2022-12-28 17:51:07
† አንድ መልአክ በአንድ ጊዜ ሁሉም ቦታ እንዴት ይገኛል?
" እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ።"
" I am Gabriel l stand in the presence of God " ሉቃ 1፥19
★ ሼር በማድረግ ሰዎች እንዲማሩበት አድርጉ ★
አንዳንድ ሰዎች አንድ መልአክ በአንድ ጊዜ ሁሉም ቦታ መገኘት እንዴት ይችላል? ይህ የፈጣሪን ሥልጣን መጋፋት ነው ይላሉ።ተሳስተዋል።ረቂቁን የመላዕክት ተፈጥሮና ከአዕምሮ በላይ የሆነውን የረቂቁን መንፈሳዊ ዓለም አሠራር በሥጋዊ ውስን አዕምሮ መገደብና በውስን ተፈጥሯዊ የማሰብ ብቃታችን ረቂቁን የመላዕክት ባሕርይና የመንፈሳዊው ዓለም አሰራርን መርምሮ ለመድረስ መሞከር ፍጹም ሞኝነት ነው።
አንድ ነገር በጣም ልናስተውል ይገባል መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለካህኑ ዘካርያስ በተገለጠለት ጊዜ " እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ" ብሎታል ይህንን ቃል መልአኩ ለምን ተናገረው ብንል ስለ ሁለት ነገር ነው አንደኛው ሚስትህ ኤልሳቤጥ ትጸንሳለች ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ ሲለው ዘካርያስ ለመልአኩ ሚስቴ እርጅታለች እንዴት ሊሆን ይችላል ባለ ጊዜ " እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ።"አለ "መቆም" ማለት መማለድ መለመን ማለት ነው።በተለያየ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መቆም መማለድ እንደሆነ ተገልጿል።" የተመረጠ ሙሴ በመቅሰፍት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ባይቆም ኖሮ እስራኤልን ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።" ተብሎ ተጽፏል መዝ 105፥ 23 ።ስለ ቅዱስ ገብርኤል ስለ አንተና ባለቤት በእግዚአብሔር ፊት ለምኜ፣ማልጄ ነበር ማለቱ ነው።
ሁለተኛ በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ገብርኤል ነኝ ማለቱ እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ መላዕክቱም አሉ የእግዚአብሔር ፊት ወዴት ነው ? ብንል እግዚአብሔር ረቂቅ ስለሆነ በሁሉም ቦታ ሁሉ አለ ስለዚህ እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ ቅዱሳን መላዕክቱ አሉ።ይህም እንደ እርሱ አምላክ የሚያሰኛቸው ሳይሆን በመለኮት ሥልጣን፣ከእግዚአብሔር በተሰጣቸው መንፈሳዊ ረቂቅ ጸጋ እርሱ ባለበት ቦታ ሁሉ እነርሱም አሉ።
‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙርያ ይሠፍራል፤ ያድናቸውማል›› (መዝ. 33፥7)
የሚገርመው ግን እግዚአብሔርን ለማይፈሩ፣በኃጢአትና በበደል ለሚመላለሱ ሰዎች ግን እንኳን በአንድ ጊዜ ለሁሉም ባሉበት ቦታ ሊደርስ ሁሉም ሰዎች ተሰብስበው መልአኩ ወዳለበት ቢመጡ እንኳ አይረዳቸውም።
የእንግሊዘኛውን ቨርዥን ብንመለከተው በደንብ ግልጽ ያደርገዋል "l am Gabriel l stand in the presence of God" ይህም ማለት እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ መልአኩም አለ።እግዚአብሔር ረቂቅ አምላክ ነው እነርሱም ረቂቃን ናቸውና እርሱ ባለበት ሁሉ እነርሱም አሉ።
ስለዚህ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሥርዓቷ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስለሆነ አልተሳሳተችም።በአንድ ቀን በተለያየ ሃገርና ቦታ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ስናከብር የእግዚአብሔርን ክብር እያወጅን ስለሆነ በሁሉም ቦታ እግዚአብሔርም መልአኩም በክብር ነበሩ።
አንድ ቅዱስ መልአክ ክብሩ ከፀሐይ ክብር ይበልጣል እንጂ አያንስም አንዲቷ ፀሐይ በአንድ ጊዜ የተለያየ ቦታና የተለያየ ሀገር የመድረስ ተፈጥሯዊ ፀጋ አላት የእግዚአብሔር መልአክ ደግሞ ከፀሐይ በላይ ሥልጣን ስላለው በአንድ ጊዜ ሁሉም ጋር መገኘት ይችላል።ይህ ማለት የእግዚአብሔርን ሥልጣን መጋፋት ሳይሆን እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ መልአኩም እንደሚገኝ ማስረገጥ ነው። "በእግዚአብሔር ፊት የምቆም ነኝ" ያለውም እግዚአብሔር ባለበት ቦታ ሁሉ መልአኩም እንደሚኖር ማረጋገጫ ነው።እግዚአብሔር ደግሞ የሌለበት ቦታ የለም።
" ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።"
(የዮሐንስ ራእይ 18:1)
ከነፋስ ይልቅ ነፍስ ትረቃለች፤ ከነፍስ ይልቅ ደግሞ መላእክት ይረቃሉ፤ ከመላእክት ደግሞ ሥላሴ ይረቃል ።በውስን አዕምሯችን ረቂቃኑን ለመገደብ አንሞክር።ከአዕምሮ በላይ የሆነብንን ነገር ዕፁብ ድንቅ ብለን ማለፍ ክርስቲያናዊ ጠባይ ነው።
በምድራዊ ቴክኖሎጂ እንኳ ብንመለከት አንድ የኮምፒውተር ሰርቨር በተለያዩ ሀገር ያሉ በሚሊየን የሚቆጠሩ ኮሚፒውተሮችን በተመሳሳይ ሰዓትና ደቂቃ የሰከንድ ልዩነት ሳይኖር መረጃ ይሰጣል መረጃም ይቀበላል።ሰው የፈጠረው ሰርቨር በአንድ ጊዜ ሁሉም ጋር መሥራት ከቻለ እግዚአብሔር የፈጠረው አንድ ቅዱስ መልአክማ ከሰዎች የእጅ ሥራ ውጤት በሰባት እጥፍ እንደሚበልጥና አንዱ ለሁሉ መድረስ እንደሚችል በእምነት ልንረዳ ይገባል።አሁን የምንጠቀምበትን የፌስቡክ አፕልኬሽን የሚቆጣጠረው አንድ ሰርቨር ነው።በዓለም ዙሪያ ያሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎችን በሙሉ የሚቆጣጠራቸው አንድ ሰርቨር ነው።የሰው ልጅ የእጁ ሥራ ዓለምን እንዲ መቆጣጠርና በአንድ ጊዜ ለሚሊየኖች ተደራሽ መሆን ከቻለ አንድ ቅዱስ መልአክ ከዚህ በላይ ሊሰራ እንደሚችል መንፈሳዊ አዕምሮ ያለው ሰው በቀላሉ የሚረዳው ሐቅ ነው።
ቅዱስ ገብርኤል አንድ ሲሆን ከእግዚአብሔር በተሰጠው ፀጋና ሥልጣን በዓለም ዙሪያ ላሉ ሰዎች ሁሉ ከዓይን ጥቅሻ ባነሰ ፍጥነት ደርሶ ይራዳል።
የመልአኩ ፈጣን ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን።
መ/ር ታሪኩ አበራ
እባካችሁ ለሌሎችም ሼር አድርጉት
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
2.3K views✞£iŧsûm✞, 14:51