Get Mystery Box with random crypto!

Nolawi ኖላዊ ኄር

የቴሌግራም ቻናል አርማ nolawiiher — Nolawi ኖላዊ ኄር N
የቴሌግራም ቻናል አርማ nolawiiher — Nolawi ኖላዊ ኄር
የሰርጥ አድራሻ: @nolawiiher
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.01K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ቻናል የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነወ።
#ለሃሳብ ለአስተያየት 👉 @Nolawiher1
Facebook :- https://www.facebook.com/estifanos.dejene.94
✟ወአንሰ በምሕረትከ ተወከልኩ ✞
✟ይትፌሥሐኒ ልብየ በአድኅኖትከ ✞

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 17:27:15 የሰርክ ማዕድ ነው ። በማስተዋል እንድታነቡ እመክራለሁ ። አእምሮአችሁ ብሩክ ይሁን !
419 views Estifanos, 14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:25:43 አልተጠገነም አለ ነቢዩ ።፦ አዎ ወገኖቼ ሽማግሌ አላስታረቀም ፤ ካህን ለንስሐ አልጋበዘም ። በርግጥም ሽማግሌ የለም ። ለካ ሽበትም ማየት ይናፍቃል ! ። ለዛሬው ውደቀታችን ትንሳኤውን ናፍቆ እርቅን የሚያወርድ ሽማግሌ ያስፈልጋል ። ''ሸምግሎ አስታራቂ ተጣልቶ ወዳቂ'' እንዲሉ ሸምግሎ አለማስታረቅ የሽምግልናን ፀጋ ለምኔ ማለት ነውና ሀገሬ ኢትዮጵያ እርጥብ ሣር ይዞ ይብቃ የሚል ሽማግሌ ያስፈልጋታል ። በርግጥ እንኳን ሽማግሌ ጳጳሳት አባቶችን ለመሳደብ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያላት ሀገር ይህን እንዳናስብ ሊያደርግን ይችላል ። ነገር ግን እግዚአብሔር ሽምግልናን የሚሰጥበት ምክንያት በትላንት ታሪክ የዛሬን ትውልድ እንዲታደግ በነጌ ብርሃን ዘመንን እንዲመርቅ ነውና ሽማግሌ ሊከበር ይገባል ። ሽማግሌ ብቻ አይደለም ካህን ለንስሐ ትውልድን አልጋበዘም ። እኛ ከእግዚአብሔር ጋር ተጣልተን እንኳን ወገናችንን እራሳችንን እንኳ መቀበል አንችልም ። ያለ እግዚአብሔር ምሕረት አንዲት ደቂቃ እንኳ ራሳችንን መቀበል አንችልም ። ከእግዚአብሔር ጋር የተጣላ ደግሞ ወንድሙን ለመጥላት ቅርብ ነው ። ወንድሙን የጠላ በሞት ውስጥ ይኖራል እግዚአብሔርን ሊያመልክ እንዴትስ ይችላል ? ከእግዚአብሔር ጋር ኑሮ የሚል ስብከት ቀዝቅዟል ። ካህን ዝም ካለ ምእመን ስሜቱን ያዳምጣል ። ካህን የእግዚአብሔር ድምፁ ነውና የእግዚአብሔርን የምሕረት ጥሪ /የንስሐ አዋጅ/ ካላሰማ ምእመን ለመረጃ ድምፅ ተላልፎ ይሰጣል ። መስቀል የያዘ ካህን የሰላም ደብዳቤ ነውና ባለበት አከባቢ ዘሬ ብሎ የሚያልቀውን ህዝብ ስለ እግዚአብሔር ብሎ ወደ ንስሐ መምራት አለበት ። ሰው ከንስሐ ከራቀ የሚደሰተው በኃጢአት ነው ። ነገር ግን ደስታ ያልሆነ ግን ደስታ የሚመስል ደስታ ነው ። አልተጠገነም ለክፋታችን ድንበር እናብጅለት ፣ ትላንት ትናንት ላይ ይቅር ዛሬን ኖረን እንሙት ፣ የኃጢአት ደስታ ግቡ ሀዘን ነውና ተመለሱና በሕይወት ኑሩ ብሎ እንደ ነቢዩ ሕዝቅኤል የሚጮህ ካህን ዛሬም ሀገሬ ኢትዮጵያ ያስፈልጋታል ። እግዚአብሔር ሳይጠገን ደርቆ ያዛለንን ሕመም በፍቅሩ ዘይት ወደ ሥፍራው ይመልስልን ።

በዘይትም አልለዘበም አለ ነቢዩ ፦ ለፍቅርና ለይቅርታ ጊዜ የለንም  ። ፍቅር የዘረኝነትን ሸካረ ያለሰልሳል ። ይቅርታ የጎሰኝነትን ኮረብታ ይደለድላል ። ከፍቅር በራቅንበት መጠን ለጥል እየቀረብን ነው ። ከይቅርታ በራቅን ቁጥር ለቂም በቀል እጥፍ ድርብ እየቀረብን ነው ። ሀገራችን በመንፈስ ቅዱስ ሰላም የምትመላው አንድነታችን ማዕከሉ ፍቅር እርምጃችን ለይቅርታ ሲሆን ነው ። መንፈስ ቅዱስ በቤተክርስቲያን አልፎም በሀገራችን እያዘነ ነውና ወዮውልን ። አዎ ወገኖቼ ከህዝብ እስከ መንግስት ፤ ከሊቅ እስከ ደቂቅ ጤና የለንም ። ሁሉ ጤና አጥቶ ሀኪሙ ጠፍቷልና ልባችን ወደ እግዚአብሔር ፣ ኑሮአችን ወደ ቃሉ ፣ ውሏአችን በቤቱ ካልሆነ አቋማችን ይረገርጋል ፣ ውበታችን ይደበዝዛል ። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ያስባት !

