Get Mystery Box with random crypto!

ፍቄ ክራር ቲዩብ-Fike Kirar Tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ aboutkirar — ፍቄ ክራር ቲዩብ-Fike Kirar Tube
የቴሌግራም ቻናል አርማ aboutkirar — ፍቄ ክራር ቲዩብ-Fike Kirar Tube
የሰርጥ አድራሻ: @aboutkirar
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.13K
የሰርጥ መግለጫ

መንፈሳዊ የክራር ትምህርት
.....ስለ ክራር ለማወቅ እና ክራር ለመማር/ለመለማመድ አሪፍ ቻናል ነው....እንዲሁም መዝሙሮችን በቁጥር እየለቀቅን እናስተምራለን.....
.
.
ከእርሶ የሚጠበቀው አሪፍ ክራር እጅዎ ላይ እንዲኖር ብቻ ነው....
.
.
እንዲሁም፡ ለክራር የሚያስፈልጉ ነገሮችን እንለቃለን.....
ሠላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
@aboutkirar...
ሊንኩን ሼር እናርግ

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 08:08:02
. Elohe Graphics

ለፕሮፋይል ፒክቸር የሚሆኑ ልዩ ኦርቶዶክሳዊ ፎቶዎች
ለ ቴሌግራም የሚሆኑ ፕሮፋይል ፒክቸሮች

የ መፅሃፍ ቅዱስ ጥቅሶች በፎቶ

ለ ስጦታ የሚሆኑ በልዩ ዲዛይን የቀረቡ የፀሎት ቤት እቃዎች

የ ፃድቃን ስዕለ አድኅኖዎች

የ ኦርቶዶክሳዊ ቻናሎች ልዩ ልዩ ሎጎዎች
መንፈሳዊ ፎቶዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ
መልሶት አዎ ከሆነ ከስር ያለውን ሊንክ በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ ገብታችሁ እዩት በጣም ትደነቁበታላችሁ
ቻናሉን ለመቀላቀል ሰማያዊውን ይጫኑ


https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

108 viewsማኅቶት ፕሮሞሽን 1000_5000, 05:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:11:52 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






154 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 21:43:33 መንፈሳዊ ትረካ እና አጫጭር ጽሑፎች:
የማንንን ስብከት ፈልገው አጥተዋል ሁሉንም በአንድ ቻናል ይዘንላችሁ መጥተናል ከ58ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ቻናል ከፍተናል

➥የመምህር ምህረተአብ አሰፋ ስብከት

➥የዲያቆን ሔኖክ ኃይሌን ስብከት

➥የመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳንን ስብከት

➥የቀሲስ ዶክተር ዘበነ ለማን ስብከት

➥የመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ትምህርቶች

➥የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን እይታ

➥የሊቀ ሊቃውን ዕዝራ ሐዲስ ስብከት

ቻናሉን ለመቀላቀል ሰማያዊውን ይጫኑ


https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

291 viewsማኅቶት ፕሮሞሽን 1000_5000, 18:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:07:32 መንፈሳዊ ትረካ እና አጫጭር ጽሑፎች:
የማንንን ስብከት ፈልገው አጥተዋል ሁሉንም በአንድ ቻናል ይዘንላችሁ መጥተናል ከ58ሺህ በላይ ተከታይ ያለው ቻናል ከፍተናል

➥የመምህር ምህረተአብ አሰፋ ስብከት

➥የዲያቆን ሔኖክ ኃይሌን ስብከት

➥የመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ አባ ገብረ ኪዳንን ስብከት

➥የቀሲስ ዶክተር ዘበነ ለማን ስብከት

➥የመጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ትምህርቶች

➥የዲያቆን ዳንኤል ክብረትን እይታ

➥የሊቀ ሊቃውን ዕዝራ ሐዲስ ስብከት

ቻናሉን ለመቀላቀል ሰማያዊውን ይጫኑ


https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk

112 viewsማኅቶት ፕሮሞሽን 1000_5000, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 21:57:46 ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
#በእውነተኛ_ታሪክ_ላይ_የተመሰረተ
ክፍል 1
#ባለታሪክ_እና_ጸሀፊ
ናሕድ ማሕሙድ ሙቱዋሊ
#ተርጓሚ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

ናታኒም ቲዩብ SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ያበረታቱ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና።






219 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 18:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 23:40:22
የፎቶ ማስረጃ:- በሁለት እጅ ቤዝ እና ሊድ ክራር ሲደረደር
498 viewsFike, 20:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 17:22:19 ስለ ክራር ጠቃሚ መረጃ ነው

በተጨማሪም በፎቶ ማስረጃ እንለቃለን ይጠብቁን
716 viewsFike, 14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 17:20:19 ስንት አይነት ክራር አለ?

