'የክርስቶስ በዓላት 9 ናቸው (አበይት በዓላቱን ማለቱ ነው)፤ የማርያም ግን 33 ናቸው። በምን ያ | ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ
"የክርስቶስ በዓላት 9 ናቸው (አበይት በዓላቱን ማለቱ ነው)፤ የማርያም ግን 33 ናቸው። በምን ያህል እንደሚበልጡ እዩ ወገኖቼ . . ." ይላል አንዱ ፓስተር ዩቲዩብ ላይ። አቤት! ሕዝቡን እንዴት ነው የሚዋሹት?
ሰንበተ ክርስቲያን (የክርስቶስ ትንሣኤ መታሰቢያ በዓል) የማን በዓል ናት? በዓመት ስንት የሰንበት እሁዶች ይከበራሉ? (55) ንዑሳን የጌታ በዓላትስ? በዓመት ስንት በዓለ ወልድ ይከበራል? (12) አማኑኤል? ኢየሱስ?
ውይ! የጌታን በዓላት መቁጠር ጀመርን እንዴ? ወደ እነርሱ ስንፍና አስገቡን! የእመቤታችንን ጨምሮ የቅዱሳን በዓላት ያለ ቅዱስ ቁርባን ይከበራሉ? በፍጹም! ቅዱሳን ሁሉ በራሳቸው በዓላት እንኳ ክብራቸው በመሠዊያው ላይ የሚገለጠው ክርስቶስ መሆኑ ይታወቅ! ክርስቶስ የማይከብርበት የቅዱሳን በዓል የለም! አትዋሹ! ሕዝቡን በድንቁርና እና በውሸት ይዛችሁ መቀጠል የማትችሉበት ጊዜ መጥቷል። የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋ እና ክቡር ደም ወደሚቀበልባት፣ ከቅዱሳን ጋር ኅብረት ወደሚፈጥርባት ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚመለስበትን ጊዜ ብታስረዝሙት እንጂ አታስቀሩትም!
***
"የመንጋዬም ቅሬታ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ ወደ በረታቸው ሰብሰቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ያፈራሉ ይበዙማል። የሚጠብቋቸውን እረኞች አስነሣላቸዋለሁ፥ ዳግመኛም አይፈሩምና አይደነግጡም፥ ከእነሱም አንድ አይጐድልም፥ ይላል እግዚአብሔር።" (ኤር. 23÷3-4)
~በረከት አዝመራው~
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero