Get Mystery Box with random crypto!

-ልብ ልብ' ይባል!!! በፀሎት ብርከካ ልባችን ሲረካ አንድ ብቻ በፆም በሁዳዴ ይመጣ ይሆን ገ | የኛ ግጥም ና ታሪክ

-ልብ ልብ' ይባል!!!


በፀሎት ብርከካ
ልባችን ሲረካ
አንድ ብቻ
በፆም በሁዳዴ
ይመጣ ይሆን ገዴ?
አቻ ላቻ
ከጥምቀት ፀበሉ
ተመላለስ ሲሉ
እማር ብዬ እኔ አንድም ከመንፈስ
በነጠላ ስጓዝ ያለኝም እብስ
ብርከካ ስግደቴ ባዶ
ልቤ ተሰዶ
ሀሳብ ተንዶ
እስከመቼ ንቀት እስከመች ልጅነት
ሽልማት ስነጠቅ ትገባኝ ይሆን ህይወት?
እንባ ከሳቹ ትርጉመ ልል
ልብ ያላወራው ቃል ይቀላል
ከምበታተን በደመነፍሴ
ሰብስቤ ልቋጥር ሁሉን ለነፍሴ
በችርቻሮ ነገር ከሚረክስ
ልብ ተሰብስቦ ጥሞና ይዳሰስ

ማህሌት ገ/ሚካኤል
@Nizan5