ጸሎት

ሁሉን የምትይዝ ሁሉን የምትገዛ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሃለሁ ። ብኖር የማልጠቅመውን ፣ በቆም የማልጸናውን ፣ ብቀመጣ ያማላርፈውን ፣ ብራመድ የማልደርሰውን በቸርነትህ ስላኖርከኝ አቤቱ ተመስገን ። ሰው ሁሉ በደለኛ ነው ። እንደ እኔ ግን የበደለህ የለም ። ሰው ሁሉ ኃጢአተኛ ነው እንደኔ ግን ነውረኛ የለም ። የዓመታት ዕዳህ የሆንኹ እኔን ስታገስከኝ ተመስገን ። ጌታ ሆይ ከአንተ ተለይቼ ለቤተሰቤ ሁከት ፣ ለሀገሬ ሸክም ሆኛለሁ እባክህ በምክርህ መልሰኝ ። በምንም መስክ ላይ ምንም ኖሪያለሁ እባክህ የሰላም ሰው አድርገኝ ። የዘርኝነት ጨለማ የከበባትን ፣ የግድያ ዜና ያብረከረካትን ሀገሬን ኢትዮጵያን በጽኑዕ ምንግሥትህ አስባት ። በማላፍርበት ደግነትህ ለዘለዓለሙ አሜን ።

    ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ
    ነሐሴ 26 ቀን 2014 ዓ.ም.
╰───────────
429 views Estifanos, 14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:25:43 ቍስልና እበጥ የሚመግልም ነው አለ ነቢዩ ።፦ የዕለት ጥዝጣዜ አልብን ፦ እርሱም ቁስል ይባላል ። በዕለቱ የሚሰማን ችግር አለ ። የሰላም ባጀት በመንግሥታት አቋም ዕቅድ ተለቆ አያውቅም አይለቀቅምም ። የሰላምን ባጀት ያለ ገደብ የሚለቅ የሰላም አለቃ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። ከዕለቱ ጋር የሚለቀቅልን የሰላም ባጀት ከጸባዖቶ ተቋርጦ አያውቅም ። ውኃ ልማት እሰከ ቤታችን ውኃ ይለቃል ። ቦኖውን ከፍቶት መጠቀም ግን የባለቤቱ ድርሻ ነው ። ክርስቶስ ወደ ልባችን ፣ ወደ ቤታችን ፣ ወደ መንደራችን ፣ ወደ ከተማችን ፣ ወደ  ሀገራችን የሚለቀውን የሰላም በረከት ልብን ለንስሐ ከፍቶ  ፣ ኑሮን ለቃሉ አዘጋጀቶ ፣ ውሎን ለምክሩ ለቅቆ መገኘት ያስፈልጋል ። ያለዚያ የዕለት ችግሮቻችንን እንኳን እንደ ሀገር እንደ መንደርም መቅዘፍ ይከብደናል ። ለዚህ ነው ነብዩ የዕለት ችግሮቻችንን በቁስል የመሰለው ። ቁስል ይጠዘጥዛል ። አትንኩኝ ባይነትን ያለማምዳል ። ዛሬ የእኛ ቁስል ዘር ነው ። መርጠን ባልተወለድንበት ዘር መርጠን መታመማችን የሚያሳዝን ነው ። አማራ ተንክቶ ሀድያ ካልደማ ፥ ሀድያ ደምቶ ኦሮሞ ከላከመ ፥ ትግሬ ተርቦ ጉራጌ ካልመገበ እያልን ጨፍረን ሰው ግን ሰው መሆኑ ገና አልገባንም ። በተወለደበት አከባቢ  በወጣለት የብሔር ስም ሰው አይመዘንም ሰው ሰው ነው የሚል ትምክህት ያስፈልጋል ። ዛሬ የእኛ ትምክህት አማረነቴ ኩራቴ ፣ ኦሮሞነቴ ብርታቴ ትግሬነቴ ክብሬ የሚል ነው ። የጋራ አንድነት እንጂ የጋራ ዘር ሀገርን አያሻግርም ። ቢመኩበት የማይጥም ትምክህት ይዘን ለጨነገፍ ፅንስ ልደት አክብረናል እግዚአብሔር በንጹሕ መዳፉ የኢትዮጵያን ቁስል ይዳባስ !

ለዘመናት የተጠራቀመ ችግር አለብን ። ነብዩ ይህን በእበጥ መስሎታል ። በመቶ ዓመት ታሩክ ዛሬ ከሚጣላ ሕዝብ በላይ ምን የሚያሳፍር ሕዝብ አለ ?! ይህን ትምህርት ቤት እገሌ የሚበል መንግሥት ነው ያሰራው ተብሎ ከድንጋይ ጋር ከሚጣላ ሕዝብ በላይ ምን የሚያሳፍር ሕዝብ አለ ?! ሰው ከድንጋይ ጋር ይጣላል ?! እገሌ የሚባል ዘማሪ ከቤተክርስቲያን ተውግዟል ሲባል መዝሙሩን ተጸይፎ ሲዲውን ከሚያቃጥል ሕዝብ በላይ ምን የሚያሳፍር ሕዝብ አለ ? ሰው ከመዝሙር ጋር ይጣላል ?!  ወገኖቼ ቂመኛ ሕዝብ አይድንም ። ክርስቶስ በማዋል ሥጋዌው ያስተማረን ብዙ ትእዛዛት ቢኖሩ እንኳ ከትእዛዛት የሚበልጠው ትእዛዝ ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚል ነው ። ሰው እግዚአብሔርን እቢ ካለ የማይሆነው የለምና የእኛ ጉድ ገደብ የለውም ። እንኳን የዛሬ ጠላታችንን መውደድ አይደለም የመቶ ዓመት አፅም ጋር ቂም ያለን ሰዎች ነን ። እረ እግዚአብሔር ያስበን ! የሕይወት መጽሐፍ እንዲህ ይላል ፦ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል።እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና። የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። (ማቴ 5:43-48 ) ። ቃሉን ስትመረምሩ ጌታ እየተናገረ ያለው አንድ ነገር ነው ። ጠላቶቻችሁን ለመውደድ ወዳጆቻችሁን በመውደድ ጀምሩ የሚል ነው ። እኛ በሚያሳዝን መልኩ የዛሬውን ጠላት አይደለም ለመውደድ ለማወቅም ዝግጁ አይደለንም ። ምክንያቱም እኛ በመቶ ዓመት የጠላት ተሪክ ላይ ነው ያለነው ። ፈትሉ የረዘመ የቂም ትብታብ ውስጥ ነን ወገኖቼ አረ እኛንስ እግዚአብሔር ያስበን ! ። አንደ ሰውነት ሰለ ሀገሬ ኢትዮጵያ አዝናለሁ ። እንደ መንፈሳዊነት ግን ተስፋ አደርጋለሁ ። እግዚአብሔር ይህችን የዘመን ቂም ያጨለማት ሀገር በብርሃን ዓምዱ ከውድቀት ይመልሳት !


