Get Mystery Box with random crypto!

ኦርቶዶክስ310

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox31 — ኦርቶዶክስ310
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodox31 — ኦርቶዶክስ310
የሰርጥ አድራሻ: @orthodox31
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.65K
የሰርጥ መግለጫ

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምላክ አሜን ይህ የዩትዩብ ቻናል ስለ ቤተክርስቲያናችን የምንማማርበት ስለ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የምናውቅበት እንዲሁም ከሌሎች እምነቶች ስለሚነሱ ጥያቄዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃነት የምናቀርብበት መንፈሳዊ ቻናል ነው
Admin: - @ናዝራዊ

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-13 19:49:59 Watch "ቤተክርስቲያን ለምን ይቃጠላል?#orthodox #ኦርቶዶክስ #ኦርቶዶክስ_ተዋህዶ #ማህቶት #orthodox310 #ኦርቶዶክስ310" on YouTube


27 views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 10:57:37 ታቦት በሐዲስ ኪዳን ስንል ምን ማለታችን ነው


35 views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 10:53:31 መፀሐፍ ቅዱስ ስታነቡ ተጠንቀቁ የትኛው እና ትክክለኛው መፀሐፍ ቅዱስ የትኛው ነው በዩትዩብ ይዘንላቹ መተናል ተከታተሉ



63 views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 13:16:32 ቅድስት ድንግል ማሪያም መዳህኒት ናት ስንል እኛ ኦርቶዶክስያዊያን በምክንያት ነው እንጂ ጣኦት ማምለካችን አይደለም እሔን ድንቅ መልስ በዩትዩብ ተከታተሉ



77 views10:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 14:02:26 የዲያቆን ሔኖክ ድንቅ እና አስተማሪ የሆኑ ስብከቶችን ይዘንላቹ መተናል ሊንኩን በመጫን ቪዲዮን ተከታተሉ
ይጠቅማችኋል