በመሰረቱ 3 የክራር አይነቶች አሉ...እነርሱም
1ኛ. ድርድር (ሊድ) ክራር
2ኛ. ግርፍ ክራር
3ኛ. ቤዝ ክራር

1ኛ. ድርድር (ሊድ) ክራር:- ይህን ክራር ለድርድርም ለግርፍም መጠቀም ይቻላል ይህ ክራር በተለምዶው ሁሉም ሰው እጅ ላይ የምናየው ነው...ምክንያቱም ለግርፍም ለድርደራም ስለሚጠቀሙበት ማለት ነው...ይህ ክራር በተለያዩ የድምፅ ሳጥኖች ሊሰራ ይችላል።
ለምሳሌ:-
ከእንጨት የሚሰራ ገበቴ (የድምፅ ሳጥን) ለምሳሌ-ከዋንዛ እንጨት
በጣም ትልቅ ከሆነ ቅል የሚሰራ ገበቴ (የድምፅ ሳጥን)
ከትልቅ ጎድጓዳ ሰሀን የሚሰራ ገበቴ (የድምፅ ሳጥን)
ከኮምፖርሳቶ (ስስ ጣውላ) የሚሰራ ገበቴ (የድምፅ ሳጥን)

ለዚህ የድርድር ክራር የምንጠቀማቸው የክር አይነቶች...የውሀ ክር(የአሳ ማጥመጃ ስትሪንግ string) ፣ የጫማ መስፊያ ጅማት እና የመሳሰሉት...እኔ የምመክረው ግን የውሀ ክር(የአሳ ማጥመጃ ስትሪንግ string) ነው። ዋጋው ቢበዛ 500 ነው...አነሰ ከተባለ ደግሞ ከ250-300ETB ነው። የሚገኝበት ቦታ ደግሞ አዲስ አበባ መርካቶ አይጠፋም። አልያም ደግም በናዝሬት (አዳማ) ከተማ ላይ ካሉት ABC tradings ውስጥ አለ።

2ኛ. ግርፍ ክራር :-ይህ ክራር አብዛኛው ሰው ሙሉ ለሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ለዘፈን ነው የሚጠቀመው። አብዛኛው የግርፍ ክራር ከቤዝ ክራር ጋር አሰራሩ ተመሳሳይ ነው። የሚያለያያቸው ነገር string (ክር) ነው።
አብዛኛው የመድረክ ግርፍ ክራር ተጫዋቾች የሚጠቀሙት የክር አይነት የሽቦ ስትሪንግ ነው። በሌሎች ክሮች መጠቀም ይቻላል። ነገር ግን በጣም የሚያምር ድምፅ የሚያወጣው የክሩ አይነት ሽቦ ሲሆን ነው።

3ኛ. ቤዝ ክራር:- ይህ ክራር ደግሞ በአይነቱም በድምፁም ከሁሉም ክራር ለየት ተደርጎ ነው የሚሰራው።
ድምፁ ከሌሎቹ ለየት ያለ ወፍራም እና የሚያምር ድምፅ ነው ያለው።
ይህ ክራር ጥቅሙ የሊዱን ክራር ወይም የድርድሩን ክራር ድምፅ ተከትሎ በወፍራም ድምፁ የእነዚህን ክራር ድምፅ ማሳመር ነው።
ይህ የክራር አይነት ሁለት አይነት አመታት አለው። እንደ ግርፍ ክራር በጭራሽ አይመታም።

1ኛው አመታት:- በግራ እጃችን ወደ መቃኛው አካባቢ ከፍ ብለን አምስቱ ጣቶቻችንን በስድስቱ ክሮች መካከል አስገብተን ፤ በቀኝ እጃችን ደግሞ ሶስቱ ጣቶቻችንን በመጠቀም እየደረደርን ከግራ እጃችን ጋር እያግባባን አንዳንድ ክር እየመታን እንጠቀመዋለን ማለት ነው። ይህ አመታት በዓለማዊም በመንፈሳዊም መጠቀም ይቻላል።

2ኛው አመታት:- ሁለተኛው አመታት ደግሞ ይህን ቤዝ ክራር ከሊድ (ከድርድር) ክራር ጋር አንድ ላይ ይዞ በመጫወት መምታት ነው።

@aboutkirar
@aboutkirar
@aboutkirar
6.8K viewsFike, 14:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 13:19:32 ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል ?

ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል

ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል

ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና

ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና

ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው

ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበርካታ ዓመታት ሲወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው

@aboutkirar
@aboutkirar
@aboutkirar
1.1K viewsFike, 10:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 11:38:44

1.5K viewsFike, 08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