የሚመግልም ነው አለ ነቢዩ፦ ሽታው የሚያውክ መግል አለብን ። ለዓለም ዜና ርዕስ የሚሆን የግድያ ፣ የግፍ ግፍ ፣ የጥላቻ ልክ ፣ የነውር ካባ ፣ የውርደት ልክ አለብን ። ብክብራችን በምንታወቅበት ዓለም በነውራችን ፣ በፍቅር በምንታወቅበት ዓለም በጥላቻ ፣ በመረዳዳት በምንታወቅበት ዓለም በገዳደል እየታወቅን ነውና ወዮውልን ። ዓለምስ ቢያውቅ ለማለት ነው እግዚአብሔር እያወቀ ዝም ካለን ግን ጉዳዩ አስጊ ነው ። ''አንዲት ሴት ያሉት ነገር ሁሌ ያስደንግጠኛል ። እንዲህ አሉ እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ካልቀጣን ሰዶምና ጎመራን ይቅርታ መጠየቅ አለበት" አዎ ቅጣት ያንስብናል ። ግን እግዚአብሔር ተመግሶናል ። እግዚአብሔር የሚናገርበት ዘመን  የምሕረት ዘመን ነው ። እግዚአብሔር ዝም የሚልበት ዘመን አስፈሪ ዘመን ነው ። በማን ላይ ቆመሽ ማንን ታሚያለሽ ነው ነገሩ ። በእግዚአብሔር ምሕረት ቆመን ማቄም ፣ በእግዚአብሔር ይቅርታ ኖረን መግደል ፣ በእግዚአብሔር ቸርነት ቆመን መበቃቀል የሚያሳዝን ነው ። ችግሩ ገድሎ የሙት ልጅ አይኮንምና መግሉ ለሚሸት ለዚህ ውድቀት ዋና ተባባሪ ነን ። ወገኖቼ ስትሆኑም አለመሆንን ተቀበሉ እንጂ ! ። እንዴ የሆነ መንደር ውስጥ 20 ዓመት ተኑሮወ ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለት ነውር ነው ። እርሱ ለመታወቂያ በቂ ነው ። አረ ኢትዮጵያን ኑሩላትና ፣ ውደዷትና ፣ ስሩላትና ፣ ጥቅሟትና ኢትዮጵያዊ ነኝ በሉ ። እስከመቼ በመታወቂያ ወረቀት ይፎከራል ? አረ ተዉ ይህ አያሻግረንም ። እኛ የተውናትን ሀገር ሌለኛው ወገን አይደለም እግዚአብሔር እንኳ አይደግፋትም ። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ጥሎ አይጥልም የሚሉ አዝማሪዎች አሉን ። አረ ተዉ እግዚአብሔር እስራኤልንም ጥሏል ። እንደ እስራኤል የተመረጠ እንደ እስራኤል የወደቀ የለም ። ከድንጋይ እና ከመዝሙር ጋር የሚጣላ ሕዝብ አይወድቅም ማለት ዘበት ነው ። ውድቀት ስብራት ቢኖረውም እንዲጠገን አድርጎ መሰበርም ግን ያስፈልጋል ። ከመቶ ዓመት ታሪክ ላይ ዛሬ የሚያቄም ትውልድ ነጌን መድረሱ ያሰጋል ። በማንማርበት ትናንት ውስጥ ዛሬን መቆም ፣ በማንመለስበት ዛሬ ውስጥ ነጌን መድረስ አንችልም ። ትናንት ስህተት ቢኖረው ለዛሬ እንዲታረም ነው ። ዛሬ ውድቀት ቢኖረው ነጌ እንዲነሳ ነው ። አረ መግላችን ያጸይፋል ሽተው ምድር አውኳል እናስተውል ! እግዚአብሔር በፍቅሩ መዓዛ የነውር መግል ያሸተታትን ኢትዮጵያ ይመልሳት ።

አልፈረጠም አለ ነቢዩ ፦ ማለትም አልተወያየንም ። ችግሩ ምንድነው ብሎ የሚጠይቅ የለም ። በፈጠራ ታሪክ ነው የምንጣላው ። ያሰብነው እንደሆነ አድርገን ነው የምንባለው እያለ ነው ነቢዩ ። ችግር ከወራጁ አይገደብም ። ቢገደብም የሚዘልቅ ሳይሆን የሚደጋገም ይሆናል ። ችግርን ከምንጩ ለመገደብ መወያየት ፣ መግባባት ፣ ሀሳብን  ማክበር  ያስፈልገናል ። አልያ አንድነቱ እስከ ወራጁ ይሆንና ችግሩ ይደጋገማል ። አንድነታችን እስከ ችግሩ ምንጭ ካልሆነ ችግርን መገላገልም ሆነ ማቆም አይቻልም ።
288 views Estifanos, 14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 17:25:43 ጤና የለንም