98 views11:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 11:33:32

118 views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 11:28:45 ክርስቲያናዊ ህይወት
ክርስትና የሚለው ቃል “XPIETIAVOS” ኽርስቲያኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም የክርስቶስ መሆን ማለት ነው፡፡ ክርስትና ሰዎች በፍቅረ እግዚአብሔር ተስበው፤ ፈጣሪያቸውን አውቀው፤ እረፍትን ሽተው፤ በህጉና በትእዛዙ ፀንተው፤ ለመኖር ሲሉ ከዓለም ፈቃድ ተለይተው የሚኖሩበት ህይወት ነው፡፡ ይህንንም ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር ዮሐንስ “ዓለምን ወይም በዓለም ያሉትን አትውደዱ በዓለም ያለው ሁሉ እርሱም የስጋ ምኞትና የዓይን አምሮት ስለገንዘብም መመካት ከዓለም ስለሆነ እንጂ ከአባት ስላልሆነ÷ ማንም ዓለምን ቢወድ የአባት ፍቅር በእርሱ ውስጥ የለም፡፡
ዓለሙም ምኞቱም ያልፋሉ የእግዚያብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዐለም ይኖራል” (1ዮሐ 2፡16) በማለት ክርስቲያን ለመሆን በመጀመሪያ ዓለምን መካድ እንዳለብን ያስተምረናል፡፡ በክርስትና ወድቆ (ተረግሞ) የነበረው የሰው ዘር እንደ ተነሳ (እንደ ተፈታ)፤ የታመመው እንደ ተፈወሰ፤ የረከሰው እንደ ተቀደሰ፤ የሞተው እንደተነሳ፤የተሰበረው እንደተጠገነ፤ የሳተው እንደ ተመለሰ ይታመናል፡፡
የክርስትና መስራቹ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ነው፡፡ “በዚህችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሰራለሁ፡፡ የገሀነም ደጆችም አይችሏት” (ማቴ 16፡18) በማለት ቤተክርስቲያን ሳይሆን ቤተክርስቲያኔን የራሱ እንደሆነች በህያው ቃሉ አረጋግጦልናል፡፡
ክርስቲያኖች ክርስቲያን ከመባላቸው አስቀድሞ ምዕመናን (መዝ 100፡7) ፤ ደቀመዛሙርት (ኢሳ 8፡16) ፤ ወንድሞች (ማቴ 8፡10) የመሳሰሉት በመባል ይጠሩ ነበር፤ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ክርስቲያን ተብለው ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰየሙት በአንጾኪያ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት እንደነበር ቅዱስ መጽሀፍ ይነግረናል፡፡ (የሐዋ 11፡26)
በምድራችን በሺዎች የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ይገኛሉ፡፡ የሃይማኖታቸውን መስራች ስናጠና ግን ሰዎች ሆነው እናገኛለን፡፡ ትምህርታቸው ዛሬም በተከታዮቻቸው ይኑር እንጂ እነርሱ ግን በህይወት የሉም፤ የክርስትና ዋና መስራች ግን ትናንት የነበረ ዛሬም ያለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ዐልፋና ዖሜጋ ዘዓአለማዊ በመሆኑ ዛሬም ስራውን አላቆመም ማለት ነው፡፡ ክርስቲያናዊ ህይወት ለመኖር ክርስቲያኖች የሚከተለውን መተግበር እንዳለብን የህይወት ምንጭ የሆነው መጽሀፍ ቅዱስ ያስተምረናል፡፡
1.    እግዚያብሔርን ማወቅ
መቼም ዓለም አንድ መንደር በሆነችበት ዘመን ስለ እግዚያብሔር ያልሰማ አለ ብሎ ለመናገር ያስቸግራል፡፡ ይሁን እንጂ ከዕውቀት ብዛት እግዚአብሄርን የካዱ (እግዚአብሔር የለም) ያሉ በርካታ ሰዎች በምድራችን መኖራቸው ግልጽ ነው፡፡ ይህም ስንፍና እንጂ እውቀት እንዳልሆነ ልበ አምላከ ቅዱስ ዳዊት ይነግረናል፡፡ “ይበል አብድ በልቡ አልቦ እግዚአብሔር” ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል (መዝ 13፡1)፡፡ ፍልስፍና ማለት ጥበብን ማፍቀር ማለት እንጂ እግዚአብሄርን አለማወቅ ወይም መካድ ማለት አይደለም፡፡ አንድ ልጅ አባቱን አላውቅህም አባቴ አይደለህም ስላለው አባቱ አልወለደውም ማለት አይደለም እንዳውም ልጁ ሲጠራ አባቱን የካደ ልጅ ተብሎ ይጠራል፡፡
እግዚአብሄርን ማወቅ፡-
ትርጉም ያለው ሕይወት ይሰጣል
በምድራችን ትርጉም ያለው ሕይወት ማለት ምን አልባት የሚመስለን ሀብት፤ ንብረት፤ ስልጣን ፤ ጥሩ መልበስ፤ ጥሩ መመገብ ፤ ጥሩ ቤት መኖር ሊመስል ይችላል፡፡ ነገር ግን ትርጉም ያው ህይወት መኖር የሚቻለው እግዚአብሄርን ሲያውቅ ነው፡፡ በዚህ ዘኪዎስ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል፡፡ ዘኪዎስ ጌታውን ሳያውቅ የኖረበት ዘመን ትርጉም አልባ ህይወት ነበር አምላኩን ሲያውቅ ግን “ጌታ ሆይ ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ ማንንም በሃሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው” (ሉቃ 19 ፤9) በማለት አዲሱ ክርስቲያናዊ ህይወት ምን እንደሚመስል ነግሮናል፡፡
ታሪክን ይቀይራል
ሰዎች እግዚአብሄሔርን ሲያውቁ ዘማዊ የነበረው ድንግል፤ ዘረኛና ወገንተኛ የነበረው ሁሉን በክርስቶስ አንድ አድርጎ የሚያይ ፍትሃዊ፤ አሳዳጅ የነበረው ስለ ክርስቶስ ተሳደጅ፤ ክፉ የነበረው ደግ፤ ዘፋኝ የነበረው ዘማሪ፤ ነፍሰ ገዳይ የነበረው የሰውን ህይወት የሚያድን ወዘተ ይሆናል፡፡ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ጥሩ አስረጅ ይሆናል፡፡
2.    በዕምነት ማደግ
ብዙዎች ክርስቲያን ተብለው ይጠራሉ ጥቂቶች ብቻ በእምነት ውስጥ በጥበብ ይኖራሉ፡፡ “ዕምነት ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነውና” (ዕብ11፡1) የሰው ልጅ በሃይማኖት ካልኖረ ለምኞቱ ገደብ የለውም፡፡ ያለኝ ይበቃኛል አይልም፡፡ አመንዝራ ሲያይ በፍትወት ስሜት ይቃጠላል፣ የወይን ጠጅ በብርሌ ባማረ መልኩ ባየ ጊዜ መጠጥ ያምረዋል ለዚህ እኮ ጥበበኛው ጠቢቡ ሰለሞን “ከተማን ከመግዛት ራስን መግዛት ይበልጣል ያለው”
109 views08:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 18:01:12 እግዚአብሔር ይመስገን ኦርቶዶክስ ያደረከኝ አምላክ ድንቅ አባቶች አሉን እኮ እሔን ድንቅ ቪዲዮ ተከታተሉ ስለ ፀሎት አስተምረውናል


409 views15:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-25 07:51:19

284 views04:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-24 08:03:04 ሰማእቷ ቅድስት አርሴማ
የክርስቶስ ሙሽራ
ገድሏን በድንቅ አቀራረብ
አቅርበንላችዋል
ሊንኩን በመጫን ይከታተሉ


312 viewsedited  05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