጥም ና ታሪክ

ርዕስ-እንደየ ሀዘኑ...
አንዳንዴ እንባ ብቻ አይበቃም
ቁስለት ለማሳበቅ
መጮህ ብቻ አይበቃም
ምሬትን ለመልቀቅ
አዎ ያስለቅሳል
ያመኑት ሲሰለብ
የያዙት ሲበተን
ያሰሉት ሲጠፋ
የልብን ማዋየት ይሆናል ጉንጭ አልፋ
አዎ ያስጮኸዋል
በስህተት ተሳስቶ
አንዴ ልቡን ከፍቶ
አለልኝ እያለ ሲጠብቅ ከጎኑ
አሉ የሚባሉት እንደ ጉም ሲበኑ
አንድ የእንባ ጠብታ መቶ ቃልን ታውጣ?
ወይስ አንድ ጩኸት ሺህ ቃላትን ይትፋ?
ይቅር እንደ ስቃይ ይቅር እንደ ህመሙ
አንድ ሁለት ሲበዛ የበሰለ ሁሉ እንዳይቀር ማረሩ
አዎ አይኖች ይሰናዱ
ጉሮሮዎች ይንቁ
ሚጠፋ ከሆነ ሚቀል እንደ ቀላል
ሁሉም አካል ይጋል
የሚመጣው የታል ??
ስማስነው ኖሬ
የዛሬን በዛሬ
ሊያስተምረኝ ኖሯል የትዕግስትን ፍሬ
እስኪ በደንብ ይብሰል ሳይጠግ ከሚመጣ
እንዲያ ሲሆን ነዋ ጉዳት ሚረታ
ስብራት ሚጠገን
የልብም አይን ያያል ሚያጓጓ ነገን
.
.
.

ገጣሚ ማህሌት ገ/ሚካኤል
@Nizan5