“ሁሉ በሽተኛ ሁሉ ራሴን ባይ
ከቤታችን ደህና መጥፋቱ ነው ወይ”

የትልቅ ነገር ክብረት የትንንሽ ነገር ቅለት ነው ። ጤና እስካለ የከበዱ ጤና ሲጎድል የረከሱ ነገሮች ለመኖራቸው ትናንታችን ምስክር ዛሬያችን ዋስትና ነው ። የመውጣትን ያህል መግባትን ስናስብ የመድረስን ያህል መጀመርን አንወድም ። የትናንቱ የሀገራችን መልካምና ክፉ ታሪክ ውስጥ ጠልቀን ስንገባ በክፉ ታሪክ ላይ መልካም ታሪክን ያጎሉ በመልካም ታሪክ ክፉ ታሪክን የሻሩ አባቶቾ እንዳሉ እንገነዘባለን ። በዚህ ውስጥ የምንረዳው ነገር ክፉ በክፋቱ ሲበረታ ከሚከተለው ባላይ የሚተቸው እንደነበረ ፤ መልካሙ ለትውልድ ሲጥር ተተኪነትን የሚወድ ሕዝብ እንደነበረን ለመረዳት በልብ ሀገር ሀገሬ ኢትዮጵያን መጎበኝት በቂ ነው ። ክፉ ነገር ዜና የሆነበት ዘመን ይህ  የእኛ ዘመን ነው ። ለክፉ ዜና ጆሮ ከመስጠት መልካሙን ለመሥራትና ለማድመጥ ጥረት ማድረግ የክፋቱን ምንጭ መድፈን ባይቻል እንኳ ከርዕሰ አደባባይ መሻር ይቻላል ።   በርግጥ ዘመን እኛ የሆነውን ነው የሚሆነው ። ይህ ''ክፉ" ዘመን የሚሉ ብዙ ሰዎች አሉ ። ክፉ ግን ሕዝቡ እንጂ ዘመን አይደለም ። ዘመን እንደኛ ነው የሆነውን ይሆናል ። አህያ ሰርዶ አብቅላ ብትመገብ ለማለቁ አትሰስትም ። የምትሳሳው ከመብላቷ በላይ ለማብቀል ነው ። የማዕዷ ፍቃድ ከአምላክ ዘንድ ነውና ይህን አቋም ግን የላትም ። ልክ እንዲሁ ሕዝባችን የመረጃ ሆኖ የሚታረድ በዛ ።  ሕዝቡ ከምሕረት አደባባይ ወርዶ ለቂም በቀል ንቁ ሆነ ። መረጃ መታረጃ ሆኖልንም ልንሰማው ያልወደድነው አንድ ድምፅ አለ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው ። ከእግዚአብሔር ቃል ይልቅ የ activists መረጃ ልባችንን ገዝቶታል ፣ ከቤተክርስቲያን ዓውደምሕረት   ይልቅ የፖለቲከኞች የጹሑፍ  መድረክ ዓይናችንን ማርኮታል ። ከመምሕረነ ወንጌል ትምህርት ይልቅ የጎሰኞች መንደር እግራችንን መርቶታል ። ከመንፈሳዊያን  አባቶች ምክር ይልቅ የአዝማሪዎች ውሸት ልባችንን ደልሎታል ። ከሀገር ሽማግሌዎች መሪነት ይልቅ ለዘረኞች ጄኔራል ተግዘተናል ። ወገኖቼ  በዘመኑ ውስጥ እኔ አንድ ዘመን ነኝ ማለት አለብን ። ዘመን ትርጉሙ ፦ የታደሰ ፣ ልቆ ያለ ፣ የተሻለ ፣ የሚበልጥ ፣ ከሆነ በላይ የሆነ ፣ ከመሰለው ባለይ የመሰለ ፣ ከሚሰራው በላይ የሚሠራ ማልት ነው ። ዘመን የታደሰ ሆኖ በእኛ አርጅቷል ፣ ዘመን የሚልቅ ሆኖ በእኛ ተዋርዷል ፣ ዘመን የተሻለ ሆኖ በእኛ መክኗል ፣ ዘመን የሚበልጥ ሆኖ በእኛ አንሷል ። በተሻለው ዘመን ተሽሎ መገኘት በሚበልጠው ዛሬ ልቆ ከፍ ማልት ያስፈልገናል ። የዘመን ሰጪው ግን ጌታ ነውና ካላከበሩት ያዋርዳል ። ከትልቁ እግዚአብሔር የተቀበልነው ትንሽ ነገር የለም ። ዘመንም የመድኃፉ ብርሃን ነውና ዘመኑን እንደሆነው ከምናደርገው ሊያረገን የወደደውን ብንሆን እግዚአብሔር ይደሰታል ። ዘመንን እንደ ዘፈኑ ፣ ዘመንን እንደ ዜናው ፣ ዘመንን እንደ ስሜታችን ፣ ዘመንን በአሉ ፣ ዘመንን በግዴለሽነት መቀበል የዕለት ተግባራችን ሆኗል ። በዚህ ምክነያት ከእግር እስከ ራስ ታመናል ። አባት በብልጫው ፣ ሽማግሌ በክብሩ የማይከበሩባት ሀገር ሀገሬ  ኢትዮጵያ ናት ። መምህራን በእውቀታቸው ፣ ጠቢባን በጥበባቸው ፣ ድሆች በጉልበታቸው ማዋያ ያጡጧባት ሀገር ሀገሬ ኢትዮጵያ ናት ። ጳጳሳት በመሪነታቸው ፣ ቀሳውስት በመስቀላቸው ፣ ዲያቆናት በትሕትናቸው ሥፍራ ያጡባት ሀገር ሀገሬ ኢትዮጵያ ናት ። ለእውነት ያደሩ የሚገፉባት የውሻት ባለሟሎች የሚሾባት ሀገር ሀገሬ ኢትዮጵያ  ናት ። አስታራቂን የሚተች ገዳይን የሚያሞግስ ወገኔ ታሟል ።  ይቅርታን የራቀ ሰይፍን የመዘዘ ወገኔ ጤና አጥቷሎ ።


