Get Mystery Box with random crypto!

እወድሻለሁ ልልሽ ቀጠሮ ነበረኝ ግን ጊዜውን አላምነው አሁን በላት አለኝ አሁን ወድሻለሁ ወድሻለሁ | የኛ ግጥም ና ታሪክ

እወድሻለሁ ልልሽ ቀጠሮ ነበረኝ
ግን ጊዜውን አላምነው አሁን በላት አለኝ
አሁን ወድሻለሁ
ወድሻለሁ ብዬ ልነግርሽ ብመጣ በክንፍ በፈረስ
ለነፍስሽ ይወደኛል በይው ከጎንሽ እስክደርስ
አሁን ወድሻለሁ ቶሎ ቶሎ ስሚኝ
ህይወት ሆኗል መድሎ
ሞልቷል ያልኩት ጎድሎ
ህያው ያልኩት ሞቷል
የገነነው ወድቆ
የገዘፈው ደቆ
ሀሳብ ንፋስ ሆነ
ጊዜ ይሉት ዑደት ሰው እያተነነ
እኔ ጊዜ የለኝ
የሚሞት ስጋና ህያው ፍቅር አለኝ
ቶሎቶሎ ስሚኝ
ቶሎቶሎ ሳሚኝ
በቀጣዩ ግጥም ማፍቀሬን ልንገርሽ ያልኩትን ትቻለሁ
እሱ ጋር ሳትደርሺ ድንገት ትን ቢላት እያልኩ እፈራለሁ
ጊዜን እያሰላው
ለምን እሸሻለው
ትላንትም አይደለም
ነገንም አይደለም
ዛሬንም አይደለም
አሁን እወድዳለሁ
አሁን ናፍቀሽኛል
አሁን አሰኘሽኝ
አሁን ባገባሁሽ
አሁን አሁን አሁን
አሁን እንፋቀር
ቀጣዩን ማን ያውቃል ከወልደ እግዜር በቀር

(ገጣሚ:- ኤልያስ ሽታሁን
ተቀንጭቦ የተወሰደ ግጥም ነው )

@besye_getm