የሀገራችን ኢትዮጵያ ጉዳይ ሲያስለቅሰን እንደ መንፈሳዊ ግን ተስፋ እናደርጋለን ። አዎ ወገኖቼ የሀገራችን ጉዳይ አስለቃሽ እና ልብን የሚሰብር ነው ። ሀገር ማለት ሰው ስው ማለት ሀገር ነው ። ሰው ይታመማል ሀገርም ይታመማል ። ሰው ይወድቃል ሀገርም ይወድቃል ። ሰው ይሞታል ሀገርም አንድአንድ ጊዜ ይሞታል ። በማይደፈር ቅጥራቸው እና በሕንፃ ጥበባቸው የከበሩ ዛሬ ግን ደብዛቸው ጠፍቶ በበረሃ አሸዋ የተዋጡ ብዙ ሀገራትን እናውቃለን ።  የነቢዩ የኢሳይያስ ትንቢት የዛሬዋን ኢትዮጵያ አቋም ቁልጭ አድርጎ ያሳያል ። ቃሉን ልብ እንበል “ከእግር ጫማ አንስቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም፤ ቍስልና እበጥ የሚመግልም ነው፤ አልፈረጠም፥ አልተጠገነም፥ በዘይትም አልለዘበም።” ( ኢሳይያስ 1፥6 ) ። በዚህ ቃል ውስጥ የዛራዋን ኢትዮጵያ ብንፈልጋት የምናገኛት በምን ሥፍራ ነው ቢሉ ፦

“ከእግር ጫማ አንስቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም አለ ነብዩ ፦ ማለትም ከሕዝብ እስከ መንግሥት ታመናል እንደ ማለት  ነው ። አዎ ወገኖቼ ሕዝብ እንደ ዜጋ አይኖርም ፤ መንግሥትም እንደ መሪነቱ አይከበርም ። ለሚመራው ሕዝብ የማይራራ ለመረጠው መንግሥት የማይገዛ ሕዝብ መቼም ሰላም የለውም  ። ባሳለፍነው ዘመን ውስጥ መሪዎች ክብራቸው በጣሞ የላቀ ነው ። እንደውም ጃንሆይ ወደ ደበረዘይት አከባቢ ሔደው አንዲት እናትን ሰላም ብለው ጨበጡ እነዛ እናት ታዲያ ቀኝ እጃቸውን በነጭ ሻሽ ጠምጥመው ንጉሦ በጨበጠ እጄ ሰው አሰጨብጥም እያሉ እንደ ነበሩ ታሪክ ያወጋናል  ። መሪ ይህን ያህል የሚከበርባት ሀገር ነበረችን ። ዛሬ ከደቂቅ እስከ ሊቅ መንግሥትን የሚሳደብ ነው ። ወገኖቼ መሪ ማለት አቅጣጫ ጠቋሚ ብቻ አይደለም ራሱ ግን አቅጣጫም ነው እንጂ ። መንግሥትን የማያከብር ህዝብ ሕዝቡን የማያከበር መንግሥት ዙፋኑ የረገረገ ነው ። አዎ ወገኖቼ በዛሬዋ ኢትዮጵያ ላይ የምናየው ውርደት ይህ ነው ። ከሕፃን እስከ ትልቅ መንግሥትን የሚሳደብ ሕዝብ ነው ። ለመከፋፈል የጨከነ ነጌን የማያስብ ሕዝብ ሆነናል ። ወገኖቼ በልኩ መንገድ ስንሄድ የሚገባን ነገር ተስፋችን መሪዎቻችን እንዳልሆኑ ነው ። ተስፈኛ ተስፋ አይሆንም ። በዚህ መክንያት መንግስትን ከመስደብ እና ቀሎ ከመገኘት መጸለይ መልካም ነው ። እኛ መንግሥትን ከመናገር ይልቅ  ለመተቸት ቅርብ ነን ። በዚህ ምክንያት ነው ከልጅ እስከ አዋቂ ጤና ያጣነው ። ለመንግሥታት ከመጸለይ ይልቅ ብንሰድባቸው ይቀናናል ። ከዚህ በላይ በሽታ አለ ? ከዚህ ባላይ መታመም አለ ? እግዚአብሔር ያስበን ! ። ወገኖቼ ዝም ብላችሁ ጤና አትጡ መንግሥትን በዙፋኑ ያስቀመጠ የእናንተ የመርጫ ወረቀት አይደለም ። መንግሥትን መንግሥት ያረገው እግዚአብሔር ነው ። ስለዚህ የእኛ ድርሻ መጸለይ ነው ። የሚጸልይ ሕዝብ ይባረካል  ። ከሊቅ እስከ ደቂቅ የታመምን ሕዝቦች ነን ። እንኳን ለእግዚአብሔር ለሰለጠኑ ሀገራት የማይመጥን ማንነት እያካበትን ነው ። አዎ ኢትዮጵያን በዘፈን የሚወዳት እንጂ በተግባር የሚወዳት ወገን አጥተናል ።

“ሁሉ በሽተኛ ሁሉ ራሴን ባይ
ከቤታችን ደህና መጥፋቱ ነው ወይ”

የተባለው ለዚህ ነው ። ሁሉ በሽተኛ ከሆነ ማን ሊያክም ነው ? ሁሉ እኔን ባይ ከሆነ ድሆችን የሚያስብ ማነው ? አረ አስተውሉ ይህ ጉዞ ጨለማ ነው ። አረ ተመለሱ ወንድም ወንድሙን አሸንፎ አያውቅም !? አረ መንገድ ተስቷል ወንድምን ገድሎ ሹመት የለም !? ። ለኢትዮጵያ ወይ ሸክም አቅልሉላት ወይ ሸክም አትሁኑባት ። ይህን የጤና ጠንቅ መገደብ የሚቻለው ቢያንስ አንድ ሰው ከእኔነት ሲድን ነው ። ኢትዮጵያን ማዳን ባትችሉ እንኳ ሕመሟ አትሁኑ ።
410 views Estifanos, 14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 09:22:51
627 views Estifanos, 06:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 07:56:29 #"ለሌሎች የሚኖር ሰው ማነው?"

ምሁሩ ንጉሡን ወደ አንድ መንደር ወሰዳቸው። ትንሽ ርቀው ሲሄዱ አንድ አዛውንት ከዛፍ ስር ተቀምጠው አገኙ። ሽማግሌው ውሃ እና ጥቂት ዳቦ ይዘው ነበር። ምሁሩ አዛውንቱን ውሃ እና ዳቦ፤ ለራሱ እና ለንጉሡ ጠየቃቸው። ንጉሡም ምሁሩም ተመገቡ።

ከዚያ በኋላ ንጉሡ ለአረጋዊው ሰው ሊከፍሉ ገንዘብ አወጡ። ነገር ግን አዛውንቱ አስቆሟቸው፤ "እኔ ሻጭ አይደለሁም፤ በዚህ እድሜዬ መሥራት የምችለውን እየሠራሁ ነው። ልጄ ዳቦ በመጋገር ሥራ ይሠራል። እኔ ደግሞ ብቻዬን ቤት መቆየት ነበረብኝ።

ስለዚህ በዚህ ለሚያልፉ መንገደኞች ነፃ ውሃ እና ነፃ ዳቦ ለማቅረብ መጣሁ። ይህ ደግሞ በጣም ደስተኛ አድርጎኛል።" ሲሉ በትህትና ተናገሩ።

ምሁሩ ወደ ንጉሡ እየተመለከተ፡- “እኚህን ሽማግሌ እንዲህ ያለው ጥሩ አስተሳሰብ ትልቅ ያደርጋቸዋል።" አለ።

ከዚያም ወደ ሌላ መንደር ገብተው በዚያ አንድ ትምህርት ቤት አዩ። ሁለቱም ወደ ውስጥ ገብተው አንድ አስተማሪ አገኙ።

ንጉሡ መምህሩን፦ "ብዙ ተማሪዎችን ብታስተምር ምን ያህል ደሞዝ ታገኛለህ?" በማለት ጠየቁት።

አስተማሪውም፡- "ንጉሥ ሆይ፤ እኔ የማስተምረው ለደሞዝ አይደለም። እዚህ ምንም አስተማሪዎች አልነበሩም፤ የወደፊት ተማሪዎችም አደጋ ላይ ናቸው። ለዚያም ነው በየቀኑ ነፃ ትምህርት ለመስጠት እዚህ የምመጣው።" በማለት መለሰ።

ንጉሡ፦ "ታዲያ የኑሮ ወጪዎችህን እንዴት ትሸፍናለህ?" አሉት።

መምህሩም፦ "ከሕፃንነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ በእግዚአብሔር ቸርነት እንጀራ፣ ልብስና ቤት ተዘጋጅቶልኛል። ስለዚህ በዚህ መሥራት እችላለሁ።" አለ።

ከዚህ በኋላ ምሁሩ ለንጉሡ፦

"ለሌሎች የሚኖር ሰው ታላቅ ነው። እንደዚህ ያለ ታላቅ አስተሳሰባቸው፤ ታላቅ የሚያደርጋቸው እና ዕጣ ፈንታቸውን የሚወስን ብዙ ሰዎች አሉ። ሰው ታላቅ የሚባለው በትልልቅ ነገር ሳይሆን በበጎ አስተሳሰብና በበጎነት ድርጊቶች ነው።" አላቸው። ንጉሡም ተገረሙ!!

“እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ፦ ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።” (ሐዋርያት 20፥35)።

@Nolawiiher
@Nolawiiher

በቸር ዋሉ !
836 views Estifanos, 04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 06:21:44 ተላላፊ በሽታ

«እርስ በርስ በቅንነት ከመዋደድ የበለጠ ምንም ነገር ነፍስን ከፍ ሊያደርጋትና ብዙ ደስታን ሊሰጥ የሚችል ነገር የለም።»

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

ዓለም ሁለት ነገሮችን አጣምሮ የያዘ እምነትን ትፈልጋለች፡፡ በአስደንጋጭ ነገሮች የማይናወጥ መለኮታዊ እውነት እና ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ የሆነ የሕይወት ለውጥ ለማምጣት ሁልጊዜ የሚሠራ ኃይል ናቸው። ማንም ቢሆን የሚፈልገው ይህንኑ ይመስለኛል። እውነት የእምነት መሠረት ሲሆን፤ ያመነውን ተግባራዊ በሆኑ መንገዶች የምንኖርበት ኃይል ደግሞ ፍቅር ነው፡፡ እንድንወድ የማያስችል ሃይማኖት ገዳይ አስገዳይ ነው፡፡ ከፍቅር የተለየ ክርስትና ሰማያዊ እውቅና አይኖረውም፡፡ አምላካችን ታላቅ፣ ወሰን የለሽ፣ ሁሉን አዋቂ እና ሁሉን የሚችል የጸጋ አምላክ ነው፡፡ በእርግጥም እግዚአብሔር ተግባራዊ በሆኑ መንገዶች እንድንወድ ኃይል ይሰጠናል። ለስም አጠራሩ ክብር ይግባው!

የፍቅር ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ፡-

«እኛ ወንድሞችን የምንወድ ስለ ሆንን ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገርን እናውቃለን፤ ወንድሙን የማይወድ በሞት ይኖራል።» ይለናል፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ፡-

«ፍቅር ከሌለው ሁሉም ነገር ርኩስ ነው። አንድ ሰው ድንግልናውን ቢጠብቅ፣ ቢፆም ወይም በትጋት ቢጸልይ ወይም ለድሆች ቢመጸውት . . . አብያተ ክርስቲያናትን ቢያሠራ ወይም ሌላ መልካም ነገር ቢያደርግ ይህ ሁሉ ያለ ፍቅር በእግዚአብሔር ዘንድ አይቆጠርም። ምክንያቱም በእግዚአብሔር የማይፈለግ ነውና። ስለዚህ ያለ ፍቅር ምንም ነገር አታድርጉ፡፡» ይላል፡፡

ተወዳጆች፤ ፍቅር ዳግመኛ የመወለዳችን ማለትም ክርስቲያን የመሆናችን ማስረጃ ነው፡፡ «እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፥ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።» (ዮሐ. 13፥35) ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መከተላችን በተግባራዊ ሁኔታ የሚገለጠው ፍቅር ሲኖረን ነው፡፡ ፍቅር ግን ከሌለን . . . .

ቅዱስ ባስልዮስ፡-

«ባልንጀራን መውደድ ጠባዩ ምንድን ነው? የራስዎን ጥቅም ሳይሆን የሚወዱትን ሰው መንፈሳዊ እና አካላዊ ደኅንነት መፈለግ ነው። ባልንጀራውን የሚወድ ፍቅሩን ለእግዚአብሔር ይገልጣል፡፡» ይላል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ቅድስናን እና ለሌሎች የሚኖረንን ፍቅር በፍርድ ቀን ከመዳን እና ካለ መዳን ጋር ያያይዘዋል /ዕብ. 12፥14፤ ገላ. 5፥21፤ 1 ቆሮ. 6፥10/፡፡ ፍቅር የእምነት እውነታ ማረጋገጫ ነው፡፡ በእግዚአብሔር የተስፋ ቃሎች ላይ ያለን እምነት፤ ሰዎችን በመውደድ/ ባለ መውደዳችን ይፈተናል፡፡ ከክርስቶስ ጋር አንድ የሚያደርገን እና ኃይሉን የምንቀበልበት መንገድ እውነተኛ ፍቅር ነው። በምናየው ሰው በኩል የማይታየውን እግዚአብሔር የምናገኘው ሌሎችን በመውደድ ነው፡፡

ቅዱስ አግናጤዎስ፡-

«በዕድሜ፣ በጾታ፣ በደረጃ ልዩነት ሳትፈጥሩ፤ ለባልንጀሮቻችሁ ቅዱስ ፍቅር አሳዩ፡፡»

ተወዳጆች ሆይ ፤ ራሳችንን እንመርምር፡፡ እግዚአብሔር በሌሎች ምን ያህል ተወዳችኋል? ብሎ አይጠይቀንም፡፡ ነገር ግን ምን ያህል ለሌሎች ፍቅር ሰጥታችኋል? ብሎ ይጠይቀናል፡፡ ከሌሎች ምን ያህል እንደ ተቀበልን ሳይሆን እንዴት ለሌሎች በረከት እንደሆንን ይጠይቀናል፡፡ አምላካችን ስለ ሌሎች ስህተት አይጠይቀንም፤ ነገር ግን እነሱን ከስህተት ለመመለስ ስላደረግነው ጥረት ይጠይቀናል፡፡ ምን ያህል እንደ ተጠላን ሳይሆን ምን ያህል እንደ ወደድን፤ ምን ያህል እንደ ተገፋን ሳይሆን ምን ያህል እንዳቀረብን፤ ምን ያህል እንደ ተበደልን ሳይሆን ምን ያህል ይቅር እንዳልን፤ ምን ያህል እንደ ተፈተንን ሳይሆን ምን ያህል እንደ ታገሥን . . . . ይጠይቀናል፡፡ በእውነት ራሳችንን የት እንዳለን እንመልከት፡፡

እኛን እንዲሁም ሌሎችን ሊበክሉና ሊጎዱ የሚችሉ ተላላፊ በሽታዎች ሁለት አይነት ናቸው፡፡ አንዱ አይነት ሰውን ከውስጥ ሊጎዳ የሚችል ሲሆን፤ ነገር ግን ሌሎችን አይጎዳም፡፡ ሌላው አይነት ግን እኛን በመጉዳት ብቻ አይቆምም፤ ሌሎችንም ይበክላል። በአገራችን ሰው ብዙ ትኩረት ያልሰጠው ማስክና ሳኒታይዘር፤ ክትባትና ኦክስጅን የማያሽለው፤ መራራቅና አለመጨባበጥ የሚያባብሰው «ጥላቻ» የሚባል ተላላፊ በሽታ ተስፋፍቷል፡፡

እንደ ጥላቻና በቀል የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎች ይኖሩብን ይሆን? ከእኛ አልፈው በሌሎች ጆሮ ውስጥ የምናፈሳቸው የተሳሳቱ አሳቦች ይኖሩን ይሆን? በራሳችን ድክመቶች ተይዘን፤ ነገር ግን ሸክማችንን በሌሎች ላይ እየጫንን ይሆን? በመውደቅ ተጠላልፈን፤ ነገር ግን ለሌሎች ማሰናከያ ሆነን ይሆን? ጥላቻችን ብዙዎችን እየበከለ፤ እየገደለ ይሆንን??

@Nolawiiher
@Nolawiiher

«ፍቅርን ተከታተሉ፥» /1 ቆሮ. 14፥1/!!
1.3K views Estifanos, 03:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 10:45:55
1.2K views Estifanos, 07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 07:44:04 ንፁሕ ምንጭ

“መጽሐፍ ቅዱስ የዕንቁ ማዕድን ነው፤ የነፍስም የአትክልት ቦታ ነው።”

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

መጽሐፍ ቅዱስ ልክ እንደምንጠጣው ውኃ ነው። ያለሱ ምንም ማድረግ አንችልም። የዕለት ተዕለት ቋሚ ፍላጎት ነው። ይህን ፍላጎት ማሟላትም የነፍስ ዕርካታዋ ነው። የእግዚአብሔርን ቃል የበለጠ ማወቅና በጥልቀት መረዳት፤ በልምላሜ ማደግ፤ በፍሬአማነት መከበብ ነው። ለክርስቲያኖች ሁሉ የከበረ ውድ ስጦታ!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “መጽሐፍ ቅዱስ የእንቁ ማዕድን ነው፤ የነፍስም የአትክልት ቦታ ነው” የሚል ግሩም አባባል አለው። ለእኔና ለእናንተስ ቃሉ ምንድነው? ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ ደግሞ በእግዚአብሔር ጸጋ ነፍስ ወደ ከፍታ የምትመጣበት የጽድቅ መንገድ እንደ ሆነ ይነግረናል። ተወዳጆች ሆይ፤ ከዚህች ምድር ትርምስ በተለየ የከፍታ ጎዳና መጓዝን ትሻላችሁን? መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት፦ ማኅቶት ለእግርየ ሕግከ (ሕግህ ለመንገዴ መብራት ነው) /መዝ. 118፥105/ እንዳለ፤ ቅዱስ ቃሉ እጅግ ያስፈልገናል።

እያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው። ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር በሌለበት ከንቱ ዓለም፤ ዓይኖቻችን ከቃሉ ውስጥ ድንቅና አዲስን ነገር መጥገብ ይችላሉ።

ፍቅርን ተርበሃል/ሻል? ጭካኔ ከብቦን ርኅራኄ ለራቀብን፣ እንባ ቀለብ ሆኖን ደስታ ለተነፈግን፣ የፍትሕ ያለህ ጩኸታችን ሰሚ ላጣ፣ ከቀኑ ብርሃን በተቃራኒ ለጨላለመብን፣ የምንበላው አልታኘክ፣ የምንጠጣው አልወርድ ብሎ ደም ደም ለሚለን፣ የወገን ስቃይ፤ የምንሰማው ግፍ ላሰከረን፣ ቀና ስንል ከእግዜር በቀር ሁሉ ለቀለለብን፣ በ የት ልሂድ መቅበዝበዝ ማረፊያ ጥላ ላጣን፤ የእግዚአብሔር ቃል ያሳርፋል። በዚህ ውስጥ በጽናት ተጓዙ።

ተወዳጆች ሆይ፤ ከምንጩ ጋር እየተገናኘን ጠቃሚ መንፈሳዊ መጻሕፍትን እናንብብ። ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ በተቃዋሚዎች መካከል ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ ክፉዎች ሊቋቋሙ ያልቻሉበት፤ በጨለማ ፊት መልኩ እንደ መልአክ ያንፀባረቀበት፣ በሕይወቱም በሞቱም እግዚአብሔርን ያከበረበት ምሥጢር፤ እግዚአብሔርን ሰምቶ መታዘዝ ነውና ወደ ቃሉ ዘወር እንበል። የሰማዕታት አክሊላቸው የሆነ ክርስቶስ በመከራ መታገሥን ያስችለን። አሜን!

@Nolawiiher
@Nolawiiher

ሌሎችም ያንብቡ ።
1.4K views Estifanos, 04:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:34:29 ገብርኤል ጌታ ያለው ማንን ነው ?

ፍፁም ሰው ባይሆን፤ በግርግም ተኝቶ የነበረው ማን ነው? እርሱ ፍፁም አምላክ ካልሆነ፤ መላእክት ወርደው ያከበሩት ማንን ነው?

እርሱ ፍፁም ሰው ባይሆን፤ በመጠቅለያ ማን ተጠቅልሎ ነበር? እርሱ ፍፁም አምላክ ካልሆነ፤ እረኞቹ ያመለኩት ማንን ነው?

ፍፁም ሰው ካልሆነ፤ ማርያም ማንን አጠባች? ፍፁም አምላክ ካልሆነ፤ ሰብአ ሰገል ለማን ስጦታ አቀረቡ?

እርሱ ፍፁም ሰው ካልሆነ፤ ስምዖን ማንን በእቅፉ ተሸከመ? እርሱ ፍፁም አምላክ ካልሆነ፤ “በሰላም አሰናብተኝ።” ያለው ለማን ነው?

ፍፁም ሰው ካልሆነ፤ ዮሴፍ ማንን ወስዶ ወደ ግብፅ ሸሸ? ፍፁም አምላክ ካልሆነ፤ “ልጄን ከግብፅ ጠራሁት።” የሚለው ቃል በማን ተፈፀመ?

እርሱ ፍፁም ሰው ካልሆነ፤ ሐዋርያትና መላእክት ወደ ሰማይ ሲያርግ ያዩት ማንን ነበር? እርሱ ፍፁም አምላክ ካልሆነ፣ ሰማይ የተከፈተለት፣ ኃይላት በፍርሃት ያመለኩት፣ አብ “በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ማንን ነው?

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መድኃኒት ያለው፤ ኢየሱስ አዳኝ ነው። ቅዱስ ገብርኤል ጌታ ያለው፤ ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ነው። ቅዱስ ገብርኤል የምሥራች ያለው፤ ኢየሱስ ፍፁም ደስታችን ነው።

@Nolawiiher
@Nolawiiher

የመላእክቱ ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይሁን!!
1.9K views Estifanos, 05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